>
5:26 pm - Wednesday September 15, 3165

ህወሃት ዛሬ ላይ እያደረሰች ላለችው ውድመት ዋና ተጠያቂው አብይ አህመድ ናቸው...!!!  (ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ

ህወሃት ዛሬ ላይ እያደረሰች ላለችው ውድመት ዋና ተጠያቂው አብይ አህመድ ናቸው…!!! 
ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ

* …  አማራን በሄደበት ሲያስጨፈጭፈው ፣ እንደ በግ ሲያሳርደው፣ የቀስት መለማመጃ ሲያስደርገው ..   የከረመው ህገ መንግስት ይሻሻል? ወይስ አብይ በትግሪኛ ቋንቋ “የትግራይ ህዝብ በደም የፃፈውን ህገ መንግስት ለማስጠበቅ” እንዳሉት “ለማስጠበቅ” ይሆናል?  መገደልና መፈናቀል ይቆማል? አጠቃላይ የኢትዮጵያ ችግር በጦርነት ይፈታል ወይ?  ምላሽ ያላገኘ ጥያቄ…?
ያረጀውን እና የተዳከመውን ህወሃት እንደገና የኢትዮጵያ ዋና ችግር እንዲሆን ያደረገጉት  እሳቸው ናቸው። የኢትዮጵያ የችግር ምንጭ የሆኑትን ኢሳያስን ቤተኛ ማድረጋቸውና ህወሃቶች አውዳሚ ሁሳኔዎችን እና እርምጃዎችን ሲወስዱ አንዴ በቀልድ ሌላ ጊዜ በዛቻ ያደረጓቸው ንግግሮች ህወሃት ዛሬ ላይ ለወሰደችው እርምጃ ዋና ምክንያቶች ናቸው።  “የቀን ጅብ፣ የትግራይ እናቶች እንዳታለቅሱ፣ ባዮሎጅም መልስ አለው፣  ሰንኮፉን እንነቅላለን” እና  የመሳሰሉት ሃላፊነት የጎደላቸው የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግሮች ችግሩ እንዲባባስ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርገዋል።
በየትኛውም ሁኔታ ጦርነት አይመረጥም ግን ተጀምሯል። አሁንም የህወሃት ጉዳይ የፌደራል መንግስቱ ጉዳይ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው። ነገር ግን በዚህ ጦርነት  ከፊት ሆኖ ዋጋ እየከፈለ ያለው አማራው ነው። እንደምንሰማው ከሆነ በሰሜን እዝ ላይ በማንነቱ እየተመረጠ የተረሸነውም  አማራ ነው።  ምንም እንኳን ወደ ጦርነቱ የገባው ያለ ስሌት እንደሆነ ቢገባኝም እና መካፈል እንደሌለበት ባምንም ከተገባበት ጦርነት ተሸንፎ እንደማይወጣ እርግጠኛ ነኝ።
የእኔ እምነት የሃገራችንም ሆነ የአማራ ጥያቄዎች ከሃይል አማራጭ ውጭ በውይይትና በድርድር ይመለሳሉ የሚል ነው። አሁን ወደ ጦርነት ተገብቷል። ከዛስ?
የኔ ስጋት ይኸ ከፊት ሆኖ ዋጋ እየከፈለ ያለው አማራ ከጦርነቱ በኋላ የሚያተርፈው ምንድን ነው? በጦር ሜዳ ያገኘው ድል በፖለቲካ ይደገማል? አማራ ለዚህ የፖለቲካ “ድል” ለሚደረገው ድርድር አቅምና ፍላጎት ያለው የፖለቲካ ሃይል አለው? የእርስት ይገባኛል ጥያቄው ይመለስለታል? ለአመታት ሲያስጨፈጭፈው የከረመው ህገ መንግስት ይሻሻል ወይስ አብይ በትግሪኛ ቋንቋ “የትግራይ ህዝብ በደም የፃፈውን ህገ መንግስት ለማስጠበቅ” እንዳሉት “ለማስጠበቅ” ይሆናል?  መገደልና መፈናቀል ይቆማል? አጠቃላይ የኢትዮጵያ ችግር በጦርነት ይፈታል ወይ? የሚለው ነው።
Filed in: Amharic