>

አ.ብ.ን - በፓርቲዎችና ባለድርሻ አካላት መካከል ከተጀመረው ሐገራዊ የውይይትና የድርድር መድረክ ላይ አቋርጦ ወጣ!

አ.ብ.ን – በፓርቲዎችና ባለድርሻ አካላት መካከል ከተጀመረው ሐገራዊ የውይይትና የድርድር መድረክ ላይ አቋርጦ ወጣ!
ዘሪሁን ገሰሰ
<< ቀይ መስመራችን ታልፏል! ህዝብን ለመከፋፈል እየተሰራና በመዋቅር የተደገፈ ህዝባዊ ጥቃት እየተፈፀመ ባለበት ለጉባኤ አብረን መቀመጥ አንችልም..! >>  አብን
 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አብን ) – በፓርቲዎችና ባለድርሻ አካላት መካከል ከተጀመረው ሐገራዊ ውይይትና ድርድር ላይ አቋርጦ መውጣቱ ተገለፀ፡፡ የዛሬ አመት ገደማ ተጀምሮ የነበረውና ገዢው ፓርቲን ጨምሮ የኦሮሞና የአማራ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ፦ ሐገራዊ የፖለቲካ ውይይትና ድርድር በቅርቡ በተደረሠ ስምምነት አቅጣጫ ይዞ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ በዚሁም መሠረት ለስምምነቱ ተፈፃሚነትና ቀጣይ ሀገራዊ የፖለቲካ መግባባቶችን የሚፈጥሩ ሌሎች ፓርቲዎችና ምሁራን እንዲሁም ታዋቂ ግለሠቦች የተሳተፉበት ተከታታይ የውይይት መድረኮችን በናዝሬትና በባህርዳር ለማድረግ ታቅዶ እንደነበረም የሚታወስ ነው፡፡
ይሁን እንጂ  የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አብን ) ትናንት ማታ ባወጣው መግለጫ መሠረት – በተፈፀመበት የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰትና በአባላትና ደጋፊዎቹ ላይ በመፈፀም ላይ ባለው የጅምላ እስር መነሻ በማድረግ ከዚህ ድርድር እራሱን ሊያገል እንደሚችል አስታውቆ ነበር፡፡  በዚህም መሠረት በዛሬው እለት በናዝሬት ከተማ ከተጀመረው ሁሉን አቀፍ ሐገራዊ የድርድርና የውይይት መድረክ ረግጦ መውጣቱ ታውቋል፡፡ ከስፍራው በደረሠኝ ተጨባጭ መረጃ መሠረትም አብን << ቀይ መስመራችን ታልፏል! ህዝብን ለመከፋፈል እየተሰራና በመዋቅር የተደገፈ ህዝባዊ ጥቃት እየተፈፀመ ባለበት ለጉባኤ አብረን መቀመጥ አንችልም! >> በማለት መድረኩን አቋርጦ መውጣቱን እንዳስታወቀ ተገልፇል፡፡
እንደምንጮቼ ገለፃ “አብን ለውይይትና ለድርድር ክፍት በር ያለውና ለዚህም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የመሪነት ሚና ወስዶ እየሠራ እንደነበር የሚታወቅ ቢሆንም ፥ በተለይ እንደሀገር ገዢው የብልፅግና ፓርቲ መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ፍጅትና በደል የማስቆም ሀላፊነቱን መወጣት ባለመቻሉ ተጠናክሮ በቀጠለበት ሁኔታና የክልሉ መንግስትም ውስጥ ሆነ ተብሎ ህዝቡን ለመከፋፈልና አንድነቱን ለማሳጣት ፥ ከአፈናና እስር ባሻገር በርካታ  በእቅድ የሚመሩ አሻጥሮች እየሠሩ በመመገኝበት ለድርድር አብረን አንቀመጥም!” ሲል ንቅናቄው አቋም መያዙና መድረኩን ረግጦ መውጣቱ ታውቋል፡፡
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!!!
Filed in: Amharic