>

ወደ ትግራይ ክልል የሚደረግ ማንኛውም በረራ እንዳማይኖር ፤ የሰሜን እዝም ከጎኑ እንደቆመ የክልሉ መንግሥት ገለጸ!!!

ወደ ትግራይ ክልል የሚደረግ ማንኛውም በረራ እንዳማይኖር ፤ የሰሜን እዝም ከጎኑ እንደቆመ የክልሉ መንግሥት ገለጸ!!!


 

የትግራይ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላትና አዛዦች ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን ለመሰለፍ መወሰናቸውን አሳውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ክልሉን በሚያስተዳድረው ሕወሃት ላይ ጦርነት መከፈቱን ማስታወቃቸውን ተከትሎ ክልሉ ባወጣው መግለጫ::
የፌደራል መንግሥትን በሕገወጥ መንገድ የተቆጣጠረው አሃዳዊና ግላዊ መንግሥት የትግራይን ክል ሕዝብ ለማንበርከክ ከውጪ ኃይሎች ጋር በመሻረክ የአገርን ሉዓላዊነት አሳልፎ በመስጠት ክህደትና በደል እየፈፀመ ነው ሲል በመግለጫው ላይ አትቷል።
የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገመንግሥቱን አክብሮ ምርጫ በማካሄዱ ተከታታይ “በደሎች” እየደረሱበት መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በመላው አገሪቱ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለመውረር በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን መታዘዙን መግለጫው አክሎ ገልጿል።
የትግራይ ክልል መንግሥት የተፈጠሩት የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም የተሰጠው “እንደ ሕዝብ ቅጣት ነው” በማለትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊትና አባላት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን በመቆም አብረው መታገል መጀመራቸውን ገልጿል።
መግለጫው ከዛሬዋ እለት ጀምሮ ጥቅትም 25/ 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ውስጥና ድንበር አካባቢ ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተከለከለ እንደሆነ ያትታል።
በተጨማሪም ወደ ትግራይ ክልል የሚደረግ ማንኛውም በረራ እንዳማይኖር የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል።
ይህንን ውሳኔ በመጣስ በሕዝብ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚወሰድ እርምጃ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።
ለሌሎች የሰራዊት አባላት እና አዛዦችም ከሰሜን እዝ ሰራዊትና አዛዦች ጎን በመቆም ታሪካዊ ኃላፊነታቸውነ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የትራንስፖርት አገልግሎትም እንደማይኖር በተጨማሪ ተገልጿል።
በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው የመከላከያ ሠራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ “ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል” በማለት ገልፀዋል።
ክራይስስ ግሩፕ፤ የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እየተፈጠረ ያለው የፖለቲካ ችግር በሃገራዊ ውይይት እንዲፈታ መጠየቃቸው ይታወሳል።
Filed in: Amharic