>

የገዳ ሥርዓት (አቻምየለህ ታምሩ)

የገዳ ሥርዓት

[ክፍል ፩]
አቻምየለህ ታምሩ

የኦሮሞ ብሔርተኞች ኦሮሞ ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ ዲና [ጠላት] እያሉ ጥላቻ በማስተማር ባሳደጉት የቄሮ ትውልድ ጭካኔና አውሬነት የረኩ አይመስልም። ይህም በመሆኑ አውሬ ካደረጓቸው የኦሮሞ ቄሮዎች አልፈው የአዲስ አበባ ልጆችም ገዳ የሚባለውን ኋላቀር የወረራና ወታደራዊ ሥርዓት እንዲያውቁና ወደ አረመኔነት እንዲመለሱ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ነግረውናል።
የገዳ ሥርዓት የኦሮሞ የገዢ መደብ ኢትዮጵያን ሲወር ከ28 በላይ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን፣ ነገዶችን፣ ማንነቶችንና ባሕሎችን በተሳከ ሁኔታ ያጠፋበት ወታደራዊ ሥርዓት ነው። የገዳ ሥርዓት በኦነጋውያንና ደቂቆቻቸው እንደሚደሰኮረው እንኳን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሊሆን ቀርቶ የፖለቲካ ስርዓት እንኳን አልነበረም። የገዳ ሥርዓት የአርመኔነት ጥግ የታየበት ወታደራዊ ሥርዓት ነበር። ይህን የምለው ፈጥሬ ሳይሆን ከዋናው የገዳ ታሪክ መዝጋቢ ከአባ ባሕርይ መጽሐፍ በተጨማሪ አባ ባሕርይ የጻፉትን ታሪክ ዝቀው የመመረቂያ ወረቀቶቻቸውን ካሰናዱት ከኦሮሞ ብሔርተኞቹ ከፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ከፕሮፈሰር ሕዝቃኤል ጊቢሳ፣ ከፕሮፌሰር ተሰማ ጠአ፣ ወዘተ ጽሑፎች ሳነብ ያገኘሁትን ታሪክ መሰረት በማድረግ ነው።
የገዳ ሥርዓት ከሌሎች ወታደራዊ ሥርዓቶች የሚለየው በምርኮኞች ላይ ሳይቀር ritualized የሆነው culture of violenceን ተቋማዊ ማድረጉ ነው። ሌሎች ወታደራዊ ሥርዓቶች ሰላማዊ ሰው አይገድሉም፤ ተፋላሚ ጠላት እንኳ ቢሆን የምርኮ አያያዝ ሥርዓት አላማቸው። የገዳ ሥርዓት ግን ተቀዳሚ ኢላማው የታጠቀ ተፋላሚ ኃይል ሳይሆን አገር አማን ብሎ የተቀመጠ ሰላማዊ ሕዝብ ነው። በገዳ ሥርዓት አንድ ሰው ለግድያ ከመሰማራቱ በፊት ለወኔው ማነሳሻ ብዙ ደም ይጠጣል፡፡ ከዚያም አገር አማን ነው ብሎ የሚሄደን መንገደኛ ወይም በቤቱ የተቀመጠን ሰላማዊ ሰው አድብቶ በመግደል ወንድ ከሆኑ ብልቱን፤ ሴት ከሆነች ደግሞ ጡቷን ቆርጦ ወደ ጎጆው ይመለሳል፡፡ ሲመለስ ፉከራ ያሰማል፡፡ እንዲሁም ሰልቦ የገደለውን ሰው ያሰማውን የጣእር ድምጽ አስመስሎ በመጮህ ያፌዛል፡፡ አንድ የኦሮሞ ወንድ ይህንን ማድረግ ከቻለ ብቻ ነው በጆሮው ላይ የብር ሎቲ ማንጠልጠል የሚፈቀድለት ወይም በግንባሩ ላይ ከለቻ የሚያስረው።
በቡታ በዓል ሰው ገድሎ መመለስ ያልቻለ ኦሮሞ ውርደት ይከናነባል፤ በግንባሩ ላይ ምልክት ይደረግበትና ወንድ አለመሆኑ ለማሳየት በትንሽ እቃ ወተት ተሰጥቶት ቅቤ እስኪወጣ ድረስ እንዲገፋው ይደረጋል። አንድ ኦሮሞ ሰው ካልገደለ በቀር በገዳ ሥርዓት ውስጥ ቦታ አይኖረውም፡፡ [ Huntigford, G. W. (1955). The Galla of Ethiopia: The kingdoms of Kafa and Janjero, Page 64]
ብቸኛው የገዳ ታሪክ ምንጭ አባ ባሕርይ ምስጋና ይግባቸውና የገዳ ሥርዓትን ከእድሜ ደረጃ አወጣጥ ጀምሮ እያንዳንዱ የሥርዓቱ ደንቦች የተቃኙት ወታደራዊ የበላይነትን ለማስገኘት እንደሆነ አስገንዝበውናል። በገዳ ሥርዓት መሪ ሆኖ የሚመረጠው ሰው ከእድሜ አቻዎቹ ብዙ ሰው የገደለው ነው። ከመመረጡ በፊት ሰውን አድኖ ገድሎ ለመረጃነት ይዞ ያልተገኘ ኦሮሞ በገዳ ሥርዓት አይመረጥም። በገዳ ሥርዓት አንዱ ሉባ ከጓደኞቹ መካከል በልጦ ለመገኘት በተለይ ወንዶችን፣ በእናት ማኅጸን ውስጥ ያለ ሕጻንን ጨምሮ ገድሎ ቸብቸቦውን ይዞ መቅረብ የሥርዓቱ አንድ አካል ነው። ባጭሩ የገዳ ስርዓት የገዳዮች ስርዓት ነው።
የገዳ ሥርዓት ምንም ዓይነት የዲሞክራሲ መልክ እንዳልነበረው የሚያሳየው ሌላው አቋሙ የፖለቲካ ስርዓቱ መሪ (አባ ቦኩ) በቤተሰብ ተወራራሽ ወይም ከልጅ ልጅ የሚያልፍ መሆኑ ነው። እውነተኛው ኦሮሞ ምንም እንኳን በቁጥር ትንሽ[ከአስር እንድ] ቢሆንም ወታደራዊ የበላይነትን እንዲያገኝ ያደረገው ይህ ለጦርነት የሰላው አደረጃጀቱ ግን ቁጥሩ እንዲበዛ አድርጎታል። አባ ቦኩ (የፖለቲካ ቢሮው) ከልጅ ልጅ የሚተላለፍ በመሆኑ ተቋማዊ ትውፊቱን (institutional memory) ሲያስቀጥል የወታደራዊ ክንፉ የሚሞላው በጉልበትም፣ በእድሜም የመግደል ችሎታቸው ከፍተኛ በሆኑ መሪዎች ነበር። ይህ በሌሎች የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች ከነበረው ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ ከሚተላለፈው የስልጣን ሽግግር ሙሉ በሙሉ የተለየ ነበር።
