አሳሳቢው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ
ደረጀ መላኩ ( የሰብአዊ መብት ተሟጋች )
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚታዩት፣ የሚሰሙት ዜናዎች ተስፋን የሚጭሩ አይደሉም፡፡ ምንም እንኳን በመንግስት የዜና አውታሮችና በአንዳንድ የግል መገናኛ ብዙሃን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው እየጎመራ ስለመሆኑ በየጊዜው ቢሰማም፣ በሌላው ሳንቲሙ ግልባጭ የሀገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ እንቅልፍ የሚነሳ ከሆነ ሰነበተ፡፡
በነገራችን ላይ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ በአይምሮዬ ጓዳ ሳሰላስል ቶሎ ብልጭ ብሎ የሚመጣልኝ ሀሳብ የመልክአ ምድር (Geography) ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡ ይህም የመሬት መንቀጥቀጥ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳይ ድንገት እንደሚከሰት የመሬት መነቀጥቀጥ አይነት እንዳይሆን በብርቱ እሰጋለሁ፡፡ የኮምፒዩተር መስኮታችሁን ከፍታችሁ ኢንትርኔት ውስጥ ከገባሁ በኋላ ጎግል በማድረግ በአለማችን በመሬት መነቀጥቀጥ ሊጎዱ የሚችሉ ሀገራትን ማወቅ ይቻላል፡፡ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያትና ውጤት ላይ የሚያጠኑ የመስኩ ጠበብቶች በደረሱበት ድምዳሜ መሰረት በአለም ላይ የተለያዩ ቦታዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ከዚህ በፊት ተከስቶ እንደነበርና ወደፊትም የሚጠቁ አካባቢዎች እንዳሉ በጥናታቸው አረጋጠዋል፡፡ ይህ እንግሪ በተፈጥሮአዊው የመሬት መንቀጥቀጥ ሊጠቁ የሚችሉ ሀገሮችን ለማወቅ ፍላጎቱ ላላችሁ ለመጠቆም ያክል እንጂ የዛሬው ጽሁፌ ዋነኛ አላማ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አቅጣጫ በእጅጉ ስላሳሰበኝ የግል አስተያየቴን ለማቅረብ ነው፡፡
በርካታ የፖለቲካ ሃያስያን በአንድ ሀገር ላይ የሚከሰቱ ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በጠረቤዛ ዙሪያ ፣ በውይይት መፈታት እንዳለበት አበክረው ያሳስባሉ፡፡ በሀገሪቱ ያሉትን ፖለቲካዊ ልዩነቶች ሁሉ በሃይል በጉልበት ለመፍታት መሞከር አስቻጋሪ ነው፡፡ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸውን ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሪዎች ዘብጥያ መወርወር ለግዜው ይጠቅም ይሆናል እንጂ ውሎ አድሮ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች የሰው ሕይወትን የሚቀጥፉትን ወንጀለኞች በፍጥነት በፍትህ አደባባይ አለማቅረብ፣ በህይወት የመኖር መብት ብረት ባነገቱ ቡድኖች ወይም የመንግስት አካሎች ከመገሰሱ በፊት የማእከላዊው መንግስት የመከላከል ግዴታ አለበት፡፡ የሰብአዊ መብቶች እንዳይገፈፉ መንግስት የተሰጠውን መንግስታዊ ሃላፊነቱን መወጣት ከተሳነው የፖለቲካው ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ መዶሉ አይቀሬ መራር ሀቅ ነው፡፡ በሌላ በኩል የጦር አውርድ የፖለቲከኞች እንካ ሰላምታ ለአንድ ሀገር ሰላምን ሊያስገኝ አይቻለውም፡፡ ፖለቲከኞች በመሃከላቸው ያለውን ልዩነት በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ እንማጸናለን፡፡
