>
5:13 pm - Tuesday April 18, 8028

ተስፋፊነት እና ወረራ ኦሮሚያን የመሰለች ኢትዮጵያ የመፍጠር ጉዞ ብልፅግናን የት ያደርሰዋል (በለስ ሚድያ)

ተስፋፊነት እና ወረራ ኦሮሚያን የመሰለች ኢትዮጵያ የመፍጠር ጉዞ ብልፅግናን የት ያደርሰዋል?

በለስ ሚድያ

– [ አደገኛው የማንቂያ ደወል ለኢትዮጵያውያን – ክፍል 1 ]
– በመተከል  በኩል ያለውን ጭፍጨፋ  እውነት ህወሓት ብቻ የምትፈፅመው ነው????
 
ከለውጡ ጋር የመጣውን ሁሉንም የኦሮሚያ አመራር የሚያስማማው ቁምነገር : ”ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ኦሮሞን የመሰለችና የኦሮሞ ሁሉን አቀፍ ብልጫና ቁጥጥር ያረጋገጠች : ኦሮሞን የመሰለች ኢትዮጵያ መሆን አለባት” የሚለው ነው።
➢ ለማ መገርሳ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቁጥጥር ለመፍጠር ህዝብ ወደአዲስአበባ ማስፈር አለብን ሲል ÷ ታከለ ኡማ እሱን ሲያስፈፅም ÷ ጃዋር አዲስአበባ የእኛ ነች ሲል ÷ ጠሚሩ እንዳላየ ሲሆን ÷ የኦሮሚያ አክቲቪስት በታከለ ላይ የነበረው በጎ አመለካከት÷ ቅሬታዎች ሲነሱ ዝም ማለት የአላማ መመሳሰል ነው።
➢  ሽመልስ አብዲሳ “በኦሮሞ አምሳል የተቀረፀ ፓርቲ እና ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ኢትዮጵያን የሚመራበት ስርዓት ተፈጥሯል” ሲል የግሉ አስተያየት ተባለ እንጂ በልሒቃኑ ዘንድ አንዳችም ልዩነት የለም።
➢ እነሌንጮ ባቲ ለቀጣይ ሶስት ሺህ አመት ኦሮሞ የሚመራት ኢትዮጵያ እንደምትሆን ሲገልፅ ÷ ሕዝቆኤል ጋቢሳ  የሰሜን አቢሲንያ ልሒቅ ከእንግዲህ ወደስልጣን እንደማይመጣ ሲገልፅ በሁሉም ልሒቅ ዘንድ አንድም ልዩነት  ስሌለ ነው።
እናም በአካሔድና አቀራረብ እንዲሁም የስልጣን ፍክክር ይለያዩ ይሆናል እንጂ የኢትዮጵያን ግዛቶች በማጥቃት በመስፋፋት እንዲሁም በሪፍረንደም ጠቅልሎ ብሔሮችን assimilate አድርጎ ኢትዮጵያን ኦሮሞ ማድረግና በኦሮሞ አምሳል መስራት የለውጡ መነሻና በጥብቅ እየተፈፀመ ያለ ነው።
==
ቀደም የህወሓት አመራር ክልሎችን የሚያስፈራራው “አማራ ይውጣችኋል” እያለ ነበር። አሁንም ድረስ የትግራይ ልሒቅ የሚፈራው አማራን በመሆኑ ለዘመናት የያዘውን “ጠቅላይ አግላይ አሃዳዊ” የሚሉ ፍረጃዎች አልጣላቸውም።
አማራን ለማስፈራራት ደግሞ : ”እምቢ ካላችሁ ስልጣኑን ለኦሮሞ ሰጥተነው እንሔዳለን” ይል ነበር።
ለሁሉም መፍትሔ ሕወሓት/ኢሕአዴግ መሆኑን ለማስረገጥ ይለው የነበረ ነው።
በህወሓት ግንዛቤ “ጠባብ” የሚላቸው “የእኩልነት እንጂ የጥቅለላ አጀንዳ የላቸውም : ኦሮሞ ደግሞ እንኳን ሊጠቀልል ተገንጣይ ነው” የሚል ግምገማ ይዞ የሠራው ፌደሬሽን ነው።  “ጠቅላይነት የትምክህት ኃይሉ ነው” ስለሚል የግዛትና ስነሕዝብ ብዛት ከአማራ ለማሸሽ ጭምር ፖለቲካዊ ውሳኔ አሳልፎበታል።
