>

‘’ ነፍጡና ነፍጣኛው ተለየ !!!  (ከመንግሥቱ ደሳለኝ)

 

‘’ ነፍጡና ነፍጣኛው ተለየ !!!    

 

  ከመንግሥቱ ደሳለኝ


የትግራይ ክልል የደረጀ ወታደራዊ ሃይል እንዳለው ለመገመት የወሬ ነጠብጣቦችን በመግጠም ሃሳብ መጨመር ይቻላል፡-

ነጥብ 1፡- የደብረዘይት አየር ሃይል ሳስቷል፣አቅም እንዲያጣ ተደርጓል ይባል ነበር ከለውጡ በፊት፣

ነጥብ 2፡- ጀነራል ሳዕረ መኮንን የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ በነበሩበት ጊዜ ትግራይ የሚገኘውን ወታደራዊ ሃይል በሚገባ አደራጅተውታል፣

ነጥብ 3፡- ለሰሜን ዕዝ የተመደቡት ምክትል አዛዥ ከመቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤየር ፖርት እንዲመለሱ ተደርጓል፤

ነጥብ 4፡- ‘’አገር መዳን ካለበት ይህ ሰራዊት መነካት የለበትም፣የእዚህ ጦር ባህርይና መገለጫ ማንነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ መደረግ አለበት ‘’- አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ይህ ሃሳብ በእርግጥ ማብራሪያ ሳያስፈልገው አይቀርም፣በእውነት ያንን ጦር ፌዴራሉ እያዘዘው ነው ወይ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡

ነጥብ 5፡- የትግራይ ክልል እንደሰሜን ኮሪያ ‘’ closed-door-policy ‘’ እየተገበረ ነው፣በእዚህም ምክንያት ፌዴራል መንግሥቱ ስለ ትግራይ ክልል ያለው መረጃ /Assessment/ ጎዶሎነት አለበት – በተለይ በወታደራዊ መስክ፣

ነጥብ 5፡- የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ዕዙን አስምጦታል፤ቢያነገራግር እንኳን በትንሽ COST ያስታግሱታል፤

ነጥብ 6፡- ጦርነት ለማስቀረት ስንል ሃይል በማጠንከር ተዘጋጅተናል – ደ/ር ደብረፅዮን፣good fence makes good neighbor ወይም good offence is good defense መሆኑ ነው በወታደራዊ ቋንቋ፡፡      

 

የትግራይ ክልል ግዙፍ ወታደራዊ ሃይልን ለመመስረት ታሳቢ የሚደረጉ ገፊ ምክንያቶች፡-

 

1ኛ. ክልሉን ወደ ሃገረ መንግሥትነት ከፍ የሚያደርግ ራዕይ ቀድሞም የነበረው በመሆኑ ያን ተግባራዊ ለማድረግ ወታደራዊ አቅም ወሳኝ ስለሆነ፣

2ኛ. በወሰን ይገባኛል ምክንያት በተለይ ከአማራ ክልል ሊነሱ የሚችሉ ቁርቁሶችን ለመመከት፣

3ኛ. ከኤርትራ መንግስት ጋር በነበረ ልዩነት እና ግጭት በቅርበታቸው ምክንያት ሊከሰት የሚችልን ማንኛውንም ጥቃት ለመቋቋም እንዲቻል፣  

4ኛ. የፕሩዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂን ከኤርትራ መንግሥት መሪነት በማውረድ ለሕወሓት የገበረ Puppet መንግሥት መመስረት፣

5ኛ. ‘’Might is right’’ የሚለውን ዶክትሪን በመቸከል የኤርትራን ሲነጋፖራዊ ህልም ሲባል የነበረውን ነጥቆ መተግበር፣

6ኛ. የኢትዮጵያ መንግሥት መሪነት ምንጊዜም ከህወሃት እጅ እንዳይወጣ አሊያም ለክልሉ የሚወግን አመራር የማስቀመጥን አቅም ለመፍጠር፣

 

ሌሎች ምን እየሰሩ ነው፡- ምንም!!!

 

በህውሃት framework  ፖለቲካን እየሰሩ በmasterፒሱ እየተቀኙ የህዝብ ነፃ አውጪ መምሰል ብዙ ይቀረዋል – በተለይ ለአማራው ኤሊት – ለፖለቲካ መሪውም፣ለአክትቪስቱም፡፡ Show your momentum and inherent political leverage ተፅዕኖ መፍጠር  የሚቻለው አቅምን በማሳባሰብ፣ በማጎልበት ነው፡፡የአማራ ኤሊት መጀመሪያ ትንሹን ስራ ይስራ – ህብረት መፍጠር፤ እዚያና እዚህ ተበታትኖ በአርባ ትንንሽ የሃገር ህልውናን እና የህዝብ ደህንነትን መታደግ አይቻልም፡፡