የሁሉንም አካባቢዎች ህዘብ ይወክላሉ ተብሎ ባይገመትም ከጎሳ ፖለቲካ ተከታዮች አኳያ በኢትዮጵያ ሶስት አይነት ፖለቲካዊ ትችት ወይም ብሶቶች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በተለይም በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ሲነገር እንሰማለን፡፡ ተጽፎም እናነባለን፡፡ የአንደኛው ወገን ነን የሚሉ አንዳንድ አክራሪ ጎሰኞች ተከዳን ሲሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ አሁን ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ስልጣኑን መልቀቅ አለበት ባይ ናቸው፡፡ በሌላው ጫፍ የሚገኙት ሌሎች ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይን በላይነት በኦሮሞ የበላይነት ለመተካት የሚሰራ ነው በማለት ይከራከራሉ፡፡ ለማናቸውም በእኔ በኩል ሶስቱንም ከላይ ያሰፈርኳቸውን አስተሳሰቦች ( እንደ ሀሳብ ከተቆጠሩ ማለቴ ነው፡፡ )እንደሚከተለው ለመመርመር እሞክራለሁ፡፡
ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ( ከ1983 ዓ.ም. -2010 ዓ.ም.) ኢትዮጵያንና ህዝቧን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው ይገዙ የነበሩት የወያኔ ኢህአዲግ የፖለቲካ ፊትአውረሪዎች የትግራይን የበላይነት አስፍነው እንደነበር በብዙ ኢትዮጵያውያን እምነት ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የወያኔ አገዛዝ ይህን አይቀበለውም ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር እኛ የኢትዮጵያን ህዝብ በእኩል አይን ነው የምናየው በማለት በአደባባይ ያለ ሀፈረት ይደሰኩሩ ነበር፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ቁልፍ የስልጣን ቦታዎች በወያኔ አባላት የተያዙ ነበሩ፡፡ ይህ እውነት ነው መካድ አይቻልም፡፡ ዛሬ ላይመለስ ስልጣናቸውን ተነጥቀዋል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ መንገዶች የፌዴራል መንግስቱን ለማዳከም ወይም ሰላም እንዳያገኝ በተለያዩ መንገዶች ስለመሞከራቸው የአደባባ ሚስጥር ነው፡፡ በአጭሩ የሀገሪቱን ሰላም ለማናጋት ጠብያለሽ በዳቦ ካሉ ውለው አድረዋል፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚከሰቱ አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የወያኔ ቡድን እጅ ከጀርባው እንዳለበት አንዳንድ የክልል መስተዳድሮች ከፍተኛ ባለስልጣናት ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በቀን ብርሃን ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰማ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ባሻግር የወያኔ የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች ሳይደብቁ የፌዴራል መንግስቱን ፊትለፊት እንደጠላት እንደሚቆጥሩት ቤጊዜው ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እራሳቸው ካጸደቁት ህገመንግስት ተጻራሪ በሆነ መልኩ የክልል ምርጫ አካሂደዋል፡፡ ፍጹም ከህገመንግሰቱ ባፈነገጠ መልኩ የኮማንዶ ብርጌድ ጦር አቋቁመዋል፡፡ የወያኔ አመራሮች ለጦርነት የሚዘጋጁ ይመስላሉ፡፡
ለምን ይሆን የወያኔ አመራሮች የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችን በተለይም ዶክተር አብይን ከዱን ብለው የሚወቅሷቸው ? እኔ እንደሚመስለኝ የብልጽግና ፓርቲ ከመመስረቱ በፊት ስልጣኑን የያዘው የለውጥ ሀይል ወያኔ ላለፉት ሀያሰባት (27) አመታት የሰራውን ግፍና በደል ስላጋለጣቸው ነው፡፡ ምንም እንኳን የወያኔ የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች እንደሚከራከሩት ባለፉት ሀያሰባት አመታት የተፈጸመው አይን ያወጣ የሙስና እና ኢሰብአዊ ድርጊት የተፈጸመው በኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራቲክ ፓርቲ( Oromo Peoples’ Democratic Party(OPDO ) ) እና በአማራ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ እንቅስቃሴ the (Amhara National Democratic Movement ) (ANDM), አመራር ድጋፍ ነው ቢሉም የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ለተፈጸሙት