ስለ ጋዜጠኛው ከውቅያኖሱ በሻይ ማንኪያ!
……ዳንኤል ሽበሺ
ጋዜጠኛ ተመስገን ቢታሰርም ባይታሰርም ነፃ ሰው ። ቀድሞ ለሀገሩ የሞተ በድን ነውና ። ስለ ነፃነት እናውራ ካልን ደሞ ነፃነት ከውስጥ የሚፈልቅ እንጂ ከውጭ የሚጫን ሶፍትዌር አይደለም ።
በእነሱ ቋንቋ ጋዜጠኛው አንድ ብጫ ካርድ ተሰጥቶታል ። ከዚህ በኋላ አንድ ብጫ ካርድ ይቀረዋል ። ሁለት ብጫ ቅጣት ካርድ አንድ ቀይ የቅጣት ካርድ ብዬ ነው። ዞሮ ዞሮ ተሜ Black list ውስጥ መግባቱን መጠርጠር ጠርጣራነት ነው ።
ብጫዎቹም ሆነ ቀያዩ ካርዶች ለእሱ እንደ ወርቅ ሜዳሊያ Golden Medals ሽልማት ናቸው ። የማይታጠፉ ክንዶች የማይደርቅ ቀለማት የማይሸራረፍ ብዕረኛ የማይፋቁ ቀለማትን እየተፋ ከሐቅ ጋር እየተጋፈጠ ይቀጥላል። #ሰው ማለት እውነቱን ተናግሮ ፣ የተሸፋፈነውን ገልጦ፣ በትንተና አሳምኖ በመሸበት የሚያድር ነው ። ጋዜጠኛ ስንል ሰው ማለታችን መሆኑ መቸስ አይጠፋብንም ።
በቅን ልቦና ለሀገራቸውና ለሐቅ የቆሙ ሁሉ በፈጣሪና በሕዝብ ልብ ውስጥ ለዘለዓለም ይኖራሉ ። አንረሳችሁም !!!