መከፋፈል ሃይል ማባከን ነው፤ገፅታ አይገነባም፤ግርማ-ሞገስ የለውም፤ከጅብ አያስጥልም፤ከኮንፈረንስና ዎርክሾፕ ማድመቂያ የዘለለ ስራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ከውስጥ ተገዳዳሪ፣ከሩቅ አጥቂ ሀገርና ህዝብን መታደግ ይሳነዋል፡፡ ’’የመቶ አመት ስራ ሰጥተናቸዋል’’  ቋሚ ምስክርና መገለጫም እኮ ይህው ነው፡፡ ትልቁን ሰላማዊ ስብስብ አሁንንው ጀምር – better late than never፣ ከሌሎች ተመሳሳይ ሃይሎች ጋር በጋራ የሚሰራበትን ሁኔታ አመቻች፡፡የጎንዮሽ ለበጣ፣ትችት፣አቃቂር፣ሃሜት፣ቁርቁስ አቁም፡፡ሃሳብን ወደ ቁስ አካላዊ ሃይል የመቀየሪያው ጊዜ አሁን ነው፡፡የኦሮማራ ጥምረት ወሳኝ ግባት ነው- ሳትሰለች ስራበት፤ከሰላማዊ ትግል ውጪ ሌላው አያማልህ – ግን በህብረት አበክረህ ስራ!!!፡፡ ጥላቻን አሰወግድ፤ ጥላቻ የጠይው ዕዳ ነው – አትሞክረው፡፡Hate destructs only the hater: Marthin Luther King::   

‘’አያጅቦ ሊበላህ ነው’’ ወይም ፈረንጆቹ የሚሉት ‘’Boogy-man-creation’’ የማታገያ ሰበብ ነው – ሁሌም ፖለቲካ ውስጥ አለ፤ያለ እርሱ ትግል ይመክናል፤ተከታይ ይጠፋል፤ ማን ይማገዳል? George W. Bush የጅምላ ጨራሽ መሳሪያን ‘’Weapons of Mass destruction’’ ሰበብን ለኢራቅ ወረራ እንደተጠቀሙበት ማለት ነው፡፡  

ዛሬ የአማራ ነፍጠኛ ካለ አቶ በረከት ስምዖን ምንም አልሰሩም ማለት ነው፡፡ ህወሃት የነፍጠኛ አከርካሪ አልሰበረም ማለት ነው – ለ27 አመታት፡፡ፐርፎርማንሱ ዝቅተኛ ነው ማለት ነው፡፡በፖለቲካው ህግ ግን ሰበብ ግድ በመሆኑ ዛሬም ‘’የአማራ ነፍጠኛ ‘’ ለቀጣዩ መቶ አመት ችግር እንደሚሆን እና እንደማይጣፋ እነ ተስፋዩ ገብረአብ፣ ህወሃትና ሌሎች ‘’ከአፈርኩ አይመልሰኝ’’ በሚል በንቀት፣በድፍረት ሌላውን ሊግቱት የሚሞክሩት ዕርቃኑን ቀረ፡፡የአማራ ነፍጠኛነት ተረት ሆነ፤ የህወሃት ነፍጠኝነት ሞልቶ ፈሰሰ፡፡

 

ኮሚኒስት ‘’ Abolish ’’ ደምስስ፣አጥፋ ማለት ይወዳል፡፡ቤት፣መሬት፣ትራንስፖርት፣ውርስንም መከልከል እና መውረስ ነው – ክፉ ልማድ፡፡ ይህን ለመመስከር የኮሚኒስት ማኒፌስቶን ትንሽ ገፆች ማንበብ ነው፡፡ጠንቅቅ ነው – ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም – እንደ ኮረና ሁለተኛው የኮሚኒስት ዌቭ ወይም ፌዝ እንዳይፈጠር፡፡ ‘’አይሆንምን ትትሽይ ይሆናልን ያዥው’’፡፡

 

ቀጣይ ምን ሊከሰት ይችላል? ግምት፡-

 

  1. አለመግባባቱ ከከረረ ህወሃት ቁርቁሱን ወደ ሌሎች በርካታ ክልሎች stretch ያደራጋል፡፡ይህም ሰራዊቱ እንዲሳሳ እና እንዲበተን ማድረግ ነው፤
  2. ማዕካዊ መንግሥትን መክፈል እና መረጋጋትን መንሳት፣
  3. ከሩቅ ሃይሎች ማበር፣ 
  4. የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ  ማድረግ፣
  5. ፋታ መንሳት፣ አሻጥር /Sabotages/፣
  6. አማራና ኦሮሞን መከፋፈል፣ ወዘተ…… ይቀጥላል
Filed in: Amharic