ኢሰብአዊ ድርጊቶችና የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብትና ንብረት ከመዝረፍ አኳያ የወያኔ አመራሮች ተወዳዳሪ አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በኢትዮጵያ ምድር ለተፈጸሙ ግፍና በደል እንዲሁም ዝርፊያ የወያኔ አመራሮች ብቻቸውን ተጠያቂ አይደሉም፡፡ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሙስናም ይሁን በኢሰብአዊ ድርጊት የተሳተፉት ተጠያቂ መሆናቸው አይቀርም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የወያኔ አገዛዝ ከማእከላዊ መንግስት ስልጣኑ ተሸቀንጥሮ ከወደቀ በኋላ እና መቀመጫውን ሰሜናዊት ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ መቀመጫውን ማድረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት (12) ወራቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ለዶክተር አብይ መንግስት ድጋፍ ስለመስጠቱ የሚያከራክር አይመስለኝም፡፡ በዚህ ምክንያት የህውሀት የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች የባይተዋርነት ስሜት እየተሰማቸው ይገኛል ወይም ተገፋን የሚል ስሜት ውስጥ የወደቁ ይመስላሉ፡፡ ከዚህም እልፍ በማለት እኛን ከጠላችሁን የራሳችንን የራስ ገዝ ግዛት ለመፍጠር እንገደዳለን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ ለዚህም በህገመንግስቱ አንቀጽ 39 ላይ የሰፈረውን ቃል ሲጠቅሱ ይሰማል፡፡
The TPLF felt the rejection and its leaders repeatedly were heard to say that ‘if we are not respected but hated, we’ll be forced to create our own de facto state’; a position which article 39 of the constitution supports as well.
በነገራችን ላይ በሟቹ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዘመነ መንግስት አቶ መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግስት የኢህአዲግ አገዛዝ በአደረገው ጥናት መሰረት የኢህአዲግ አባል ድርጅቶችን በአንድ ፓርቲ ጥላ ስር ለማዋሀድ ተወስኖ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ለጥሩም ሆነ መጥፎ ምክንያት በጊዜው የነበሩት የኢህአዲግ የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች ለሰባት አመታት አዘግይተውታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶክተር አቢይ የስልጣን መንበሩን ከጨበጡ በኋላ ሁሉንም የኢህአዲግ አባል ድርጅቶችን በአንድ ፓርቲ ጥላ ስር አድርገዋቸዋል፡፡ ( የዚሁ የአንድ ፓርቲ ስም ብልጽግና በሚል መጠሪያ ይታወቃል፡፡) በነገራችን ላይ የህውሀት ፖለቲካ ፓርቲ ወደዚሁ ጥምረት እንዲገባ ተጋብዞ ግብዣውን ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ሀያስያን በጥናት እንደደረሱበት ከሆነ አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ የወያኔን የበላይነት የሚቀበል እንዳልሆነ ይገመታል፡፡
ምንም እንኳን ህውሀት ከአመታት በፊት የኢህአዲግ አባል ድርጅቶችን በአባልነት ያሰባሰበ አንድ ፓርቲ ለመመስረት ቢስማማም፣ ዛሬ ድንገት ብድግ ብሎ የተመሰረተው አንድ ፓርቲ ህጋዊ አይደለም ለማለት የሞራል ብቃት ያለው አይመስለኝም፡፡ ከህውሀት ውሳኔ የምንረዳው ነገር ቢኖር ሰዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ አቋሞችን እንደሚይዙ ነው፡፡ Many agreed that TPLF attempted to introduce a double standard regarding the establishment of one party out of the EPRDF.
