>

ማይካድራ - ዳግማዊት ጉሊሶ (ይነጋል በላቸው)

ማይካድራ – ዳግማዊት ጉሊሶ

ይነጋል በላቸው


 

ከዘረኝነት ችግሮች ልጀምር፡፡ ዘረኝነት ጥምባት መሆኑን፣ ህክምናውም ሞት ብቻ መሆኑን ብዙዎቻችን ትንናገር ሰንብተናል፡፡  አለመታመን አንዱና ዋናው የዘረኝነት ችግር ነው፡፡ በዘረኝነት የተዋቀረ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ የሚመድባቸው ባለሥልጣናትና የሚቀጥራቸው የመንግሥት ሠራተኞች ሁሉም ባይሆኑ በአብዛኛው ከራሱ ነገድ በብቃት ሳይሆን በታማኝነትና በቀረቤታ ይመለምላል፡፡ ወያኔ እንዲህ ነበር የሚያደርገው፡፡ አሁንም ኦህዲድ እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው – “ኮፒፔስት” ይሉታል የኮምፒውተር ሊቃውንት፡፡ አንድን ደግም ሆነ መጥፎ ነገር እንዳለ ገልብጦ መድገም እንደማለት ነው፡፡ በጥሩ ጎኑ ከሆነ ጥሩ ነው፡፡ የመጥፎው ነው መጥፎ፡፡

አለመታመን ገዝፎ ይታያል – በዘረኛ መንግሥት መዋቅር፡፡ ወያኔ የራሱን ሰዎች በሰገሰገባቸው እንደአየር መንገድና ባንክ ወይም ሌሎች የጸጥታ፣ የመከላከያና የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ኦህዲድ በተመሳሳይ ቅኝት የራሱን ሰዎች በመሰግሰግ የአድልዖ ሥራውን በግልጽ ሲያከናውን ይስተዋላል፡፡ ዘረኞች በባሕርያቸው ይሉኝታንና ሀፍረትን አያውቁም፡፡ የመጨረሻ የውድመት ዕጣ ፋንታቸውን ስለማያስተውሉ አስተሳሰባቸው ከአፍ እስካፍንጫቸው ነው – እስከዚያም መድረሱን እግዜር ይወቅ፡፡ አሁን አዲስ አበባንና የተበጣጠሰችዋን መላዋን ኢትዮጵያ የተቆጣጠረው ኦህዲድ አቅሉን ስቶ በኬኛ የፖለቲካ ፈሊጡ ሁሉንም እያግበሰበሰ ነው፡፡ ትግሬዎችንና አማሮችን ከየመሥሪያ ቤቱ በገፍና በግፍ እያባረረ የራሱን ዜጎች እየተካ ነው፡፡ እኔ በግሌ እነዚህ የዕውቀት ጠላቶች በጣም ያሳዝኑኛል፡፡ አለማስተዋላቸው እንጂ ወያኔም ከላይኛው ማማ ቁልቁል ወርዶ የተፈጠፈጠው በዚህ ወልጋዳ አካሄዱ ምክንያት ነው ወይም ነበር፡፡ ዕብሪት ያሳውራል፤ ሥልጣን ያሳብዳል፡፡ ከዕብሪተኛና ከዕብድ ደግሞ ምንም መልካም ነገር አይጠበቅም፡፡ የማይካድራው ጭፍጨፋ የሚያሳየውም ይህንኑ ነው፡፡ አንድ ጤነኛ አካል ያሸነፈውን ጦር ትቶ ንጹሕ ዜጎችን አይገድልም፡፡ “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ሮጠ” የሚለውን ባህላዊ ሥነ ቃል ያስታውሰናል ይህ ዕኩይ ድርጊት፡፡ ሰው ስለመሆናቸው ተጠራጠርኩ፡፡ 

