>

የአማራው ጠላቶች ስማቸው እንጂ ግብራቸው ያልተለወጠው አዴፓዎች ናቸው...!!! (መርእድ እስጢፋኖስ)

የአማራው ጠላቶች ስማቸው እንጂ ግብራቸው ያልተለወጠው አዴፓዎች ናቸው…!!!

መርእድ እስጢፋኖስ

ያልገቡኝ የማይገቡኝ ሊገቡኝ የማይችሉ ነገሮች አሉ ።አብን የተባለው ድርጅት በአማራ ለይ የሚደርሰውን ጭፍጨፋ እንዲቆም ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ።የባህርዳር አማራ መንግስት ሰልፉ እንዳይካሄድ ትእዛዝ ሰጠ ።አስፈራራ።
ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት የነበረባቸው የባህርዳር የአማራ ህዝብ ወኪል ነን የሚሉ የቀድሞ በአዴን በሁኑ ብልጽግና መሆን ነበረበትኮ።ምክንያቱ የአማራ ህዝብ ምርጫውም ባይሆን የወከለው በአዴንን በመሆኑ።አሁንም በድጋሚ መመስከር እንደሚቻለው ስማችሁ እንጂ የተቀየረው ስራችሁ አይደለም ማለት ነው።
የወያኔ አብሪ ጥይት በመሆን 27 አመት ስታሳርዱት ስታስቀጠቅጡት ኖራችሁ።ላለፉት 3 አመታት አለምን ያስደነገጠ ግፍ ሲሰራ ከዲርጊቱ ፈጻሚዎች የኢትዮጵያ አልሸባብ ቄሮ ጋር ተባበራችሁ ።ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎችሁ በራሳቸው ተነሳሽነት የአማራው ድምጽ እንሁን ያሉ ወጣቶችን ከሰላማዊ ሰልፍ አገዳችሁ።የባህርዳር ባለስልጣናት የምትሰሩት ግፍ ማለቂው የት ይሆን? ?
ሌላ ቢቀር ከዘመነ “አድጊ “ወደ ዘመነ” ሀሬ” ስትሽጋገሩ የባህሪ ለውጥ ታመጣላችሁ ብለን ነበር ።በቃ እድሜ እንጂ እውቀት አትጨምሩም ማለት ነው?
የአማራ ክልላዊ መንስት በሰጠው መግለጫ ሰልፉን የተቃወመው በሶውስት ዋና ዋና ምክንያት ነው።
[ ] አንደኛ 15 ሚሊዮን የሚደርሰው በሌላ ክልል ላይ የሚኖረው አማራ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስበት
[ ] ሰልፉን አጋጣሚ ተተቅመው የሚያተራምሱን ሀይሎች እንቅስቃሴ እንዳለ ስለተረዳን
[ ] የአባይ ጉዳይ አለበት።አባይን አደጋላይ ለመጣል
እስኪ በግርድፉ እንመልከተው።15 ሚልዮን የሚደርስ አማራ ጉዳት እንዳይደራበት? እዴት አይነት ቀልድ ነው ? በግፍ በየቦታው እንደንስሣ ከመገደል በላይ ምን አይነት ጉዳት አለ ? በጎጃም ባለስልጣናት አማራው በቀስትና በገጀራ እንዲሁም የቄሮ ኢላማ መለማመጃ መሆኑ የከፋ አይደለም ማለት ነው? የአሟሟት ትርጉሙ ከአብይ ማዶ ተቀየረ እንዴ?hello
ሁለተኛ “የሚያትራምሱን ” ሀይሎች ነው።እነዚ የሚያተራምሱትን ሀይሎች የአማራ ኢሊቶች ቆዳቸው ላይ” ተነቅሰዋቸዋል አተራማሾቹን”?።27 አመት አትራማሾች ሲሉ ኖሩ።አሁንም ያው ነው።የሚገርመው ደሞ ያውቋቸዋል።ምክንያቱም እናቃቸዋለን ስለሚሉ። ለዚ ነው “ህጋዊ ወንጀለኞች ” ናችሁ የምንለው።ወንጀለኞችን እያወቃችሁ እየደበቃችኋልና …ሽፋን እየሰጣችሁና።በሌላ መልኩ መብቴ በህግ ይከበርልኝ ሰላማዊ ሰልፍ ልውጣ ያለን ትገላላችሁ ታስራላችሁ ትሰውራላችሁ።hello
የአማራ አመራሮች ጸረ አማራ መሆናችሁን የምታቆሙት መቼ ነው?
ሶዎስተኛው የአባይ ጉዳይ አለበት ነው።ቄሮ የሚያደርሰው ጭፍጨፋ ኦነግ የሚያደርሰው ጭፍጨፋ ይቁም ማለት ካአባይ ጉዳይ ጋራ እንዴት እንደሚገናኝ የባህርዳር ጊዮርጊስ ነው የሚያውቀው።
ባህርዳርላይ አውሎ ንፋስ ተነሳ. ..የአባይ ጉዳይ አለበት… ከባድ ያለ ዝናብ ከዘነበ የአባይ ጉዳይ አለበት ….ጽሀይ በስተምስራቅ ትወጣለች የአባይ ጉዳይ አለበት .።የአማራ ኢሊት ሰበብ. ..የወያኔ የውሽት ትርክት እና የኦሮሙማ ቅዥት ነው።የሰለቸን።hello