ከላይ በጠቀስኳቸውና በሌሎች ምክንያቶች የህውሀት ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የዶክተር አብይን መንግስት እንደጠላት ይቆጥሩታል፡፡ ሁላችንም እንደምንስማማው ከሆነ የወያኔ የበላይነት እንዲያከትምለት የዶክተር አቢይ መንግስት ሁነኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡ ከዚህ በሻግር ወያኔ የፈጸመውን ግፍና ሙስና በአደባባይ አስጥቶታል፡፡ ከብዙ የመገናኛ ብዙሃን የዜና አውታሮች ዘገባ፣ ሀተታ እና የጶለቲካ ሀያሳያንን ቃለ ምልልስ መሰረት አድርገው ከሚቀርቡ ዝግጅቶች እንደሚሰማው ወይም ለመረዳት እንደሚቻለው ከሆነ በኢትዮጵያ የተለያዩ ግዛቶች በሚፈጸሙ ኢሰብአዊ ድርጊቶችና የሰላም መደፍረስ ጀርባ የወያኔ እጅ እንዳለበት ይታመናል፡፡ ስለሆነም የወያኔ ቡድን የዶክተር አብይን መንግስትን ቢያወግዝና ሰላምን ለማደፍረስ ብዙ እርቀት ቢጓዝ የሚያስገርም አይደለም፡፡ አለማቸው ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡
እውን የሕውሀት የፖለቲካ ፊትአውራሪዎች የኢትዮጵያን ማእከላዊ መንግስት ስልጣን ለማናጋት የሚያካሂዱት የሴራ ፖለቲካ ይሳካላቸው ይሆን እውን በአለም ላይ እውቅና የሌላት ነጻ ግዛት ለመመስረት ይችሉ ይሆን እውን የትግራይ ክልል መስተዳድር ገዢዎች ከ30 አመታት በፊት እንዳደረጉት በፌዴራል መንግስቱ ላይ የጦርነት ነጋሪት ይጎስሙ ይሆን (ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ጊዜ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. እኩለ ለሊት ላይ ጦርነት መክፈታቸውን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ በማህበራዊ ድረገጽ መስኮታቸው ላይ ከለጠፉት ጽሁፍ ላይ አብቤአለሁ፡፡ ) በነገራችን ላይ የህውሀት መሪዎች ከ40 አመት በፊት ከነበሩበት የማርክሲስት ሌኒንስት ርእዮት አለም እሳቤ የተላቀቁ አይመስለኝም፡፡ ምንም እንኳን የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብት በመዝረፍ የታወቁ ቱጃሮች ለመሆን ወግ ቢደርቸውም ( እንደወግ ከተቆጠረ ማለቴ ነው፡፡) እነርሱ ዛሬም የእነእስታሊን የርእዮትአለም ምርኮኛ ናቸው፡፡ የትግራይን ህዝብ እንደ ሰብአዊ ጋሻነት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ ወንድማችን እህታችን እድሉ በነጻነት ተሰጥቶት ወያኔ ወይም ኢትዮጵያ ትሻልሃለች ተብሎ ጥያቄ ቢቀርብለት መልሱ ምን ይሆናል ለሚለው ጥያቄ ህሊና ለፈጠረባችሁ አንባብያን ትቼዋለሁ፡፡ በእኔ አስተያየት የትግራይ ህዝብ ወንድማችን፣ እህታችን፣ እናቶቻችን፣ አባቶቻችን በቃኝ የሚልበት ቀን የሚመጣ ይመስለኛል ፡፡ የህውሀት የፖለቲካ መሪዎች የትግራይን ህዝብ በሰብአዊ ጋሻነት ይያዙት እንጂ የትግራይ ህዝብ ነጻነቱን የሚያስከብርበት ቀን ይመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ (The TPLF holds now the Tigray people as a human shield. Time will come when the Tigray people to say “enough is enough”. )
ምንም እንኳን ቄሮ በመባል የሚጠሩት ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ወጣቶች የወያኔን አገዛዝ ለመጣል በተደረገው ትግል ከባድ መስእዋትነት የከፈሉ መሆናቸው የታወቀ ቢሆንም፣ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው የከፈሉት መስእዋትነት መዘንጋት የለበትም፡፡ በኢህአዲግ ውስጥ የነበሩት ፓርቲዎች አመራሮች ( ኦህዲድ እና የአዴፓ አመራሮችን ማለቴ ነው) የወሰዱትን ስትራቴጂክ ስልት ሳንዘነጋ ማለቴ ነው፡፡ ዛሬ ስማቸው ተቀይሮ የብልጽግና ፓርቲ ተብሎው እንደሚጠሩ ሁላችንም የምናውቀው