>
5:31 pm - Saturday November 13, 6782

የባለጋራን ባህሪ ጠንቅቆ ማወቅ የድልን ግማሽ መንገድ መዝለቅ ይህል  ነው...!!! (መስከረም አበራ)

የባለጋራን ባህሪ ጠንቅቆ ማወቅ የድልን ግማሽ መንገድ መዝለቅ ይህል  ነው…!!!

መስከረም አበራ

 

* …እነዚህ ሰዎች የልባቸውን ከሰሩ በኋላ  እንደ አጋንንት የሚጠሉትን እስክንድርን እንኳን “በቤተመንግስት መግለጫስጥ ብለን ነው አደራሽ የከለከልንህ” ያሉ ብልጥ ከእኛ በላይ ላሳር ባዮች ናቸው
በሞት ጥላ ስር ላለው፣ገና ያልተገለፀ ጭምር የሞት አደጋ ላንዣበበት የአማራ ህዝብ በህይወት የመኖር መብት አብኖች ለሚያደርጉት የመሪነት ሚና አድናቆት አለኝ። ግን ስጋትም አለኝ!
ስጋቴ ይህ እንደ ድመት ተለሳልሶ ገብቶ እንደ እባብ የሚናደፍ የዘረኛ ካድሬዎች አስተዳደር ምን ያህል አሳሳች እንደሆነ ተገንዝበው ይህን የመንግስትን አደገኝነት በሚመጥን መንገድ መጓዝ ካልቻሉ የሚመጣው ነገር ነው።
 አብኖች በመግለጫቸው መንግስት ለሰራው የአፈና አካሄድ ይቅርታ እንደጠየቃቸውና እርምት እንደሚወስድ ነግሮናል ባዮች ናቸው። ይቅርታው እውነት ከሆነ መቅረብ ያለበት ለእነሱ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነት ለሚሰማው ፣ ዲሞክራሲን  ለሚናፍቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉና በተለይ ለሚታረደው የአማራህዝብ ሁሉ ነው።
 በመሆኑም  አብኖች መንግስት በይፋ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያለዚያ የሚያወራውን ይቅርታም ሆነ እታረማለሁ የሚል ፌዝ ተቀባይነት እንደሌለው  በመግለፅ ፣ይህንም ለህዝባቸው እንደሚገልፁ ማሳሰብ ነበረባቸው።
 መንግስት እታረማለሁ ብሎናል ሲሉ ደግሞ ለመታረሙ መገለጫው የፊታችን እሁድ አብን በአዲስ አበባ  የጠራውን ሰልፍ ከማስተጓጎል በመቆጠቡ መሆኑን ገልፀው ፤ይህ እስካልሆነ ድረስ መንግስት የሚወተውተውን የይቅርታ እና የእታረማለሁ ውትወታ እንደማይቀበሉት ማሳወቅ ይጠበቅባቸው ነበር። ይህን ግን በመግለጫቸው አልገለፁም! የአዲስ አበባውን ሰልፍ በተመለከተ ግልፅ ያደረጉት ነገርም የለም።
 የባለጋራን ባህሪ ጠንቅቆ ማወቅ የድልን ግማሽ መንገድ መዝለቅ ነው። እነዚህ ሰዎች የልባቸውን ከሰሩ በኋላ  እንደ አጋንንት የሚጠሉትን እስክንድርን እንኳን “በቤተመንግስት መግለጫስጥ ብለን ነው አደራሽ የከለከልንህ” ያሉ ብልጥ ከእኛ በላይ ላሳር ባዮች ናቸው። ከነሱ ጋር የሚደረግ በውይይት ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
Filed in: Amharic