>

“የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ” ዎች ላይ ተላልፎ የነበረው እግድ ተነሣ...!!! (ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው)

“የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ” ዎች ላይ ተላልፎ የነበረው እግድ ተነሣ…!!!

ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው

       የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፦ “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ” በሚል ስያሜ ከቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውጭ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች ወደ መዋቅሩ ለመመለስ በመስማማታቸው አስተላልፎባቸው የነበረውን እግድ በዛሬው ዕለት አንሥቶ ላቸዋል።በመሆኑም ወደ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ተመልሰው ያገለግላሉ።በወቅቱ ሁላች ንም የተቃወምነው፦ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውጭ መንቀሳቀሳቸውን ነበር።ቤተ ክርስቲ ያንም እንደ እናትነቷ ነገሮችን ሁሉ በትዕግሥት ይዛ ልጆቿን ወደ እቅፏ በመመለሷ ልትመ ሰገን ይገባል።ለእነርሱም ክብራቸው ወደ እናት ቤተክርስቲያን መመለሳቸው እንጂ ደጅ ደጁን በዘር ፖለቲከኞች እና በሃይማኖት በማይመስሏቸው ሰዎች መታጀብ አልነበረም።
    በእውነቱ የግል ሥራቸውን በድለው፥ውድ ጊዜአቸውንም መሥዋዕት በማድረግ ይህ እንዲመጣ የደከሙትን የኮሚቴ አባላት ሁሉ ማመስገን ይገባል።ጥንቱንም ቢሆን ምእመ ናን በሚሰሙት ቋንቋ መማር አለባቸው በሚለው ጉዳይ የአሳብም የተግባርም የዓላማም ልዩነት ሳይኖር የተፈጠረው ነገር መፈጠሩ የልብ ሐዘን ነበር።የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ይኽንን ክፍተት ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያንን ይበልጥ ለማዳከም ምን ያህል እጃቸውን አስረዝመው እንደ ነበረ በገሃድ አይተናል።እኛ ውሉደ ጥምቀት የሆንን ክርስቲያኖች መቼም ይሁን መች ዘራችን ክርስቶስ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።ከሥጋ ዝምድና የሚበ ልጥብንም መንፈሳዊው ዝምድና ነው።ምክንያቱም በክርስቶስ አንድ አካል ነንና።ሃይማኖ ታችንም፦ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ ነው።የሃይማኖታችንም ጸሎት፦”ወነአምን በአሐቲ ቅድ ስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” የሚል ነው።
      አንዳንዶች “እነዚህ ሰዎች መመለሳቸው ከልብ ነው ወይ?” የሚል ጥያቄ ያነሣሉ።ይኸ ውም ከስጋት ሊሆን ይችላል፥ቢሆንም ስጋቱን ትቶ ከልብ መሆኑን እና አለመሆኑን ልብን እና ኵላሊትን ለሚመረምረው አምላክ አሳልፎ መስጠት ይገባል።በእውነቱ በራሱ ፈቃደ ኝነት የተቋቋመው ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ብዙ ደክሞበታል።ተስማምተው የተፈራረሙበት ቃለ ጉባኤ ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ ቀርቧል።የቃለ ጉባኤው መቅረብም የተስማሙበትን ነጥብ በግምት ከመናገር ይጠብቀናል።ሲኖዶሱ የመጨረሻውን ውሳኔ የወሰነው፦በዚህ ቃለ ጉባኤ ላይ ተመሥርቶ ነው፥የኮሚቴው አባላትም ቀርበው የቃል ማብራሪያ ሰጥተው በታል።ሲኖዶስ ያሰረውን የሚፈታው ሲኖዶስ ብቻ ነውና።
        የኮሚቴው አባላት የሆናችሁ፦
፩ኛ፦ላዕከ ሰላም ባያብል ሙላቴ፤
፪ኛ፦መጋቤ ጥበብ ወርቁ አየለ፤
፫ኛ፦ዶክተር ብርሃነ መስቀል ጠና፤
፬ኛ፦አቶ መስፍን አበበ፤
፭ኛ፦አቶ ወርቅነህ ደሳለኝ፤ እናመሰግናለን፥ችግሮችን ከማባባስ ይልቅ ለችግሮች መፍትሔ መፈለግ ልባምነት ነውና።
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የሚባል ድርጅት ሞቶ ተቀበረ…!!!
አባይ ነህ ካሴ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ ለሚመለሱ ሰፊ የምሕረት፤ በኑፋቄ ለሚያምታቱ ጠባብ አንቀጽ (በር) ያላት ናት። ከወርኀ ነሐሴ ፳፻፲፪ ዓ.ም. ጀምሮ በቀና መንፈስ ሲካሔድ የነበረው ውይይት በቤተ ክርስቲያን ይቅር ባይነት በቅሬታ ተለይተው በነበሩት ወንድሞች የመመለስ አዝማሚያ እልባት አግኝቷል።
ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ኾኗል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷልም። ደስም ይላቸው ጀመር። ሉቃ ፲፭ ፡ ፳፬።
ለመሔድ ከመጨከን ለመመለስ መጨከን ዋጋ አለው። መሔድ ሞት መመለስ ሕይወት ነውና። አሁንም አምርረው በዚያው ለመቅረት የሚግደረደሩ እንዳሉ ቢታወቅም በተመለሱት ደስ ይለናል። በድርድር ተመለስን ብሎ መኮፈስ ከተነሳሒ አይጠበቅም። አንበረከክናቸው ብሎ መፎከርም ከይቅር ባይ አይጠበቅም።
ፈርቅ ይዞ ይቅር ባይነት እንደሌለ ሁሉ ፈርቅ ይዞ መመለስም የለም። አዲስ ሰውነት ያስፈልጋል። ባልዳነ ቁስል መምጣት እና ማምጣት ብዙ ጓዝ አለው። ተነሳሒ ልጅ ልባል አይገባኝም ሲል ይቅር ባይ ደግሞ ልጄ ትላለች።
ወደ ዝርዝር መግባት ከሰይጣኑ ያደርሳል። ድሮም ችግሩ ቋንቋ አልነበረም። ትምህርተ ክርስትናም ኾነ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በሚጠበቀው የቋንቋ ክሂል እና ዝግጅት እንዳልነበረ አልተካደምና።
አሁን ለአንድ ቋንቋ አገልግሎት ብቻ ሳይኾን ለብዙ መኾን ይገባል። ይህንን አምናችሁ ስለመጣችሁ ደስ ይለናል። አንተ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለዘለዓለሙ አይመልስህ ብለናል።
Filed in: Amharic