ትግሬ ሲመጣ አማራን ካላመነ፤ ኦሮሞ ሲመጣ አማራንና ትግሬን ካላመነ፣ ሶማሊያ ሲመጣ ሁሉንም ካላመነ … በዚህ ሸፋፋ አካሄድ ገደል እንገባታለን እንጂ ወትም አንደርስም፡፡ ይህን ጠማማ መንገድ ለማስተካከል ከተፈለገ ኢትዮጵያዊነት ብቻውን በቂ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት ማለት ስምህንና የኋላ ዳራህን ጠይቆ ሳይሆን በማመልከቻህና በሥራ ልምድ ወረቀትህ ላይ ብቻ ተመሥርቶ አወዳድሮ ስታሸንፍ ሥራ የሚቀጥርህ ነው፡፡ ዘር ማንዘርህንና ነገድህን እየጠየቀ ካለችሎታህና ልምድህ ቢቀጥርህ አንተንም አልጠቀመህ፤ ሀገርህንም አልጠቀመ፤ ራሱንም ለማይሞት ትዝብትና የኅሊና ጸጸት ዳረገ እንጂ የተጠቀመው ነገር የለም፡፡ የቦሰና ልጅ ወይም የሸጊቱ ልጅ ስለሆንክ ወይ ስላልሆንክ ሳይሆን “ምን ተምረሃል? ምን ታውቃለህ? የሥንት ዓመት የሥራ ልምድ አለህ? …” ብሎ ሥራ የሚቀጥርህ ኢትዮጵያዊ ሲኖር ይህ ሰው የሰውነትን ውኃ ልክ አሟልቷል ማለት ነውና በውጤቱ ሀገር በሁለት እግሯ ቆማ ትሄዳለች፡፡ ስምሽ/ህ በሻዱ ወይም ትንቧለል ወይም ዘበርጋ ወይም ስንሻው አሊያም ሐጎስ ወይ ደቻሳ በመሆኑ ሳይሆን በብቃትህ የሚቀጥር ሰው በየመሥሪያ ቤቱ ሲመደብ ያኔ ኢትዮጵያዊነት አበበ ማለት ነው፡፡ በፈረንጅኛው አገላለጽ “ሜሪቶክራሲ” ቀርቶ ዘረኝነትና በዘረኝነት ላይ የተመሠረተ የኮታ አሠራር ከገነነ አገር ጠፋች፤ የፍትኅና ርትዕ ዐይኖችም ተደነቆሉ፡፡ ይነጋል በላቸው ስልህ እንግዲህ ይህ ዓይነቱ ወርቃማ ዘመን እንደሚመጣ በተለይ ለደናቁርቱ አስታውሳቸው ማለቴ ነው፡፡ እስኪያልፍ ማልፋቱ የተፈጥሮ ህግ ሆኖ ተቸገርን እንጂ ሁሉም ያልፋል፡፡  

ወያኔ “እሽ አትበሉኝ የሹም ዶሮ ነኝ” ብላለች፡፡ ያልጠበቀችው መቅሰፍት እየወረደባት ነው፡፡ እየሆነ ያለውን ማመን አልፈለገችም፡፡ ኬሚካል አሊ ማለትም ጌታቸው ረዳ መሬት ውስጥ የሚገኝ በሚመስል ዋሻ ውስጥ ሆኖ ሲናገር እንዳየሁት አፉ ብቻ ነው እንጂ የሠራ አካሉ ሞቷል፤ መጠጡ ይሁን ቅጠሉ አላውቅም መላ ሰውነቱን አናውዞታል፡፡ ከሰውነት ተራም የወጣ ይመስላል፡፡ አፉ ብቻ አልሞተም፡፡

በዚያኛው ሰሞን በወለጋዋ ጉሊሶ ወረዳ ኦነግ ሸኔዎች አማሮችን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ሕጻን ሽማግሌ ሳይሉ ሰላማዊ ዜጎችን በመትረየስ ጨፈጨፉ፡፡ በኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ሰው ጦር ከያዘ ጋር ይዋጋል እንጂ ሴቶችንና ሕጻናትን እንዲሁም ያልታጠቁ ገበሬዎችን በስብሰባ ስም ጠርቶ እንዲህ በጥይት የሚያጭድ በዓለም ታሪክ አልተመዘገበም፡፡ ሰላማዊ ዜጋን በማንነቱ ምክንያት እንደዚህ መጨፍጨፍ ጀግንነት አይደለም፡፡ ጀግንነት ማለት ከእኩያ ጋር ሲገጥሙና በተመሳሳይ መሣሪያ ተፋልመው ሲሸናነፉ ነው፡፡ የዚያው አሳዛኝ ድራማ ክፍል ሁለት ደግሞ በዚህ ሳምንት በወያኔዎች ማይካድራ በሚባለው ከተማ ውስጥ ተፈጽሟል፡፡ በዚህ ዕልቂት ወደ 550 የሚጠጉ ዜጎች እንዳለቁ ተዘግቧል፡፡ ከዚህ ዕልቂት ቀደም ብሎም ወያኔ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ጦር ውስጥ የነበሩ አማራ የሠራዊት አባላት ላይ በተኙበት ብዙ ዕልቂት እንዳስከተለች ተነግሯል፡፡ ወያኔ በቅርብ ጉድጓድ መቀበርን የፈለገች አትመስልም፤ እያራቀችው ነው፡፡ 

