>

የህወሓት ሰዎች  አነሳስና አወዳደቅ በታሪክ ጸሀፊ እይታ...!!! (ምኒልክ ሰይፉ ማሩ)

የህወሓት ሰዎች  አነሳስና አወዳደቅ በታሪክ ጸሀፊ እይታ…!!!

ምኒልክ ሰይፉ ማሩ

እንደማንኛውም አትዮጵያዊ እስከ ስምንተኛ ክፍል በትግራይ ክልል ተማሩ ። ዕድሜያቸው ለአቅመ ጦርነት ሲደርስ ወደው ገቡ።  ከረጅም አመት ትግል በኃላ ወደ አገረር  ገዥነት ተሸጋገሩ። ሁሉም ሳይማሩ ዲግሪ ኖራቸው።
 በዲግሪያቸው →መሬት አዘራረፍ ፣በቀረጥ አወነባበድ እንዲሁም ነፍስ አጠፋፍና ኮንዶሚኒየም አሰራረቅን በደንብ ተማሩ።
ቻይናና ህንድ ከሚገኙ ማስተርስ ሻጭ ድርጅቶች
 በነፃ አስመጭነት፣ በኮዳ አንጠላጠል፣ ፍርድ ማዛባትና በአማራ አጠላል ዘዴዎች፣ የኦሮሞ ወጣትን በማደንቆር፤   አዲስ አበቤን በማጀዘብ ፣ድሬዎችን በማወዛገብ፣ ጋምቤላን በማደደብ፣ ቤንሻንጉልን በማሰይጠን፣ ደቡብን በማንዠዋዠው፣ አፋርን በማስቆዘም ዘዴ እና በመሳሰሉት የትምህርት ዘርፎች ማስተርስሳቸውን አገኙ።
ለብዙ አመታት በሰዎች አሰዋወርና አፈና ዘዴዎች እንዲሁም እንዴት አፄ ምኒሊክን ማስጠላት በሚቻልባቸው ዘዴዎች፣ በአሰተኛ ወሬ ፍብረካና ህንፃ በነፃ አሰራር ዘዴዎች ዶክትሬታቸውን አገኙ።
በመጨረሻም ስልጣን ባመጣባቸው ከፍተኛ መባለግ እመም ለከፍተኛ ህክምና ወደ መቀሌ አመሩ ።
 እንደማይድን የታወቀው የስልጣን ካንሰራቸው ፈንድቶ በየክልሉ በመንሰራፋት መተከል፣ በኦሮሚያና በተለያዩ ቦታዎች ተዛመተ ወደ መሞቻቸው አካባቢ መከላከያ የተባለ ፈፅሞ ካንሰር ሊነካው የማይገባ ቦታ በመነካካታቸው በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ዶክተር ትህዛዝ መሰረት ተቆርጠው እንዲጣሉ ተወሰነባቸው።
ቆርጦ ለመጣል የሚያስፈልጉ እንደ አማራ ልዩ ሀይልና መከላከያ ከትላልቅ ሰንጋዎች ጋር ተዘጋጅተው ኦፕሬሽኑ በመከናወን ላይ ይገኛል።
ለተቆራጩ አካል ነፍስ አይማር ብለናል።
Filed in: Amharic