ይመስለኛል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በተለይም በአንዳንድ በኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ልዩነት ያለ ይመስላል፡፡ ለአብነት ያህል በኢትዮጵያ የማእከላዊ መንግስቱን ስልጣኑን የኦዴፓ እና አዴፓ፣ እንዲሁም የሌሎች የብልጽግና ፓርቲ አጋር ድርጅቶች አመራሮች ናቸው ( የስልጣን እርከን እና ደረጃ ላይ ያለው ልዩነት ሳይዘነጋ …) ሆኖም ግን ይሁንና በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ እንደነ አቶ ጃዋር፣ አቶ በቀለ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ሌሎች የኦነግ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ እጅግ ጨካኝ ግድያ የሚፈጽሙ የኦነግ ሸኔ አባላት ይገኙበታል፡፡
ከመንግስት የመገናኛ ብዙሃን በየጊዜው እንደሚሰማው ከሆነ የኦዴፓ ብልጽና ፓርቲና አዴፓ ብልጽና ፓርቲ አመራሮች ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻቸው ጋር ተባብረው ኢትዮጵያን የነጻነት ምድር ለማድረግ እንደሚሰሩ፣ ለህግ የበላይነት፣ ለዲሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር እንደሚታገሉ የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ግን እንዳንድ ጊዜ ተስፋ የሚያስቆርጡ ንግግሮች ከከፍተኛ ባለስልጣናት አንደበት ሳይቀር ይሰማል፡፡ ለአብነት ያህል የአንድ ክልላዊ መስተዳድር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዜዴንት የነፍጠኛውን አከርካሪ ሰብረነዋል ሲሉ መናገራቸውን የመገናኛ ብዙሃን በሰፊው የሄዱበት ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ ግዜ ደግሞ ‹‹ እኛ ቁማሩን አሸንፈናል ወይም ግራ አገባናቸው ›› የሚል ግራ አጋቢ ዲስኩር በአደባባይ ተናግረዋል፡፡
‹‹ The vice president of a given << x >>Ethiopian region at one point said “we have broken the ‘Neftegna’ ” and on another occasion he is quoted as saying “we confused and convinced them
ከላይ ያሰፈርኩትን አወዛጋቢ ዲስኩር በአደባባይ ያሰሙት ከፍተኛ ባለስልጣን ለሚወክሉት የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ለክልላቸው ምክር ቤት ቀርበው በውስጥ ስብሰባቸው ላይ ይቅርታ ስለመጠየቃቸው ወይም ስላለመጠየቃቸው የማቀው ጉዳይ የለም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና አወዛጋቢ ንግግራቸውን በተመለከተ በታወቁ መገናኛ ብዙሃን ፊት ቀርበው ይቅርታ እንዳልጠየቁ አውቃለሁ፡፡ በነገራችን ላይ የባለስልጣኑን አወዛጋቢ ንግግር በተመለከተ የአማራ ክልል ፕሬዜዴንት በማህበራዊ ድረገጻቸው ላይ በለጠፉት ጽሁፍ ‹‹ እኛ ግራ አልተጋብንም ወይም ቁማሩን አልተሸነፍንም ›› የሚል መልእክታቸውን አቅረበው ነበር፡፡ መልእክቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ ምክትል ፕሬዜዴንት የተሰጠ ቀጥተኛ ምላሽ ይመስላል፡፡
The Amhara President, in his social media platform, wrote “we are neither confused nor convinced”. The statement seemed a direct reply to the Oromo Regional v/president
