>
8:02 pm - Tuesday June 6, 2023

የዶ/አብይ አህመድ የለውጥ ተስፋዎች ምን ነበሩ ወጤታቸውስ ?!? (አስገደ ገብረስላሴ) 

የዶ/አብይ አህመድ የለውጥ ተስፋዎች ምን ነበሩ ወጤታቸውስ ?!?

ክፍል 1 
 አስገደ ገብረስላሴ
ኢትዮጱያና ህዝቦቻ ለማዳን ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው!!!  

ይድረስ ለዶ/ አብይ አህመድ ዓሊ፤ የዜጎች ሀሳብ አስተያዬት መቀበል በኣቦቶቻችን ባህል ጨዋነት ነው ይሉታል ።እኔም እንደ አባትም እንደ ዜጋም የአለፈውና የአሁኑ ያለው የአብይ አህመድ የሁለት አመት ተኩል ክፉ የአገዛዝ ዘበን አስተያዬትም ሀሳብም ልትቀበለኝ በማክበር እጠይቃለሁ ፤
ዶክተር አብይ አህመድ አሊ እኔ የ72  አመት እድሜ የሽማግሌ ጎልማሳ ነኝ ስለእኔ ወርቃማ ታሪክ  የታጋይነቴን  ማንነት ለአንተ የተደበቀ አይሆንም።በአጭሩ የህዋሓት ኢህአደግ ታማኝ  ታታሪ ለኢትዮጱያ ህዝቦች ከ ከጭራቁ ፋሽሽታዊ ደርግ በማላቀቅ ረገድ ወሳይ ሚና የነበረኝ ጅግና ህዝባዊ ታጋይ እንደነበርኩ የትግራይ ህዝብ በሙሉ ፤የኢትዮጱያ ህዝብ ደግሞ በከፊል ያውቀኛል ። ከህዋሓት ኢህአደግ በሀሳብ ተለይቸ ከወጣሁ እኖሆ 29 አመት አስቆጥሬ አለሁ ።በለፉት 29 አመታትም በግልም በፖለቲካ ፓርቲ በመደራጀት እየታገልኩ  በዚህ የህዋሓት የጭቆና ማእከል የሆነ መቐለ እኖራለሁ ። እኔ ከታገልኩበት ዘመን ጀምሮ እስከ ዘንድሮ ህዝብን የሚበድል ነገር ካየሁ ለህዝብ መብት የሚነካ ሁሉ አልቀበልም ።ፊት ለፊትም እጋፈጠዋለሁ ፣ በአስገደ  ገብረስላሴ ቤት መንበርከክ የሚባል አይታሰብ ።
ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ተከታታዮቼ ሁሉ አሁን በክፍል በክፍል እማቀርበው አስተያዬት በጽሞና ትካታተሉኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ ፤
 ክፍል 1
ዶክ/ አብይ አህመድ መጀመሪያ አንተና ቡዱኖችህ   ከኢህአደግ ማህጸን  ውስጥ 27 አመት ሙሉ አብራችሁ ኖሯችሁ  ከአፋኝ እሱር ቤት ለመውጣት በህዝቦች ፣ በተፎካካሪ ፓርቲ ጥያቄ  ተነስቶ ነገር ግን  እናንተም በተዋናይነት የተሳተፋችሁበት በኢህአደግ ጸረ ዲሞክራሲያዊ አሰራር  ምክንያት እጅግ ቡዙ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ፣አባሎቻቸው  የታሰሩበት ፣የተሰቃዩበት የተሰደዱበት የሞቱበት  ስርአት  የፈጸመው ወንጀል በመኮነን ፤ የዜጎች ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ  ተገንዝባችሁ  የኢህአደግ ካቴና ሰብራችሁ ያሁላ ሰው በላ የአፈና ካድረ መረብ በጣጥሳችሁ   ወጥታችሁ የቡዙሀኑ ህዝቦች ጥያቄ እንዲሁም በደርዘን የሚቆጠሩ ተፎካካሪ ፓርቲ ፣ፖለቲኮኞች ጥያቄ ታጥቃችሁ ትወጣላችሁ ተብሎ  ፍጺም የማይታሰብ ፣የማይገመት በመኖሩ በወቅቱ ለመላው የኢትዮጱያህዝቦች በየ ነበሩበት ቦታ ሀቅ ነግተዋል ወይ በማለት ትንሳኤ ሙውታን ሆኖባቸው   ነበር ።