ሞጋሳ የገዳ ሥርዓት ምሰሶ ነው። የሞጋሳ ሥርዓት የተጀመረው እውነተኛ ኦሮሞ የሆኑት የቦረናና ባሬንቱ ነገዶች ወረራ ሲጀምሩ የሚወሩት ግዛት እያሰፋ በመሄዱ ቁጥራቸው ሳስቶ ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ነበር። በዚህ ጊዜ የወረሩትን አካባቢ ሙሉ በሙሉ ከመግደል የማረኩትን ባሪያ፣ ገባርና ገርባ ቢያደጉት የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ተረድተው የመጀመሪያ ልምዳቸውን ሻሽለውታል። በዚህ ጊዜ ነበር የጉዲፈቻና ሞጋሳ ሥርዓቶች በስራ ላይ መዋል የጀመሩት። ቦረናና ባሬንቱ ሲስፋፉ በጦርነት የያዙትን ሕዝብ ገድለው ከመጨረስ ይልቅ ባሕሉንና ቋንቋውን በማጥፋት፣ በምንም ዓይነት ማንነቱን ወደ ኋላ እንዳያስታውስ አድርገው የአባቱን ስም ሳይቀር በመቀየር ለጦርነቱ የሚማገድ ኃይል ለማድረግ ነበር ሞጋሳ የተጀመረው። እንዲህም ከተደረገ በኋላ በሞጋሳ የተያዘው ኦሮሞ አልተደረገም ገርባ እንጂ። ገርባ አገልጋይ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞው በፈለገ ጊዜ የሚሸጠው ባሪያም ነበር። ለዚህ ምንጭ የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን ከሰላሳ ዓመታት በፊት “The Oromo of Ethiopia: A History, 1570-1860” በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ገጽ 126 ላይ የጻፈውን ያነቧል።
የሞጋሳ ስሪት ከልጅ ልጅ የሚተላለፍ ሥርዓት ነበር። በገዳ ሥርዓት መሰረት ገርባ የተደረገው ሕዝብ ማንነቱን እንዲያጣ ተደርጎ፤ ከማኅበራዊ ቦታውም ወጥቶ መሬትም ሆነ ሌላ ንብረት እንዳያፈራ ይከለክላል። ገርባ የኦሮሞ ንብረት ብቻ ነበር። ባጭሩ ገርባ ምንም እንኳን ኦሮምኛ እንዲናገር ቢገደድም ኦሮሞ ግን ፈጽሞ አልነበረም፤ እንዲሆንም የገዳ ሥርዓትም አይፈቅድለትም።
ከ17ኛው እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ ድረስ አብዛኛው የባሪያ አቅራቢዎች ሞቲ[የኦሮሞ ንጉሥ] የሆኑት አንጋፋዎች እንደነበሩ የተመዘገበ ታሪክ ነው። በዚህም የተነሳ አብዛኛው ባሪያ ኦሮምኛ ተናጋሪ ነበር። ይህ ማለት ግን ሞቲዎች ለሽያጭ የሚያቀርቡት ኦሮሞዎችን ነበር ማለት አይደለም። በሞቲዎችና አባገዳዎች ለሽያጭ የሚቀርቡት አገልጋይ የነበሩ ገርባዎች ነበሩ። በደቡቡ፣ በምዕራቡና በመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ከአባገዳ መር የዘር ጀኖሳይድ የተረፉት ነገዶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሞቲ ባሪያ ፈንጋዮች ጥቃትን ያስተናግዱ ነበር። ለዚህ የሚከተሉትን እውነታዎች መጥቀስ ይቻላል።
ዳግማዊ አባ ጅፋርን በ1904 ዓ.ም. በሚኖሩበት ጅማ ሄዶ የጎበኛቸው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም አባ ጅፋር «ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካባቢውን ሕዝብ በተለይም የሞችን በባርነት ሽጦ እንደጨረሰው» ኦቶባዮግራፊ [የሕይወቴ ታሪክ] በሚል ባዘጋጁት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ አስፍረዋል።
በ1916 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] አባል ለመሆን ባመለከተችበት ወቅት በእንግሊዝ መንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦባት ነበር። የኢትዮጵያን መንግሥት የአባልነት ማመልከቻ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] ለማስገባት ወደ ጀኔቫ የተላከው ቡድን መሪ የነበሩት ራስ ናደው አባ ወሎ በፈረስ ስማቸው «አባ መብረቅ» እንግሊዝ ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር አባል እንዳትሆን የተቃወመችበትን ምክንያት ለንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በላኩት የቴሌግራም መልዕክት፤
 