አብን ወደ ኢብን ሲለወጥ ይታየኛል፡፡ አመሠራረቱ ይገባኛል፡፡ የጨነቅው እርጉዝ፣ የባሰበትም እመጫት ያገባሉ እንደሚባለው በአማራው መሰቃየት የተበሳጩ ወገኖች “አብን” ብለው ድርጅት ቢያቋቁሙ እንደጊዜያዊ ሥልት ምንም ቅዋሜ የለኝም፡፡ በሂደት ግን ይህ ስም አማራን በፍጹም ስለማይመጥን “የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ” ወደ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ” መለወጥ ይኖርበታል፡፡ ያኔ ራሳቸውን በነገድ መለካትና በጠባብ የጎሣ ጥብቆ ውስጥ ገብቶ መጨነቅን የሚጠሉ ሶዎች ድርጅቱን ይቀላቀላሉ፡፡ ያኔ አማራ የሚገባውንና የሚያምርበትን በባለሦስት ቀለማት ያሸበረቀ ሰፊ ካባ ይለብሳል፡፡ ያኔ ዛሬ በገዳይነታቸው ካባ የሚሸለሙ ባዶ ጭንቅላቶች ከነሸላሚዎቻቸው ጥጋቸውን ይይዛሉ፡፡ ያኔ “ዛሬስ ምን ዓይነት ዕልቂት የት ቦታ እንሰማ ይሆን?” የሚለው የሰቀቀን ዜና ታሪክ ይሆናል፡፡

… ማንም በማንም ሞት አይደሰት፡፡ መጥፎ ሰው ሲሞት እንደሰው ደስ ሊል መቻሉ ያለ ነው፡፡ ግን ካለቅጥ መደሰት የራስን መፃዒ ዕድልም ማጠልሸት ነው፡፡ ስለሆነም እንዘን፤ እያዘንንም መሞት ያለባቸውን ሰዎች በሰላም እንዲሞቱ እንርዳቸው፡፡ አለመኖራቸው ከመኖራቸው እጅግ የሚጠቅም እንደአቦይ ስብሃትና ጌታቸው አሰፋ ያሉ ሰዎችን እንዲሞቱ ብንረዳ ጥድቅ ነውና አንጨክንባቸው፡፡ የሞት ፋብሪካ ከፍተው የንጹሓን ዜጎቻችንን ሕይወት በየቀኑ የሚቀጥፉ ሰዎች ዘላለማዊ ዕረፍት እንዲያገኙና እኛም እፎይ እንድንል በፍልሚያው ቦታ ያላችሁ የሕዝብ ልጆች የበኩላችሁን ድርሻ ተወጡ፡፡ ፑቲን እንዲህ አለ አሉ – እጠቅሳለሁ – “ለሽብርተኞች ምሕረት የማድረግ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ነው፤ የኔ ኃላፊነት ሽብርተኞችን ወደርሱ መላክ ነው፡፡” ግሩም አባባል፡፡ ሳይቃጠል በቅጠል፡፡   