ዶክ / አብይ አህመድ የለውጥ ሀይሎች ብላችሁ መጀመሪያ ብቅ እንዳላቹሁ በሀገራችን የነበረ እናንተ  ተሳታፊ የነበራችሁበት ኢህአደግ በፈጠረው የየተባላሸ አስተዳደር ውጤት በተፈጠረው ዘርፈ ቡዙ ጭቆና ፣ ያለማጣራት በጅምረላ እስራት ፣ግድያ ፣ እጅጉን የተስፋፋ ሙሱና ፣በዘር በዘመድ በጋብቻ በስልጣን መባለግ አስወግደን በሀገራቸን ሁሉም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት እናመጣለን ብላችሁ ብቅ ማለታችሁ ህዝቦች  ባገር ውስጥም በዲያስቦራም የነበሩ የኢትዮጱያ ህዝቦች 80 % ከዛበላይ  አዳባባይ እየወጡ ድጋፋቸው ሰጥተዋቹሁ ነበር ። ሌላ ቀርቶ አሁን በጠላትነት ፈርጃችሁት ያላቹሁ የምትጠሉት የትግራይ ህዝብም እንኳ ቢያንስ 90%  ህዝብ አደባባይ በመውጣትም በየቤቱም ፣በቡዱንም በተናጠልም ይደግፋችሁ  ነበር ። በዛንግዜ ነው አንባገነኑ እና አፋኙ የህዋሓት የአማራር ቡዱን እንዲሁም ሰው በላ ካድሬዎቹ ለሀጫቸው የጣሉት በዛው ሰአት ነበር ።
የኢትዮጱያ ህዝብ በሙሉ የተፎካካሪ ፓርቲ አማራር አባሎቻቸው ፣ደጋፊዎቻቸው ሁሉም ለውጥ ፈላጊ ዜጋ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉ ሲያሳያቹሁ ዋናው ሚስጢሩ  በኢህአደግ አስከፊ ስርአት ቆሽጡ ተቃጥሎ ስለነበር ነው ።
እናንተም በግብታዊ ስሜት መንፈስ በመጋጋል ሁሉም ፖለቲካ እስሮኞች ይፈቱ ከእንግዲህ ወዲህ ኢትዮጱያ ሀገራችን ዜጎች ያለ አንዳች ተጨባጭ ማስረጃ በጥርጣሬ የማይታሰርባት፤ ዜጎች በድህንነቶች በፖሊሶች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ የማይታሰሩባት ፣የማይሳቀዩባት ፣የማይገደሉባት ፣ ፖሊሶች ከዳኞች በላይ መሆናቸው ያበቁባት ፣ካድሬዎች በዜጎች ላይ የማይፈነጩባት ኢትየጱያ ትሆናለች ብላችሁ  በአደባባይ ቃለማሀላ  ፈጽማችኃል ። ።ሁሉም ዜጎች የሚሳቃዩባቸው የነበሩ የድህንነት ማእከላት አፍርሰን በመዝጋት  መናፈሻ (ሙዜሞች) ይሆናሉ ። በኢህአደግ አሸጋሪ አፋኝ ስርአት በውጭ የተሰደዱ ፖለቲከኞች ፣ወይ በግለሰው ጥላቻ የተሰደዱ ሙሁራን ባገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ያልቻሉ ነፍጥ አንስተው በበረሀ ከኢህአደግ ጋር ለ27 አመት ያህል ሲፋለሙ  የለነበሩ ። በዲያስፖራ  ተደራጅተው ጥገኛ የነበሩ ፣ ፓርቲዎች በሙሉ ሀገራቸው ገብተው በነጻነት በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ በማወጃችሁ  ፤ ከሁሉም ነገር ነጻና ገለልተኛ የሆነ  ምርጫ ቦርድ ነጻ ፍትሀዊ ታማኝ ግልጽና ሁሉም ፖለከኞች የሚወዳደሩበት ምርጫ ቦርድ እናቋቁማለን ።  