የጉራ ፈርዳ አሰቃቂ ግድያ ማን ላይ አነጣጠረ ??
በዲን.ዶር.ያየህ ነጋሽ
* አማራን_ማኅበራዊ_ረፍት_መንሳት…‼️
“የኦሮሙማ ፕሮጀክት ይሳካ ዘንድ አማራው እንደ አውሬ እየታደነ መታረድ አለበት፡፡”አማራን ማኅበራዊ ረፍት መንሳት” የምትለዋ የትህነግ ማኒፌስቶ በመጨረሻዋ ህቅታ በማደጎ ልጇ አብይ አህመድ አስፈፃሚነት፣ በብአዴን/ ብል*ግና አጋፋሪነት፣ በእኛ እንዝላልነት ለተረኞች አስረክባ የጭንጋፍ ርዕያቸው ማስፈፀሚያ ሆናለች፡፡”
(1) ጉራ ፈረዳ ወረዳ ውስጥ በሠፈራ የሚኖሩ ብዙ
አማራዎች አሉ። እነኚህ ሰዎች ከ1990ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ስቃያቸውን ሲያዩ የቆዩ ናቸው።
(2) የሸኮ (ሸካ አይደለም) ብሔረሰብ አባላት ከቤንቺ ማጂ ዞን ተገንጥለው ዞን የመመሥረት ጥያቄ አላቸው።
(3) ከሰሞኑ አንድ ትልቅ የደቡብ ክልል ባለስልጣን
አካባቢውን ጎብኝቶ እንደተመለሰ ከ3 ቀናት በፊትጀምሮ የታጠቁ ሸኮዎች በአካባቢው የሚገኙ አማሮች ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ።
(4) በመገናኛ ብዙኃን እንደተነገረው ወደ 31 ንጹሐ ተገድለዋል። እየተለመደ የመጣው የጭካኔ አገዳደል
እዚያም አካባቢ ታይቷል።
(5) አብዛኞቹ የሞቱት የእስልምና እምነት ተከታዮች (ከ20 በላይ) ሲሆኑ የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ አመራር አባል የነበረ አንድ ሰው ተገድሏል።
(6) የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጽላት ወጥቶ ወደ
መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንዲገባ ተደርጓል።
(7) ባጠቃላይ 3 አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል።
(8) ሕዝቡም ተፈናቅሎ የተወሰነው ወደ ቢፍቱ ከተማ የተወሰነውም ወደ አማን ገብቷል ተብሏል።
(9) መከላከያውም እንደተለመደው አልታዘዝኩም ብሎ አደጋው እስኪባባስ ድረስ ዝምታን መርጦ ቆይቷል ተብሏል።
በመንግስታዊ እቅድ አማራን የማፅዳት ዘመቻ ደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ ገብቷል፡፡ ከሽፈራው ሽጉጤ የቀጠለው አማራን የማፅዳት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ እስካሁን የሟቾች ቁጥር 60 ደርሷል፡፡
ይህ ሰው በህግ ሲጠይቅ ሳይሆን በብልፅግና አምባሳደርነት ሹመት ሲቸረው አካባቢው ላይ አንግሷቸው የመጣቸው ሹማምንት ከእሱ የተሻለ በመጨፍጨፍ ሹመትን እንደሚጠብቁ አለመጥርጠር የዋህነት ነው።የሽፈራውን በዚህ ወንጀል አለመጠየቅ የሚመለከቱ የአካባቢው ባለስልጣናት ዛሬም ተመሳሳይ ጭፍጨፋ እያስፈፀሙ ይገኛል።የጭፍጨፋው ቀጣይነት እና መንግስታዊ ድጋፍ መኖሩን ለማየት ይህ በቂ ነው።
የሚሆነው ሁሉ የህገመንግስት፣ የመንግስት ተቋማት እና ኃላፊዎቻቸው ድጋፍ ያለው ብቻ ሳይሆን መንግስት መር ጥቃት ነው።
በጉራ ፈረዳ በ2004 እና 2005 ዓም የተፈናቀሉ ዐማሮች ቁጥራቸው ከ 20,000 ይበልጣል። የሳብ ሰሃራን ቴሌቪዢን ቁጥሩ ከ 22,000 በላይ እንደሆነ ዘግቦት እንደነበር የሚታወስ ነው።ይህ ክልል የዐማራውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በስፋት የተፈጸመበትና የዐማሮች ደም በእጁ ያለ አንዱ ቦታ ነው።
ዝሆኖች ሲሻኮቱ በመሀል የሚጎዳው ሳሩ ነው፡፡ዝሆኖቹ ለመጣላት ሆነ ለመታገል አንድ ሺህ አንድ ምክንያት ሊኖራው ይችላል፡፡ግጭቱ አካባቢያቸውን የሚያተራምስ ከሆነ ግን ላደረሱት ጉዳትም ሆነ ጥቃት ከተጠያቂነት አያመልጡም፡፡
ሰሞኑን የተከሰተው አረመናዊ ድርጊት የሳሮቹ አምሳያ የሆኑትን ንጹሀን ዜጎን ህይወት በገፍ መፍጀት ነው፡፡
እኔን ሁሌም የሚያመኝ በጥጋበኞች ሴራ ነባይ ወገኖቻችን ከለላ አጥተው እንደዋዛ ውድ ህይወታቸውን ማጣት ነው፡፡
ይህ በጥቁር መዝገብ የሚመዘገብ ታሪክ ይቅር የማይለውና በተለይም ጠንሻሹን ሀይል ከተጠያቂነት የማያስቀር አካይስታዊ ድርጊት መሆኑን ባለጊዜዎች ሊያጤኑት ይገባል፡፡