>
5:28 pm - Monday October 10, 6681

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ በሹፒ እና አሮጌ ብርሀን ቀበሌዎች በአማራ ላይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል!

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ በሹፒ እና አሮጌ ብርሀን ቀበሌዎች በአማራ ላይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል!

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
      አዲስ አበባ ሸዋ

ከፌደራል፣ከደቡብ ክልል እና ከቤንች ሸኮ ዞን ወደ ጉራ ፈርዳ ወረዳ ያቀኑ አመራሮች ከኡጅንታ፣ሹፒ እና ጌኒቃ ቀበሌ ከወጣጡ ተፈናቃዮች ጋር በወረዳው ዋና ከተማ ቢፍቱ አዳራሽ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጧል።
ከእያንዳንዱ ቀበሌ ሰላሳ ሰላሳ ሰዎችን ያሳተፈ ውይይት ስለመካሄዱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ውይይቱ በምን ጉዳይ ላይ እንዳተኮረ የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በጉራ ፈርዳ ወረዳ ከሹፒ፣ ከኡጅንታና ጌኒቃ ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ከ2 ሽህ በላይ ንፁሀን በቢፍቱ ከተማ በትምህርት ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በተያያዘ በዛሬው እለት ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ዋስትና የሚሰጠን ማን ነው፤እጣፈንታችን ምንድን ነው? በሚል በቢፍቱ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በሞከሩ በመጠለያ ባሉ ተፈናቃዮችና ነዋሪዎች ላይ በዱላ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ገልፀዋል።
ጥቅምት 11 ለ12 ምሽት የሸኮ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቻቸው የፈፀሙትን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ 21 አስከሬን እንዲነሳ ማድረጋቸውን የገለፁት የዐይን እማኝ በቢፍቱ እና በሚዛን ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙን ጠቁመዋል።
ሌላው ጥቅምት 8ለ9 ሌሊት በጉራ ፈርዳ ሹፒ ቀበሌ በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ አማራዎች ምሽት ላይ የመከላከያ ልብስ የለበሱ የሸኮ ታጣቂዎች በፈፀሙት አሰቃቂ ጭፍጨፋ 15 አማራዎች መገደላቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
የሹፒው ጥቃት በአካባቢው የመስተዳድር አካላት ተባባሪነት በሴራ እንደተፈፀመ ነው  ተፈናቃይ ወገኖች የገለፁት።
ይኸውም በእለተ እሁድ ጥቅምት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በጌኒቃ ቀበሌ ተቆርቋሪና የሚፈሩ የተባሉ 21 አማራዎች ከቀኑ 10 ሰዓት አንድ ሰው በመግደል ተጠርጥራችኋል በሚል ሰበብ በሚሊሻዎች እንዲታሰሩና ከፍተኛ ድብደባ እንዲፈፀምባቸው ተደርጓል፤ የተወሰኑት መሳሪያቸውን
እንዲያወርዱ ስለመደረጉ የዐይን እማኞችና ታስሮ የተፈታ ምንጫችን ተናግሯል።