«እንግሊዝ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሐን የዘገቡትንና በሱዳን፣ በኬንያ፣ በኤደንና በግብጽ ባሉት የቅኝ ግዛት መንግሥቱ በኩል የሰበሰበውን ማስረጃ በማያያዝ በደቡብ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስለነበረው የባርያ ንግድ ሁኔታ፤ በተለይም የጂማው አባ ጅፋር በከፋ፣ በማጂ፣ በጊሚራና በጉራፈርዳ ሕዝብ ላይ እየካሄዱት ያለው መጠነ ሰፊ የባሪያ ንግድ ለማኅበሩ የፖለቲካ ኮሚሲዮንና ለጠቅላላ ጉባኤ በማቅረብ አባል እንዳንሆን ከፍተኛ ተቃውሞ አቅርቦብናል» 
 
ሲሉ አስረድተዋል።
 
ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በአባ ጅፋር አማካኝነት የሚካሄደው የባርያ ንግድ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሶ እንዲታገድና የሰው ልጅ መብት በመላው የአገሪቱ ግዛት እንዲከበር የአልጋወራሽ ተፈሪ መንግሥት ለመንግሥታቱ ማኅበር ቃል በመግባት ኢትዮጵያ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከመስከረም 17 ቀን 1916 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ማህበር 57ኛ አባል ሆና መመዝገቧ በይፋ ታወጀላት።
 