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ባህርዳር ከተማ ድረስ ተጋብዘው በስልጣን አቻቸው የአማራ ክልላዊ መስተዳድር የክብር ካባ ሽልማት ከተበረከተላቸው በኋላ አወዛጋቢ ንግግር ያሰሙት ከፍተኛ ባለስልጣን በብልጽግና ፓርቲ የውስጥ ስብሰባቸው ላይ ይቅርታ ጠይቀዋል የሚል ግምት በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እንዳሳደረ የሚያሳዩ ጽሁፎችን ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡
በነገራችን ኢትዮጵያውያን ሁሉ በተለይም ስለ የኢትዮጵያ አንድነት የሚሰብኩና የሚጨነቁት ሁሉ ባፉት ሁለት አመታት በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር አንዳንድ ቦታዎች ላይ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደሚያሳስባቸው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ማውገዛቸውን፣ አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ስለመፈጸሙ በብዙ መልኩ መጻፋቸውን እናስታውሳለን፡፡ በተለይም ታዋቂው የኦሮምኛ ቋንቋ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ ( ነፍሱን ይማረው) በንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግድያ ( ነፍሳቸውን ይማር ) ብዙ ኢትዮጵያውያንን ከባድ ሀዘን ላይ የጣለ ነበር፡፡
እንዲህ አይነት ቅጥ ያጣ ግፍ እና ርህራሄ የሌለው ግድያ በዜጎች ላይ ከመፈጸሙ በፊት የኢትዮጵያ መንግስት መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ወቀሳና ትችትን እንዳስከተለበት እናስታውሳለን፡፡ ከዚህ ባሻግር የአለም አቀፍና ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች መንግስት የዜጎችን የሰብአዊ መብት ማስከበር ተግባሩን እንዲወጣ በብርቱ ማሳሰባቸውን ማስታወሱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ከተሰሙ ዜናዎች በተገኘው መረጃ መሰረት ከ6000 በላይ በሰብአዊ መብት ጥሰት እና በወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ተጠርጥረው የታሰሩ ግለሰቦች ነበሩ፡፡ ( ከእነኚሁ ተጠርጣሪዎች መሃከል በመቶዎች የሚቆጠሩት በተለያዩ የመንግስት ተቋማት የስራ ሀላፊዎች ነበሩ፡፡)
በመጨረሻም ሶስት መላምቶችን በማቅረብ የዛሬውን ጽሁፌን እቋጫለሁ፡፡ ( ማስረጃ ለማቅረብ አዳጋች ይሆናል በሚል አመክንዮ እንጂ እንዲህ አይነት ሃሳቦችን በአደባባይ፣ በየኪዮስክ ቤቱ፣ በቡና ቤት ሳይቀር፣ በማህበራዊ ድረገጽ ላይ የሚሰነዝሩ ወይም የሚናገሩ ወይም የሚለጥፉ ሞለተው ተርፈዋል፡፡ ) እስቲ ሶስት የጎሳ ፖለቲካ አራማጆችን ጠባብ አስተሳሰብ ላስቃኛችሁ ( ሀሳብ ከተባለ ማለቴ ነው፡፡ በእኔ አስተያየት ራስወዳድነት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለአብነት ያህል አንድ የአማራ ብሔር ፖለቲካ አቀንቃኝ ምኞትና ፍላጎት ለቆመለት ጎሳ ወይም ብሔር የበላይነት የሚታገል ነው፡፡ አንድ የኦሮሞ ብሔር ፖለቲካ አቀንቃኝ በበኩሉ የኦሮሞ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ ከተማ መከበር አለበት በማለት ሲከራከር ይሰማል፡፡ በሌላ በኩል አንድ የወያኔ ቡድን አመራር ወይም አባል ፍላጎትና ምኞት በማእከላዊ መንግስት ያጣውን ስልጣን ለማስመለስ ምኞትና ፍላጎት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
በነገራችን ከላይ የጠቀስኳቸውን የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞች ምኞትና ፍላጎት ወይም አላማ በዚች አጭር ጽሁፍ ለመግለጽ አዳጋች ቢሆንም፣ እኔ ከእውነታው ብዙም እርቄ የሄድኩ አይመስለኝም፡፡
It might not be that simple to generalize their demands as easily as I have just done but I am not very far from the truth.