በማግስቱ የጌኒቃ ቀበሌ አማራዎች ወንድሞቻችን አስራችሁ አስጨረሳችሁን በሚል መቃወማቸውን ተከትሎ አስከሬን አንሱ በሚል ስለመለቀቃቸው የተናገሩት የመረጃ ምንጫችን ጌኒቃ ለሹፒ ቀበሌ አዋሳኝና በር በመሆኑ ሆንተብሎ የአፀፋ ምላሽ ይሰጣሉ የተባሉ ተቆርቋሪዎች ታስረው ስለማደራቸው ጠቁመዋል።
 አማራን ለማጥቃት ሲፈልጉ የተቀነባበረ ሴራ በመፍጠር፣ በራሳቸው የገደሉትን ሳይቀር አማራ ነው የገደለው በማለት ጭፍጨፋ መፈፀም የተለመደ ሆኗል ነው ያሉት።
እንደአብነትም ከሹፒ ቀበሌ ወደ ጌኒቃ ከሄዱበት ያለበደላቸው በሚሊሻዎች ታስረው ያደሩት አቶ ጣሰው ሙሉጌታ ስልካቸውን ተቀምተው በማግስቱ ተፈተው ወደ ሹፒ ሲመለሱ በቤተሰቦቻቸው ላይ ግድያ በመፈፀሙ ሀዘን ጠብቋቸዋል።
የቅርብ ጓደኛቸው ተገድሏል፤ያሳደጉት ሰው ቆስሏል፤ እስካሁን አድራሻው ያልታወቀም አለ።
ሆንተብሎ ጥቅምት 8ለ9 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በጌኒቃ ቀበሌ ታስረው እንዲያድሩ ከተደረጉት አማራዎች መካከል:_
1)ደሳለኝ አበበ የቀበሌው ምክትል አስተዳዳሪ -ጦር መሳሪያውን አስወርደው።
2)አቶ ቢያልፈው- ጦር መሳሪያውን አስወርደው።
3)አቶ ጣሰው ሙሉጌታ -መሳሪያውን አስወርደው።
4)ይርጋ ደለለኝ
5)ጥላሁን አስርዴ
6)አመኑ ማናሌ
7)ወርቄ ይርጋ
8)አንማው ታደሰ
9)ወንድይፍራው ለሽ
10)ወንድሜነህ አበበ
11)ምንአለ በላቸው
12)ዘለቀ ሙላቱ
13)ከተማው ማሙሻ
14)ማንአዬ በላይነህ
15)አሰፋ መካሻ
16)አማኑኤል ማንአሌ
17)እማወቅ ታደሰ
18)አብነው ንጉሴ
19)ወንድምነህ ከፍያለኝ
20)ይታገስ ሰለሞን
21)ሻንቆ ፈርዴ
22)አቶ ወርቁ
23)አቶ ጀማል
በእስር ላይ ያደሩት አማራዎች በሹፒ ቀበሌ ጥቅምት 8ለ9 ምሽት ከተገፀመው ግድያ ማግስት ተለቀዋል።
ለምን ታሰራችሁ? በማለት የአማራ ሚዲያ ማዕከል የጠየቀ ሲሆን ያሰሩንማ አላማቸውን ከማስፈፀም ውጭ አንድም የሰራነው ወንጀል የለም ብለዋል። ወንጀል ቢኖርብንማ በማግስቱ እንዴት እንፈታለን ሲሉም ጠይቀዋል።
በመዋቅሩ ያሉ አመራሮች ጭምር በአማራው እልቂት ላይ እጃቸው አለበት ያሉት የዐይን እማኞች ዩኒፎርምና ጥይት ማነው የሚሸጥላቸው? ሲሉም ይጠይቃሉ።
በጥቅምት 8 ቀን 2013 ዓ.ም የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ በመጡበት ቀን ጥቃቱ ለምን ተፈፀመ? ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ ብርሀን ላይ ተፈናቃዮችን ሰብስበው ከጎናችሁ ነን አይዟችሁ፤ መከላከያ ሰራዊት ገብቷል ብለው ባወያዩን ምሽት ስለምንድን ነው ጭፍጨፋው የተፈፀመው? ምላሻቸው የአመራሮች እጅ ስላለበትና ተባባሪ ስለሆኑ ነው። የአብዛኞች ከሞት የተረፉት ምላሽ ይኸው ነው።
ሀ)በጉራ ፈርዳ ሹፒ ቀበሌ ጥቅምት 8ለ9 ምሽት ላይ በጥይትና በድምፅ አልባ መሳሪያ ግፍ ከተገደሉት አማራዎች መካከል:_
1)ይርጋ አስራት ከነእህቱ
 2)ሀሊማ ሁሴን
3)መሀመድ ሁሴን በሽር
4)ፋጡማ
5)መሀመድ ኡመር
6) ሰኢድ ሀሰን
 ከእነ ልጆቹ መሀመድ ሰኢድና አይሻ ሰኢድ
6)ሁሴን ይማም
7)መሀመድ ሁሴን
8)ሰይድ ሀሰን
9)ተገኝ ፈረደ
10)መንግስቱ
11 ) አይሻ ሰኢድ
12 )መሀመድ ሼህ ኡመር
13)ባለቤታቸው ሀሊማ ሁሴን
ለ)በጉራ ፈርዳ ወረዳ
አሮጌ ብርሀን ቀበሌ ጥቅምት 11ለ12 ምሽት ላይ በጥይትና በድምፅ አልባ መሳሪያ
ከተገደሉት አማራዎች መካከል:_
1)እንድሪስ ሽፈራው
2)እንድሪስ አሊ
3)ከድር እንድሪስ
4)አሰፋ ገሰሰ
5)ወርቅዬ በላይ
6)መልካሙ
7)ሼህ አደም መሀመድ (ማየት የተሳናቸው)
እስከ ባለቤታቸው
 የንፁሀን ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር!
       መፅናናትን እንመኛለን።
Filed in: Amharic