ባጭሩ በአባ ገዳ የተመራው የኦሮሞ ገዢ መደብ ወረራ ተሳክቶለት ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠር ኖሮ ሁሉም ባሕልና ቋንቋ ተጨፍልቆና ተሰልቅጦ ዛሬ ሁሉም አንድ ወጥ ኦሮሞ ብቻ ይሆን ነበር። ለዚህ ማሳያው ቀላል ነው። ኦሮሞ በወረራ የያዛቸው የጥንት ነገዶች ሙሉ በሙሉ ወደ ኦሮሞነት ተቀይረዋል። ኦሮሚያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከኦሮሞ ወረራ በፊት ይኖሩ የነበሩት ጥንታዊ ነገዶች ሁሉ ጸድተው ማንነታቸውን እንዲቀይሩ ተገድደዋል። ይህም የሆነው በዋናነት በገዳ ሥርዓ ነው። እንደ መልካም ነገር የአዲስ አበባ ልጆች እንዲማሩት እየተፈለገ ያለው ይህንን ጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገዶች የጸዱበትን ሥርዓት ነው።
 
ገራሚው ነገር ዛሬ ገዳን ለሌላው ሊያስተምሩ የተነሱት ባለጊዜዎች «ተበደልን፣ የዘር ጥቃት ደረሰብን» ብለው ሊያለቃቅሱ የነበሩና በጦረኛ አባገዳዎች ተሸንፈው የተያዙ ገርባ ልጆች መሆናቸው ነው። እነዚህ ገርባዎች ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ተነስተው አባ ላፋዎች [የኦሮሞ የመሬት ከበርቴዎች]፣ ሞቲዎች፣ መልከኞች [የአካባቢ ገዢዎች]፣ አባ ገዳዎች ወዘተ ጠቅልለው ከያዙት መሬት ውስጥ ቀንሰው የሚያርሱት መሬትና የግል ንብረት ባለቤት እስኪያደርጓቸው ድረስ መሬትም ንብረትም እንዳልነበራቸው አያውቁም። ይህን ባለማወቃቸው ዛሬ በኦነጋውያን በየአካባቢው የሚደርሰውን ጥቃትና ተዳፍኖ የቆየው ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች በሞጋሳ የጠፉበት የገዳ ሥርዓት የወለደውን ጦረኝነት ክፍል ሁለት ለማስቀጠም ገዳን ሊያስተምሩ ይዳዳቸዋል።
 
 
ኢትዮጵያ የተወረረችበትን፣ ነባር ነገዶቿ ከርስታቸው የፈለሱበትን፣ 400 ዓመታት ሙሉ በደም ጎርፍ የታጠብንበትን፣ ከ28 በላይ የኢትዮጵያ የጥንት ነገዶች ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ የጠፉበትን የገዳን ሥርዓት ከጥፋቱ ለተረፉት ማስተማር ስድስት ሚልዮን አይሁዶችን ለጥፋት የዳረገውን የናዚ ሥርዓት ለእብራውያን ልጆች ከማስተማር ተለይቶ አይታይም። የናዚዎቹን ስኬት ለማስተማር የሚፈልጉ የሉም ማለት አይደለም። በደንብ አሉ። ሆኖም ግን ታሪክ በትክክል በመነገሩ ጨካኝ የናዚ ሥርዓት በዓለም ላይ እየተወገዘ እንዲኖርና ተመልሶ እንዳይመጣ ተደርጓል። በአገራችን ግን ታሪካችንን በደምብ ባለማወቃችን፣ የዘር ማጥፋትን የተካሄደበትና ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች የጠፉበትን ገዳን እንደበረከት እንድንማረው እየተደረግን እንገኛለን። ታሪካችንን ጠንቅቀን ያወቅን ቢሆን ኖሮ የጠፋንበትን ወታደራዊና የወረራ ሥርዓታቸውን እንድንማር ሳይሆን በወረራ በያዙት ባድማ ላይ የነባሩን ሕዝብ ቋንቋ፣ ባሕልና ሃይማኖት አጥፍተው የሰፈሩት የሥርዓቱ ባለቤቶች የሆኑት አባገዳዎች ቋንቋና ባሕላቸውን ላጠፉባቸው፣ መሬታቸውን ነጥቀው ገርባ ላደረጓቸው፣ ባሪያ አደርገው ለሸጧቸው ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ እንችል ነበር።
Filed in: Amharic