መቶ ሃምሳ አመት ተጉዘው ወዲህም የህወሓትን ፖለቲካ ሲያወግዙ የነበሩት የኦሮሞ ልሒቃን ደግሞ የሚያወግዙትን ራሳቸው ለራሳቸው ፍላጎት ሊደግሙት እየሮጡ ነው።
– ዛሬ ህወሓት ” ያልኩት አልቀረም: ይበላችሁ” እንዲል ክልሎችም  “የህወሓት ዘመን በስንት ጣዕሙ” እንዲሉ የሚያደርገው የጥቅለላ ጉዞ ተጀምሯል።
-ብልፅግና ፓርቲም ሲነሳ በያዘው መርሁ  በብሔሮች ባለቤትነት የተተረተረችውን አገር በጋራ የፖለቲካ መድረክ የጋራ አገር የማድረግ ሳይሆን “ኦሮሞን እንድትመስል” የማድረግ ከሆነ መድረሻው የት ይሆን?የሚያሰኝ ሁኔታ ተፈጥሯል።
-አሁን ኦሮሚያ በወሳኝነት በክልሉ መዋቅር እንደሚደገፍ በሚገለፀው ታጣቂ ቡድን በሁሉም ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ግዛቶች ላይ ጥቃት ከፍቶ ማስከፈት ÷  ሰዎችን አስገብቶ ማስፈር እና መጠቅለል ትልቁ ተግባር ሆኗል።
በቀዳሚ ክፍል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ የሚደረገውን ጥቅለላና የመዋጥ አደጋ (assimilation) እንመልከተው።
==
➀ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን የመዋጥ እርምጃዎች
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የኦሮሚያ አመራር የወረራና ጥቅለላ ትኩረት ተደርጎበት እየተሰራበት ያለ ነው።
ሀ) ጥቅለላው ‘የተጠናቀቀው’ የማኦኮሞ ወረዳ
ቤኒሻንጉል ጉሙዝን ከጋምቤላ የሚያዋስነው የማኦኮሞ  ወረዳ አሁን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ጥቅለላና ወረራ የተፈፀመበት ነው።
ከዚህ ቀደም በነበረው የአገሪቱ ካርታ ኦሮሚያ ክልል ከሱዳን የሚዋሰንበት አካባቢ አልነበረም። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መግለጫም ” ክልሉን በደቡብ የጋምቤላ ክልል ያዋስነዋል” ይል ነበር። አሁን ግን በሁሉም የካርታ መረጃዎች ላይ  ኦሮሚያ ከሱዳን በስፋት እንዲዋሰን ሆኗል።  [ see Maps ]
ይህን ለማድረግ መጀመሪያ በአካባቢው ታጣቂ በማስረግ ጥቃት መፈፀም ቀጥሎም የተጠቁ ሰዎች ሲሸሹ በስራና መሰል ጉዳይ ሰዎች ማስገባት የአፈፃፀም ቅደም ተከተል ነው። በማኦ ኮሞ ወረዳ በእርሻና በእጣን ለቀማ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ የተፈፀመው ጥቃትና አፍኖ መሠወር ተግባር የሚታወቅ ነው። አሁን ደግሞ ብልጫ ቁጥጥር በተያዘበት አካባቢ የኦሮሚኛ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ እየሆነ ነው።
ለ) ከፊል ግዛቷ የተወሰደው yaso ወረዳ
መተከል ውስጥ አባይን ተሻግሮ ያለው ወምበርማ ወረዳ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ወረዳ እንጅ ከኦሮሚያ ጋር ድንበር አልነበረውም::
