ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሃገራዊ ምርጫ የፊታችን ግንቦት ወይም ሰኔ ላይ ለማካሄድ ማቀዱን አስታወቀ…!!!
አ. ሚ.ኔ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሃገራዊ ምርጫ ከኮቪድ 19 ወረረሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ማካሄድ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚዲያ አካላትና የሲቪክ ማህበራትን በማሳተፍ እየመከረ ነው፡፡ቦርዱ ለውይይት ባቀረበው መነሻ ሃሳብም 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫ በግንቦት ወር የመጨረሻ ሁለት ሳምንታት አልያም የሰኔ ወር የመጀመርያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለማካሄድ እቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡የጊዜ ሰሌዳውን በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን እንደሚያካትትም ቦርዱ ገልጿል፡፡
[AMN]