ከላይ ካሰፈርኩት እውነታ በመነሳት የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል ? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም
እውን ኢትዮጵያ አንደነቷ ይናጋ ይሆን ? በፍጹም አይመስለኝም፡፡ ምንም እንኳን በሀገሪቱ ልሳነ ምድር ያሉ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ልዩነት ሰፊ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ፍጹም ዋልታ ረገጥ ልዩነት አለን ቢሉም፣ በሀገሪቱ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ( ሀገሪቱ ደሃ በመሆኗ ምክንያት)፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ስነልቦና ( በደቡብ፣ሰሜን፣ ምስራቅና ምእራብ የሚኖረው ህዝብ ) ለመለያየት የተዘጋጀ ባለመሆኑ ምክንያት የኢትዮጵያን አንድነት ይደግፋል፡፡ እርግጥ ነው ህዝቡ ንቃተ ህሊናውን ማስፋት ከተሳነው፣ የጎሰኞች ተከታይ ለመሆን ከፈቀደ ፣ ለዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብቶችና ለህግ የበላይነት ካልታገለ በቀር አንድነቱ ሊላ ይቻለዋል፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰማየ ሰማያት የሚስተዋለውም ይሄው መራር እውነት ነው፡፡
እውን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሚያሰጋቸው ሀገራት በአደጋ ላይ የሚገኝ ነውን ? እርግጥ ነው ይህ የተጋነነ ጥያቄ ይመስላል ሆኖም ግን ይሁንና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሀኔታ በአግባቡ ካልተያዘና ነጻነት አልባ ከሆነ ከብዙ አመታት በኋላ ሊፈነዳ እንደሚችል ዘገምተኛ እሳተ ገሞራ አይነት ሊመሰል ይቻለዋል፡፡ የሚያዋጣው ኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን በሰከነ መንፈስ አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ በመባባል አንድነታቸውን ማጥበቅ ነው፡፡ መለያየት ውድቀትን እንጂ ብልጽናን አያጎናጽንም፡፡
የ19ኛው ክፍለዘመን የጀርመኑ ፈለስፋ Friedrich Nietzsche በአንድ ወቅት እንደተናገረው ‹‹ የማይገልህ ነገር ያጠነክርሃል ›› የኢትዮጵያ ክፉዋን እንደሚያስቡት እኩያን ምኞት ኢትዮጵያ አትፈርስም፡፡ በተቃራኒው በኢትዮጵያ ያለውን ልዩነት እንደ ውበት ካየነው፣ ኢትዮጵያውያን ርሰበርሳቸው ከተከባበሩ፣ የህግ የበላይነት ገቢራዊ ከሆነ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች፡፡
. As the 19th century German philosopher Friedrich Nietzsche once said “What doesn’t kill you, makes you stronger”. Ethiopia will not crumble as some nihilists might wish, but will prevail, stronger where diversity is appreciated and valued, where people respect each other and the rule of law prescribed.
በትግራይና አማራ ክልሎች መሃከል፣በኦሮሞና አማራ ክልሎች መሃከል፣በአፋርና ሶማ ክልሎች መሃከል ወዘተ ወዘተ ወድድርና ፉክክር መደረጉ ጤናማ ነው፡፡ ወድድሩና ፉክክሩ መሆን ያለበት ግን ወጣት ልጆችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማሰልጠን እንጂ ልዩ የክልል ሚሊሻ ለማስለጠን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ክልሎች መፎካከር ካለባቸው ለብዙ ክፍለ ዘመናት ከበሬ ጫንቃ ላይ መነሳት ያልቻለውን የኢትዮጵያ ገበሬ የዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂ ለማድረግ መሆን አለበት፡፡ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ የበለጸገች ሀገር እንድትሆን ቢፎካከሩ የሰውነት ደረጃ የሚያሳይ ስልጣኔን መቋደስ ይቻለናል፡፡ አሳዛኙ ገጽታ ግን አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በስልጣን ሻሞ ትርምስ ውስጥ መዶላቸው ነው፡፡ እነርሱ በፖለቲካ ስልጣን ሻሞ ውስጥ ሲተራመሱ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዜጋ በኑሮ ውድነት አባሳውን ያያል፡፡
እስከመቼ ነው እንዲህ አይነት እንቆቅልሽ የሚቀጥለው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ አይነት ፌዝን መቀበል የደከመው ይመስለኛል፡፡ ለማናቸውም ሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀይሎች እና የኢትዮጵያ መንግስት ቁጭ ብለው በመነጋገር ለህዝባቸው ዘለቄታዊ መፍትሔ ያመጣሉ ብዬ ተስፋ በማድረግ ልሰናበት፡፡