ለቅሶውን ቀንሰን ስራ እንስራ!!!
አራጅ አሳራጆችን በአለምአቀፍ ፍ/ቤት እናቅርባቸው‼️
ታማኝ በየነ
የተከበሩ ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ
ወደ ብልጽግና የሚደረገዉ ጉዞ በአማራ ደም በመረማመድ ነው እንዴ የሚሳካው? በእውነት በአማራው ላይ የሚደርሰው በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አሳስቦወት ከሆነ እንደ መንግስት ቆፍጠን ያለ እርምጃ ወስደው ያሳዩን እንጅ ለቅሶማ ማንም ይደርሳል። ለመሆኑ ዛሬ ያወጡት መግለጫ በአማርኛ ብቻ ለምን ሆነ?ሁልጊዜም መልክትዎን የሚያስተላለፉት በሶስት ቋንቋ ነበር።ድርጊቱ የተፈፀመዉ ወለጋ፣ ድርጊቱን የፈፀመዉ ደግሞ ኦነግ፣ ሆኖ እያለ መልክተዎት ግን በአማርኛ ብቻ ለምን አደረጉት አፋን ኦሮሞንና እንግሊዘኛዉን ለምን ዘለሉት?
ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ
በአርሲ ባሌ ሀረር ሻሸመኔ መተከል ቤንሻንጉል አሁን ደግሞ ወለጋ አማራዎች ተመርጠው ተጨፍጭፈዋል የክልሉ ኘሬዝዳንት እርስዎ ሰለኾኑ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት እንሰብራቸዋለን ባሉት መሰረት የሚቀጥለው የጭፍጨፋ ቦታ የት እንደሆነ ያውቃሉና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በህግ እንደሚጠየቁ አይጠራጠሩ::
ይድረሰ ለመላው ኢትዪጵያዊያን
ይህ በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ አርባ አመት በላይ ሲሰበክ ኖሮ በ1983 በህግ ፀድቆ ዛሬ ደግሞ በመንግስት መዋቅር ጭምር ድጋፍ እየተደረገለት የሚካሄድ ዘመቻ ነው::
ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከፈለግን ይሄን በአንድ ማህረሰብ ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ጭፍጨፋን የሚያበረታታ ህገመንግስት ለመቀየር የአጭርና የረዥም ጊዜ እቅድ አዉጥተን መንቀሳቀስ እንጀምር::
በውጭ ሀገር የምንኖረው ኢትዮጵያዊያን ጊዜ ሳንወስድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በዚህ እኩይ ተግባር እጃቸው ያለበትን የመንግስት ባለስልጣናት በዓለማቀፍ ፍርድ ቤት የሚከሰሱበትን መንገድ ማመቻቸት ይኖርብናል