የባህርዳር “አህዮች” መቼነው ለመርጣችሁ ሕዝብ…ቃለመሀላ ላደረጋችሁለትን ህዝብ የምታገለግሉት፧?
በዘመነ ወያኔ አመታት ፥-በበደኖ በወተር በጅጅጋ ኋላም በባሌ ሮቤ በሞያሌ በቢንሻንግል በአሶሳ በምእራብ ወለጋ አማራ ሲጨፈጨፍ እነ አዲሱ ለገሰና ደመቀ መኮንን መግለጫ ሰጥተው አያውቁም።ማውገዝ ይቅር።ለምን በወያኔ ፊታውራሪነት በውሽት ትርክት የተማረኩ አማራን በጠላትነት የፈረጁ ጸንፈኛ ኦሮሞዎች ናቸው ገዳዮቹ።ወያኔን ላለማስቀየም።
5 ሚልዮን የሚጠጋ የአማራህዝብ በስታስቲክስ ቢሮ ጠፋ ሲባል በላጵስ ይሁን በመቅሰፍት. ..እንዴት ብሎ የጠየቀ የለም።ለምን ወያኔን ላለማስቀየም።የባህርዳር አማራ ፖለቲካ ጌቶቹን “ያለማስቀየም ማንፌስቶ ነው”።
ወያኔ ሄደች ኦሮሙማ መጣ. ሰሜን ሽዋ አጣዬ ማጀቴናካራቆሬ ጭፍጨፋ ተካሄደ በውቅቱ አድሱ ተሿሚ ዶ/ር አምባቸው በሄዱበት አይቅናቸውና በእልቂቱ ማዘናቸውን በቴሌቪዥን ገልጾ መጽናናትን ተመኘ።”ወንጀልኞችን ለፍርድ እናቀርባለን”ለአፉንኳ እንደመንግስት አላላም።በአራተኛው ቀን ግን አምቦላይ ጠጁን ይጥጣ ነበር።ይሄ ነው የአማራ አመራር።
ቀጥሎ ቀጥሎ ባለፍት ሁለት አመታት በ 13 የተለያዩ ጊዝያቶች 34 ቦታዎች አዲስ አበባን ጨምሮ 3000 የሚጠጋ አማራን ሲጨፈጨፍ ተቃውሞ ይቅር መግለጫ እንኳ አላወጣም።አማራ የወከላቸው አመራሮች አውግዘው አያውቁም ለምን? አሁንም በአብዛኛው ገዳዮቹ ጸንፈኛ ኦሮሞዎች እና ኦነጎች ናቸው።ያውቋቸዋል ግን በዝምታ ያልፋሉ።ኦሮሙማን ላለማስቀየም ።በምራብ ወልጋ ለትምርት የውጡ የይንቨርስቲ ተማሪውች ታፈኑ ደብዛቸው ጠፋ ።የአማራ አመራር ዝም።ይህ ነገር በአማራ ክልል ላይ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ቢፈጸም አብይናሽመልስ አብዲሳን ለማስደስት ስንት አማራ በነ ደመቀ መኮንን በተገደለ በታሰረ ነበር….hello
2 ሚልዮን የምጠጋ ኦሮሞ በአማራ ክልል ከጅሊ ጥሙጋ እና ጨፋደዋ መብቱ ተከብሮለት በልዩ ዞን ተደራጅቶ ይኖራል።በአማራ ክልል ምከርቤትም የራሱ ውክልና አለው።15 ሚሊዮን ይሚጠጋ አማራ በተመሳሳይ መለኩ በኦሮምያ ውክልና ይኑረው የመደራጀት መብት ይኑረው ብላችሁ ጠይቃችሁ ታቃላችሁን? ሲኖርም አኗኗሩን ሲሞትም አሟሟቱን ሳታውቁለት ሰላማዊ ሰልፍ አድርጌ መብቴን ልለምን ባለ የ30 አመት ባዳንዳነት ልምምዳችሁ ከኦሮሙማ ገዥመደብ ጋር ተሰልፋችሁ ጭፍጨፋን ታበረታታላችሁ? ?
መቼ ነው አማራ እራሱ በመረጠው ልጆቹ ክብር የሚገኘው? መቼ አማራ አመራር ከንደ ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ከመሳሰሉ የሞራልናየእውነት ድሀዎች የሚላቀቀው። መቼነው የአማራ በአዴን ብልጽግና ከኦሮሞ ከሚሰፈርልት ልክ ወጥቶ ለራሱ ህዝብ የሚቆመው?
እስከመቼ ነው የአማራ ህዝብ በራሱ ልጆች ጨለማ ታስሮ የሚኖረው?
የአዲስ አበባ ህዝብ በአካባቢው የኦሮምያ መንግስት ሲወረር እኔም የክልሌ ተውላጆች አሉና መብታቸው ይከበር ብሎ የሚቆመው መቼነው?።ለኦሮሙማ የሰራ ህግ ለአማራው አይሰራም ይሆን፧?
መቼነው በአዴን/ብልጽግና ከስም እድገት ወጥቶ የአእምሮ እድገት የሚያሳየው?
አዎ እንደ ሽመልስ አብዲሳ ከሆነ “ሀሬ”ናችሁ።አህያ ማርም ጫኗት መርዝ የተሽከመችውን ይዛ ተፈለገው ቦታ ታደርሳለች።ልክ ነው።የአማራ ኢሊቶች የተጫናችሁትን አመላልሱ።ከጭነቱ መልስ ደግሞ ጌቶቻችሁን” ካባ” አልብሱ።የምትሽልሙት ካባ ያልቃል እንጂ እኛ እንደምኞታችሁ አናልቅም።

Filed in: Amharic