በካርታው ላይ በቀስት የተመለከተው የያሶ ወረዳ ክፍል ከተጠቀለለ በኋላ ግን የኦሮሚያ ድንበር አባይ ድረስ ሆኗል።
በወቅቱ ሁኔታውን የፃፈው Getahun kassahun እንዲህ ብሎ ነበር።
” The Oromia Region has annexed parts of the Benshagnul-Gumuz (BG) areas adjacent to the Abay River by stealth and are now administered by so-called Oromia region. In the process, Oromia Police forcefully displaced Gumuz residents from their places. For example, I have confirmed about 730+ Gumuz people were forced to flee to the low-laying areas of Womberma Woreda of Gojjam (metekel) across Abay River. “
በያሶ የሚኖሩ ጉሙዞች ከተገፉ በኋላ  ኦነግ መተከል ላይ ፅ/ቤት  ስላለው  በርካታ ታጣቂዎቹ ሰርገው በመግባት በወንበራ : ቡለን እና ጉባ ወረዳዎች በዋናነት የአማራ አገውና ሺናሻ ነዋሪዎች ላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ጥቃት በመፈፀም መተከልን የመውረር ስራው ተጀምሯል።
በመተከል ከሚደርሰው ጥቃት ጀርባ ኢ-መደበኛው የኦሮሚያ ታጣቂ ከሌሎች ኃይሎችና አኩራፊዎች ጋር በመተባበር የሚፈፀም ነው። በገንዘብ ተገዝተው ቀዮችን ግደሉ የሚባሉ እና ለጥቃት የሚሰለፉ አኩራፊዎችም አሉ።
 “መተከል የኦሮሚያ ነው” የሚለውን የኦነግ/ኦህዴድ ትርክት ለማሳካት አላማ ያደረገ : የታሰበበትና የታቀደ ኦፕሬሽን ነው።
በተጠቀለሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎች የኦሮምኛ ቋንቀበ ትምህርት እንዲሰጥ እየተደረገ ነው።
በቀጣይ ልክ ከሱማሊ አዋሳኝ አካባቢዎች ጋር ሲደረግ እንደኖረው አይነት በሕዝበ ውሳኔ (Referendum) ድንበሮች ይለዩ የሚል “ሰላማዊ መፍትሔ”  ከአራት ኪሎ ይቀርባል።
ከዚያ በፊት የአባይ ግድብ በኦሮሚያ የተከበበ ነው እስኪባል ድረስ የኦነግ ሸኔ ኢ-መደበኛ ኃይል ጥቃት እያደረሰ ነዋሪን እያፈናቀለ በሚከፍተው በር በርካታ ነዋሪ ማስፈር በትኩረት ይሰራል።
አሳዛኙ ነገር የክልሉ አመራር ይህንን የመዋጥ እርምጃ የመናገር እንኳ ድፍረት አጥቷል። ይባሱንም በነሽመልስ አብዲሳ በኩል ከአማራ ክልል ጋር ትወግናላችሁ የሚል ማስፈራሪያ አለበት።
አመራሩ ፀባዩን ካላሳመረም ከስልጣን በማንሳት ከኦሮሞ የተዋለደ ወይም ከአማራ ቅራኔ ያለውና የነሽመልስ ታማኝ እንዲሾም ይደረጋል።
በዚህ ሁኔታ “ብልፅግና” የኦሮሞ ጥቅለላ መሳሪያ ተደርጎ ቢታይ ምኑ ይገርማል? በዚህ ሁኔታ ክልሎች “የሕወሓት አገዛዝ በስንት ጠዓሙ”  ቢሉ ይፈረዳል??ይሄንን ስል ህወሀትን መናፈቄ ግን እንዳልሆነ አንባቢ ሆይ  አስምርልኝ !
ይቀጥላል
Filed in: Amharic