ሁሉም አይነት ሚዲያዎች የመንግስትም የግልም ነጻ  ሆነው እንዲዘግቡ ፣ ለመንግስትም ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እኩል የሚዲያ ተጠቃሚነት ይኖራል ዜጎች በሰላማዊ ሰልፊ ፣በመሰብሰብ ያለአንዳች ተጽእኖ  ሀሳባቸው እንዲገልጹ ተቃውሞ ወይ ድጋፍ ሊያሰሙ ይችላሉ ተብሎ ታወጀ ።  የባለጉ የበሰበሱ ሙሶኞች ክራይ ሰብሳቢዎች በህግ እርምጃ እንወስዳለን ፣በዘር በዘመድ አዝማድ ፣በጋብቻ የተሳሰሩ የመንግስት ቢሮክራሲ መዋቅር ከስር መሰረታቸው አፍርሰን በቡቁ ሙሁራን እንተካለን ብላችሁ ምላችኃል ። ።
ሌላስ የዶክ/አብይ አህመድ የለውጥ ቡዱን ሀገሪቱ የምትመራበት የአጭርና የረጅም ስትራተጅ ፖሊሲ  በሚመለከት  የፖለቲካዊና ስነሀሳባዊ ( አይዶሎጂ ) መርሆዎቹ እንደነገረን መደመር ፣አብሮነት፣ አንድነት ፣ይዘን ወደ ብልጽግና እንገሰሰገሳለን ወ ዘ ተ የሚሉ መፎኮሮች ይዞው በመላው ሀገራችን አስተጋቡ። ይሁን እንጅ የዶክ/ አብይ አህመድ ተስፋዎች አብዛኛው የኢትዮጱያ ህዝቦች በጥርጣሬ አይን ይመለከታቸው ነበር ።ምክንያቱም የዶክተር አብይ አህመድ የአዲሱ የለውጥ ሀይል የመዋቅር መረብ የሚመለከቱዋቸው  የነበሩ ታማኝ መዋቅሮች በሙሉ  ( 100 ) የወደቀው የኢህአደግ ስርአት ከጠ/ ምኒስቴር ቢሮ ጀምሮ እስከ ቀበሌ  የተዘረጉት ባለስልጣናት በሙሉ   በዘመነ ኢህአደግ ተሻሚዎች ካድሬዎች ሆነው ህዝባችን ያሰቃዩ ሰለነበረ በህዝብ መተማመን አልነበም ።ይይ ሆኖ ግን በአብይ አህመድ የለውጥ ሞፎከር ምክንያት ከላይ እንደገለጽኩት መላው ሀገራችን ዜጎች  በድጋፍ ሰላማዊ ሰልፊ ተናወጠች ።
የአብይ የለማ ቲም ዳያስፖራን ለመነሳሳት  ወደ አመሪካ ፣አውሮፓ ፣መካከለኛ ምስራቅ ( አረብ አገሮች ) አቀኑ ። እዛውም ቢሄር ሀይማኖት በማይ ለይ  እጅግ በቡዙ  ሞቶ ሽዎች የሚገመቱ ህዝቦች  ተቀባይነት  አግኝተው በአለም ታይቶ የማያውቅ  የድጋፍ  ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገላቸው ። በኢህአደግ  ጸረዲሞክራሲ አሰራርር ፖሊሲ ባለመቀበላቸው ተባርረው ፣ሸሽተው የነበሩ ዜጎች    ቁጥር ስፍር የሌላቸው  እጅግ ቡዙ ተፎካካሪ ፓቲ ግለሰዎች ፖለቲኮኞች ወደ ናፎቃት ሀገራቸው በገፍ ገቡ ።
      ከላይ የተዘረዘሩ የአብይ አህመድ የለውጥ ሀይል ተስፋዎች እንዴት በተግባር ዋሉ ለሚለው ዝርዝር መልስ በክፍል 2 ተከታተሉ ።
                       መቐለ ፣
               01  / 02 / 20 13
Filed in: Amharic