>
5:33 pm - Tuesday December 5, 8215

ፍርድ ቤት የሚባል ነገር  ምን ያደርጋል - ለምን አትዘጉትም??  (ሀብታሙ አያሌው)

ፍርድ ቤት የሚባል ነገር  ምን ያደርጋል – ለምን አትዘጉትም?? 

ሀብታሙ አያሌው

ፍትህ ባፍጢሟ ተደፍቶባት  ፓርክ የሚሰራላት አገር !!
 
ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ  “የእርስ በእርስ ግጭት በመቀስቀስ እና የሽብር ተግባር ለመከወን መንቀሳቀስ” በሚል ወንጀል ከሰሱት  ህግ አለ ብለው  ፍርድ ቤት አቀረቡት።
የራሳቸው የካንጋሮ ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲፈታ ወሰነለት ያለምንም የህግ መሰረት ለ3 ወራት አስረው አስቀመጡት። በዚህ አላበቁም ለእስራቸው የህግ ከለላ ለመስጠት ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ጠየቀ።  ጨዋታው ቀጠለ…  ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙን ውድቅ አድርጎ መለሰ ድሪባ  ከእስር እንዲፈታ ውሳኔውን አፀና።  ህግ እና ፍትህን በአፍጢሙ የደፋው ብልፅግና ግን  አሁንም  አልፈታውም።
እኔ የምለው ታዲያ ፍርድ ቤቱ ምን ያደርግላችኋል ? ለምን አትዘጉትም ?
ፍትህ ባፍጢሟ ተደፍቶባት  ፓርክ የሚሰራላት አገር !!
Filed in: Amharic