አማራ በወያኔ የተወሰዱበትን መሬቶች ለመረከብ አይቸኩል፡፡ የጅብ ችኩል መሆን አይገባም፡፡ “ሰባት ዓመት የታወረ ሰው ‹ነገ ዐይንህ ይበራል› ቢሉት፣ ‹ዛሬን እንዴት አድሬ?› ይላል” አሉ፡፡ ለ30 ዓመታት ወያኔ የተጫወተበትን መሬትና ሕዝብ በአንድ ቀንና በሁለት ቀን ጦርነት ያለ ደረሰኝና ያለማወራረጃ ለማስመለስ መቻኮል ብልኅነት አይደለም፤ የሚያስቸኩል ነገርም የለም፡፡ መጀመሪያ ጭራቆቹ እንደማይመለሱ ሆነው ከነሰንኮፋቸው ይውደሙ፤ ነገ ሌላ ዕልቂት የማይደግሱልን ስለመሆናቸው እርግጠኞች ሳንሆን በብጫቂ መሬት ትዝብት ውስጥ አንግባ – ዓላማችን ሰውን ማዳን ይሁን፡፡ የኛ የሆነ ያራል ይሻግታል እንጂ መቼም ቢሆን የኛው ነው፡፡ በመሠረቱና እንደእውነቱ ደግሞ ይሄ ሸፋፋ ህገ መንግሥት ተብዬ ሲቀዳደድና ሀገር እንደገና ስትፈጠር ሁሉም የኛ ነው፡፡ ወልቃይትና ራያ የሚያወዛግበን የወያኔ ሤራ የተከለብን የዘር ፖለቲካ እንጂ የጂማው ጎንደር ላይ፣ የወሎው ሙርሲ ላይ፣ የሃዲያው ትግራይ ላይ፣ የወለጋው ጎጃም ላይ … ቢንፈላሰስ ሀገሩ ነውና ማንም ጠያቂ የለውም፡፡ በዚህ ዓይነት ሀገራዊ አደረጃጀት ወልቃይት ቅብጥርስ ቦታ የለውም፡፡ “የኛ”ና “የነሱ” የምንለው ሽል መንጣሪ ወያኔያዊ ርዕዮተ ዓለምና ፍልስፍና ቀርቶ ሁሉም የኛ ከሆነና በዜግነትህ እንጂ በዘርህ መስተናገድ ከቀረ ይህ የሚታየው ውዥንብር ሁሉ እንደጉም ተኖ፣ እንደጤዛ ረግፎ ወደታሪክ ትቢያነት ይለወጣል፡፡ ስለዚህ በቁራጭ መሬቶች ላይ ሳይሆን በትልቁ ሀገራዊ ምስል ላይ እናተኩር፡፡ ትልቅ እንመኝ – ትልቅ እንድናገኝ፡፡ አማራውም ሆነ ትግሬው፣ ጉራጌውም ሆነ ኦሮሞው፣ ሶማሌውም ሆነ ከምባታው… ከቁርጥራጭ የግጦሽም በለው የእርሻ መሬቶች የሰፋች ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችው፡፡ ስለዚህ ትዝብት ውስጥ እንዳንገባ በአስተውሎት እንራመድ፡፡ አንዷ “እንዲህ ልጠግብ በሬየን አረድኩ” አለች አሉ፡፡ እውነቷን ነው፡፡

አክራሪ ኦሮሞ ጠግቧል፤ የጥጋቡን ግን በቅርብ ያገኛል፡፡ የእርጉዝ ሴት ሆድ ቀድዶ ያልተወለዱ ሕጻናትን አንገት በጠሰ፤ ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት አማሮችን በስብሰባ ስም ጠርቶ ሕጻን አሮጊት ሳይል በመትረየስ ጨፈጨፈ፤ ቤት ንበረት አቃጠለ፡፡ ምስኪን የዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎችን አፍኖ ወሰደ፤ የጠየቀውም የለም፡፡ እንዴት ጀግና ነው ግን ጃል! ወንዶቹ በሚውሉበት ቦታ ቢሄድ ይሄኔ እማዬ ድረሽ ይላል፤ ደግነቱ ያም ቀን ቀርቧል፡፡ እናቱ ማኅጸን ቢደበቅ እያንዳንዱ ወንጀለኛ የማያመልጥበት ቀን በፊታችን አለ፡፡ ማንም ቢሆን የዘራውን ያጭዳል፡፡ ግና እንጸልይ፤ ከጥፋት መንገድ እንመለስ፤ ከተፈጥሮ ውጪ የምንጓዝ ተጸጽተን በቶሎ ንስሃ እንግባ፤ አሥረሽ ምቺው በዝቷልና ገደብ ይበጅለት፡፡ “ሰይጣን ቆንጆ ድስት ይሠራል መግላሊት ግን አይሠራለትም” ይባላል፡፡ የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለምና ከፈጣሪ መንገድ ያወጣንን ገንዘብም ሆነ ወሲብ ወይም ሥልጣን ገደብ ካላበጀንለት መጨረሻችን አያምርም፡፡…. 

ጦርነቱ ሰላማዊ እንዲሆን እየተመኘሁ እዚያና እዚህ የሚረግጥ ወሬየን እዚህች ላይ ላብቃ፡፡ ቸር ያሰማን!

Filed in: Amharic