የአብይ መንግስት ኦነግና ሕወሓትን
በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ካላደረገ ፍጅቱ መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት እንደሆነ ይታመናል…!!!
አቻምየለህ ታምሩ
* በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አገዛዝ በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ በንጹሐን የአማራ ተወላጆች ላይ የተካሄደውን ፍጅትና የዘር ማጥፋት “በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ባለው ማንነትን መሠረት ባደረገው ጥቃት” መሆኑን አምኖ ጥቃቱ በኦነግ እና በሕወሓት የተፈጸመ የሽብር ተግባር መሆኑን ነግሮናል።
የኦሮሙማው አገዛዝ “ማንነትን መሠረት ያደረገው ጥቃት” ያለውን የሽብር ድርጊት ሕወሓትና ኦነግ እንደፈጸሙት ካመነና አገዛዙ በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ፍጅት በኦነግና ሕወሓት የተፈጸመ የሽብር ጥቃት ሲል የገለጸመው ለፖለቲካ ፍጆቻ ብቻ ብሎ ካልሆነ፤ በአማራ ተወላጆች ላይ ሽብር የሚፈጸሙት ኦነግና ሕወሓት በብርቱካን ሜዴቅሳ የሚመራው ምርጫ ቦርድ በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ የሰጣቸውን የፖለቲካ ፓርቲነት ፍቃድ ሰርዞ “ፓርላማው” በአሸባሪነት መፈረጅ አለበት።
የኦሮሙማው አገዛዙ ራሱ ያመነው ማንነትን መሠረት ያደረገው የሽብር ጥቃት ሕገ መንግሥት ተብዮው በጠላትነት በፈረጃቸው የአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመ ስለሆነ የሕገ መንግሥት ተብዮው ፈረሰኞች የሆኑትን ኦነግና ሕወሓትን በአሸባሪነት ሊያስፈርጅ የሚችል ካላለ በስተቀር ሽብር ፈጻሚዎቹ ኦነግና ሕወሓት ባስቸኳል አለማቀፍ አሸባሪዎች ሆነው ሊፈረጁ ይገባል።
በአገዛዙ የታመነ ሽብር ፈጻሚዎች የሆኑት ኦነግና ሕወሓት ብርቱካን ሜዴቅሳ የምትመራው ምርጫ ቦርድ “በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ” በሚል የሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲነት ፍቃድ ተሰርዞ “ፓርላማው” አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ሁለቱን ድርጅቶች በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ካልተደረገ ግን እነዚህ ሁለት አሸባሪ ድርጅቶች እስካሁንም ሆነ ወደፊት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጽሙት የሽብር ጥቃት በዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አገዛዝ እውቅናና ፍቃድ የሚፈጸም መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል።