>

ጠ/ሚኒስትሩ የአማራን እርስቶች በኦሮሙማ ፕሮጀክታቸው ሊውጧቸው አስበው ይሆን? (ደረጄ ከበደ)

ጠ/ሚኒስትሩ የአማራን እርስቶች በኦሮሙማ ፕሮጀክታቸው ሊውጧቸው አስበው ይሆን?

ደረጄ ከበደ

ይህንን የውሸት ጦርነት ምን ብዬ ልሰይመው እያልኩ ሳስብ “ሲውዶዋር” Pseudowar የሚለው ቃል መጣልኝ። የዚህን ቃል ትርጉም ስመለከት በሚገርም ሁኔታ የዚህን ጦርነት ተብዬውን ጉድ በደንብ አድርጎ የሚገልፅ ሆኖ አገኘሁት። ዲክሺነሪ እንዲህ ይተረጉመዋል 
 
A pseudo-war is a conflict which gives a government all the benefits of war but few of the problems.
 
ከጥቃቅን ጉዳቶች በተቀር ገዢውን መደብ የሚጠቅም ግጭት ማለት ነው።
 
ይህ የውሸት ጦርነት አቢይን በብዙ መንገድ ጠቀመ እንጅ ሃገሪቱዋን ወይም አማራን በምንም መልኩ አላተረፋቸውም። እንዲያውም አማራው በዚህ ውስጥ ዋና ታርጌትና ኢላማ ሆኖ ነው ያለው። ትህነግና ህዋሃትም የመቡዋጨር ያህል እንጅ ምንም አልተነኩም። እስካሁን ባለው ገፅታው ሲገመገም ይህ ሹኩቻ ፈረንጆች “Much a do about nothing”  የሚሉት አይነት ነው።
የጊምቢውን የአማራ ጭፍጨፋ ተከትሎ የአቢይ አተዳደር ሳያስበው ጀኖሳይድርነቱ በአለም አደባባይ ተናኘበት፣ ደነገጠ፣ የመጨረሻ ማጨበርበሪያ ካርዱን ሳበ። “ጦርነት!!” ይሀው ነው።
ይህን ቀላል ጥያቄ እንጠይቅ እስቲ—–
ጦርነት ተብዬው ያስመዘገበው ምን ነገር አለ? ለአማራውም ሆነ ለሃገሪቱ ዴሞክራሲ?? ከአማራው ጥፋትና ከከተማዎቹም በጦርነት ስም መደብደብ በቀር? እርግጥ ነው አሁን ለመገምገም አይቻልም ምክንያቱት Pseudowar ሩ አሁንም እየተካሄደ ነው የሚሉኝ ይኖራሉ። እቀበላለሁ።
ግን እንዲያው በአንክሮ ለተመለከተ ሰው እስካሁን ማነው ሰለባው?? አማራው እይደለም?!!
ከጠዋቱም ጦርነቱ በብዙ አቅጣጫ ጥያቄ ጭሮብኛል። እንዲያው አንዳንድ ሰው የሰማውንና ያየውን ነገር ሁሉ ደርሶ መጠራጠር ወይም ሴራ የተለወሰ ነገር አድርጎ ማሰብ ይወዳል (conspiracy-monger)። አለ አይደል! ያጎረሱትን ዝም ብሎ አለመዋጥ! ያን ሰው ሆኜ ይሆን እንዴ የሚል ጥያቄ ጭንቅላቴ ውስጥ ሲደውል እንደነበር አልክድም። ለነገሩ እንኩዋንስ ያገኘነውን ሁሉ ውጠን  ተጠራጣሪዎችም ሆነን እኝህን ጠ/ሚኒስትር አልቻላንቸውም።
አቢይና ህዋሃት/ትህነግ በዚህ ውጊያ-መሰል ሹኩቻቸው ያደረጉት ነገር ኪሳራና ትርፋቸውን መዝነው የጋራ ጠላታቸውን አማራንም በ equation ኑ ውስጥ አስገብተው ካሰሉ በሁዋላ planned with forethought ወይም በዘመኑ እንግሊዝኛ (Calculated Risk) እርምጃ ነው የወሰዱት። እስካሁን ደግሞ ግቡን እየመታ ነው።
የአቢይና ደፂ ጦርነት ትኩረት ከማስቀየሪያነቱ ባሻገር አንድ ትልቅ ተልእኮ አለው። በጦርነት ስም ወይም በማያስከስስ መንገድ አማራውን መጨረስ።
እስቲ እንኝህን ከእሳቤ ውስጥ እናስገባ
1/በጂምላ የተጨፈጨፉት አማራዎች ናቸው, ማይካድራ 524 አማራዎች።
2/ የአረጁና የጠላቶቻቸውን መሳሪያዎች የማይመጥኑ መሳሪያዎች የታጠቁ አማራዎች ከሁዋላ በትግራይ ልዩ ሃይል፣ ከፊት በመከላከያ መሃከል ተወርውረው ታርጌት የሆኑት አማራዎች ናቸው። ለብዙ መቶ የታጠቁ አማራዎች ጦር ግንባር መማገድና መጨፍጨፍ ምክንያት ሆኖአል።
3/ ሮኬቱም ወደ አማራ ከተሞች ነው እየተተኮሰ ያለው አስመራ የሚል አሁን አሁን ብንሰማም። የባህር ዳር ኤርፖርት እንደተመታ ሰምተናል
4/ ህዋሃትም መከላከያም በደንብ ያላቸውን መሳሪያ ተጠቅመው የቀለጠ ጦርነት ውስጥ አልገቡም። አንዱ ወገን ለሌላው ወገን የሚሳሳ ይመስላል። በተለይ ትግራይ ምንም ሳይዋጋ የያዛቸውን የአማራ ግዛቶች ዝም ብሎ ለቆ ወጣ ማለት ትልቅ ጥርጣሬ ውስጥ ሊከተን ይገባል
5/ በሁለቱ ወገኖች መካከል መናበብ አለ ብዬ የማምንበት ሌላው ምክንያት የተመለሱ የአማራ ግዛቶች ምእራብ ትግራይ ተብለው ለህዋሃት ሊመለሱለት ነው ወይም ኦሮሙማ ይውጣቸው ይሆናል። ለዛም ይመስላል ትህነጎች ምንም ሳይዋጉ ለቀው የወጡት።
6/ አቢይ ህዋሃትንና ትህነግን በአለም የቴረሪስት ግሩፕ እንዳይደመሩ የማይካድራውንም ጭፍጨፋ ትግሬዎች አደረጉ ብሎ አልፈረጀም። የመንግስት ሚዲያዎችም ዜናውን ከትህነግ ጋር አያይዘው ከመዘገብ ተቆጥበዋል።
7/ አሁንም አማራው የአቢይን ጦርነት እየተዋጋ ባለበት ሰአት እየታረደ መቀጠሉ። ትላንት በመተከል፣ድባጤ ቂዶና ከ60 በላይ አብዛኛዎቹ አማራዎች (ሁሉም አይደለሙ፣ ታርጌቱ ግን አማራው ነበር) ከአውቶብስ እንዲወርዱ ተደርገው ተጨፍጭፈዋል
8/ በአማራው ላይ በተለያየ ወቅት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመውና አስፈፅመው እጆቻቸው በደም የተጨማለቀ ሰዎችን ከስልጣን በማውረድ ስም ካንዣበበባቸው የህግና የህዝብ መአት ለማስመለጥ በግርግሩ በጠ/ሚኒስትሩ ሹም ሽረት መደረግ። ለምሳሌ የሽመልስ አብዲሳ፣ የደብረፅዮንና የተመስገን ጥሩነህ ከርእሰ መስተዳደርነት መገለል በወንጀል እንዳይጠየቁ በምክክር የሆነ እንጅ እነኝህ ሁለት ነፍሰገዳዮችን ሳይወዱ አቢይ ከስልጣናቸው የማውረድ እርምጃ አልወሰደም።
 ይህ ጦርነት የጄኖሳይድን ወሬ ማፈኛ፣ ትኩረት ማስቀየሪያና በተለይም ደግሞ አማራውን መማገጃ  እንጅ፣ ህዋሃትን ነቅሎ ለመጣያ፣ ወይም ትህነግን ማስወገጃ፣ ወይም በሃይል የተወሰዱትን የአማራውን እርስቶች ማስመለሻ፣ ወይም የመቀሌ ወንጀለኞችን፣ ህወሃትንና ትህነግን የማስወገጃ ጦርነት አልነበረም ያልኩባቸውን ምክንያቶች እስካሁን ከተመዘገቡት የጦርነቱ ውጤቶች ስናይ ውነትም ስሜት ይሰጣሉ ያሰኛል።
አያችሁ ወገኖቼ፣ እላይ እንድገለፅኩት ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ከጠላት ካምፕ የሚደርሱትን ጥቃቅን ጉዳቶችን ማስተናገድ የጦርነት አንዱ ስልት ነው። 20 ሰዎችን የማጣት Risk ወስዶ በመቶዎች ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ ጠላቶችንና ሰፈሮቻቸውን የመደምሰስ እርምጃ መውሰድ የተለመደ ነው (calculated risk)። በዚህ ጦርነት የህዋሃት ልዩ ሃይሎችና የትህነግ ሰራዊት አልተነኩም ማለት አይደለም። ለምሳሌ ከያዙዋቸው የአማራ ግዛቶች ሲለቁ አይተናል። የሞቱም አሉ። ነገር ግን ከከሰሩት ይልቅ ያተረፉት እጅግ ብዙ ነው። ተመለሱ የተባሉት የአማራ ግዛቶች ለአማራው አልተላለፉም።
ጦርነቱን የተለመደው የአቢይ ማወናበጃ ነው ባልኩ ጊዜ አብዛኛው ሰው፣ ለአማራው የሚቆረቆረውንም ክፍል ጨምሮ፣ ጦርነቱ ”አማራው ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው፣ በፌዴራሉ ሰራዊት/መከላከያ የታገዘ፣ በነመለስ ዜናዊ የተወሰዱበትን እርስቶቹን ለማስለቀቅ ያገኘው ወርቅ እድል ነው” እያለ ነበር የሞገተኝ። ከዚህ በፊት ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በተመሳሳይ ጎዳና ረጅም ርቀት አብረን ተጉዘናል። አሰራራቸው እስካሁን ያልገባው መቼም ይገባዋል ብዬ አልልም። ግን ጦርነት ብለው ማወጃቸው በአንድ በኩል ደስ አለኝ፣ ምክንያቱም ጠ/ሚኒስትሩ ህዝቡን ማሞኛ ካርዳቸውን መዘው ወደመጨረሳቸው መቃረባቸውን አበሰረኝ። በሌላ በኩል ደግሞ እኩይነታቸውን ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ በማየቴ ለሃገራችን ምንኛ አደገኛ ሰው እንደሆኑ መገንዘብ ቻልኩ።
አማራው በተለይ ለጦርነቱ ልዩ ሃላፊነት እንዳለበት እንዲሰማው እንዴት አደርጉ?? 
አማራውን የጦርነቱ ተካፋይ እንዲሆንም ጥሩ ቅንብር ተደርጎበታል። ትህነግ አጠቃ የተባለው የሰሜኑን እዝ ብቻ ነው ቢባል ኖሮ አማራው ብቻ መከላከያን የመቀላቀል ግዴታ አይኖርበትም ነበር ምክንያቱም የፌዴራል አካል ነውና የተጠቃው። ነገር ግን የጦርነቱ አላማ ሲጀመር አማራውን እግረመንገዳቸውን ለመጨረስ ስለነበር አማራውን የግዴታ በጦርነቱ እንዲሳተፍ የሚያደርጉ ምክንያቶችን አከሉበት። ለምሳሌ ያህል ትህነግ አጠቃቸው ከተባሉት ታርጌቶች መካከል የአማራ ክልል የሆኑት እነዳንሻም ተካተቱ። ዳንሻ የአማራ ክልል ስለሆነ እንግዲህ ብአዴን አማራውን ተነስ ክልልህ ተጠቅቶአል ብሎ ትእዛዝ ለመስጠት መንገድ ሆነው ማለት ነው። ነገሩ ውሎ አድሮ እንደታየው ግን የአቢይን ጦርነት አማራው እንዲዋጋለትና በዚያም እንዲያልቅ ነበር የተጠነሰሰው።
አማራው ምንም ሳያቅማማ ለምን መከላከያን ተቀላቀለ?? 
ልብ የሚሰብር ነገር ነው። የዚህ መንግስት ሸፍጠኝነትና ጭካኔ እንዲሁም ንቀት በአማራው ብሄር ላይ፣ ይህ ነው አይባልም።
አማራው ከመከላከያ ጋር አብሮ ትህነግን እንዲወጋ በተጠራ ጊዜ እሱ ያሰበውና ያለመው እርስቱ በዶ/ር አቢይ ሰራዊት እገዛ ሊመለስለት ነው ብሎ ነበር። ትህነግ ከአማራው ክልል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊወጣልን ነው ብሎ ነበር፣ በክልላችን መዋከብ ሊቀር ነው፣ ሁመራን ልናርስ ነው፣ ወልቃይት ወደ እናት ምድሩዋ ልትመለስ ነው፣ ጠለምትም ራያም ወዘተ ብሎ ነበር ያሰበው። የዋሁ አማራ ጎመጀ፣ ነፃነትን ለማየት በዱላም ዝመት ቢሉት ይዘምት ነበር።
ከጦርነቱ ጥንስስ በስተጀርባ ግን እኩይ ሰዎች እንደነበሩ አልተገነዘበም። በሰዎች ህይወት ቁማር የሚጫወቱ አመራሮችና ጄነራሎች እንደነበሩበት ትዝም አላለውም ነበር። እሱ የዋህና ይቅር ባይ ስለሆነ ጠ/ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት አስጨፍጭፈውትም እንኩዋን ያንን ረስቶ መሪው ለእርሱ እርስት ግድ ይሰጣቸዋል ብሎ አመነ። ይሄ የዋህነቱ ነው አማራውን የቀበረው!!!!!
እርካብና መንበር
ጠ/ሚኒስትራችን አማራው መስማት የሚፈልገውን ነገር አሰምተውት ነበር ትህነግን ከመግጠሙ በፊት። ትዝ ይለናል አይደል ይህ አሰራር???የእርካብና መንበርን ገፅ ኮፒ አድርጌ እንድታዩት ያህል ከዚህ በታች እዩት። “የሚፈልጉትን ነገር አያሳየህ ወደሚፈልጉት ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው” ከዚያም “በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” የሚለውን ተረት ተርትባቸው። ጠ/ሚኒስትሩ ይችን ዘዴአቸውን በአማራው ታጣቂ ላይ ሲጠቀሙ ምን አሉ? “ጀግናው የአማራ ታጣቂ/ገበሬ….” ብለው ትላንትና በኦነግና በኦነግ ሸኔ ያስገደሉትን አማራ አሁን ለጦርነቱ ሲፈልጉት ይቺን በማስመሰል የተሞላች ሙገሳና ሽንገላ በጆሮው አንቆረቆሩለት። ለነገሩ የሳቸው ጣፋጭ ንግግር ሳይሆን አማራውን ያዘመተው የተነጠቀው የእናት አባቶቹ፣ የአያት የቅምአያቶቹ፣ የራሱም ትውልድ እርስት ይመለሳል የሚል ተስፋ እንጂ። በዚያ ላይ ደግሞ ብአዴን አለ፣ የአቢይ ሎሌ፣ አማራውን ክተት ብሎ የሚያዝለት። ስለዚህ አማራው ለወልቃይት፣ ለመተከል፣ ለጠለምትና ለራያ ሲል ዘመተ። ምን ያህሉ እንደተሰዋ ገና በውል አልታወቀም ። በውል የታወቀ ነገር ቢኖር አማራው መሃል የገባ የጭዳ ዶሮ እንደነበር ነው።
ጠ/ሚኒስትሩ እርስቶቹን በኦሮሙማ ፕርጀክት ሊውጡዋቸው ይሆን?
እነኝህ የአማራ እርስቶች ከትህነግ እጅ ተለቀቁ። ትግሬው የጨረሰውን ጨርሶ ወደቤቱ ወደትግራይ ፈረጠጠ። ወልቃይትም ራያም ሌሎችም እርስቶች ተለቀው ለመጀመሪያ ጊዜ በ 29 አመት ትግሬ አልባ አየር ተነፈሱ፣ በአማራው ልዩ ሃይልና በመከላከያው ትብብር። ለጥቆም እንግዲህ አማራው እልል ማለት ጀመረ አማራው “እርስታችን ተመለሰ” “እርስታችን ተመለሰ” እያለ።
የዋህ አማራ ጠ/ሚኒስትሩ ምን ያህል ነውረኛና ሃሰተኛ ሰው እንደሆኑ አላወቀም። የስራ መመሪያቸው ህዝብን ማገልገል ሳይሆን፣ ህዝብን እያታለሉና እየደለሉ በጥቃቅን ጊዜያዊ ቁጣ ማብረጃ ቀናቸውን የሚገፉ ስው እንደሆኑ አላወቀም።
ጉድ እኮ ነው!!! የአማራውን ግዛቶች ጠ/ሚኒስትሩ ለአማራው የማያስረክብበት ምክንያት ምንድነው? እንኩዋንስ አማራው ደሙን አፍስሶላቸው ይቅርና በጦርነቱ ባይሳተፍም እንኩዋ፣ መተከል፣ ራያ፣ጠገዴ ወልቃይት፣ ጠለምት የአማራ ግዛት የነበሩበት ጊዜ እኮ እንደትላንት ቅርብ ነው። በአለም መንግስታት የፀደቀ፣ ይፋ የሆነ ካርታ በየቤታቻችን አለ። ነው ወይስ ጠ/ሚኒስትሩ በአማራው ግዛቶች ቁማራቸውን ሊጫወቱ ነው??? ይሉኝታ፣ ሃጢአት፣ ነውር፣ ወንጀል የማያሳስባቸው፣ ያለቦታቸው የተቀመጡ በቀን ቅዠት ውስጥ የሚኖሩ ጠ/ሚኒስትር። መቼም ህዝብን በቀጥተኝነትና በሃቅ መምራትን አያውቁም። አቁዋራጭ፣ ሸፍጥና ውሸት የሚያዋጣቸው ይመስል
 ሴራና ስንፍና ከተጣመመ የወንጌል እምነት (የእምነት ቃል/Word of faith) ጋር የተላበሱ ጠ/ሚኒስትር
አሁን ላለንበት ጣጣ የተዳረግነው የእኚህ ሰው ስራቸውንና ቅደም ተከተልን አለማወቅ፣ ካላቸው ብልጣ ብልጥ የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ጋር ተደምሮ ባመጣው ምስቅልቅል ነው። ከመጀመሪያው ወደ ውጭ ከመሩዋሩዋጥ ይልቅ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉትን የላሉ ቁዋጠሮዎች ቢያጠብቁ ኖሮ ዛሬ እዚህ አንደርስም ነበር።
የጠ/ሚኒስትሩ ቁጥር አንድ አሰራር የጥፋት አካላትንና ወንጀለኞችን አቅፎ ከሁዋላ እየደግፉ ቆሻሻ ስራቸውን እንዲሰሩላቸው ማድረግ ነው። ትህነግ እሳቸው ስልጣን ከያዙ ጊዜ ጀምሮ በሰሜኑ አካባቢ ሲፉዋልል፣ ምሽግ ሲቆፍር፣ ሽብር ሲፈጥር ምንም ነገር አልተነፈሱም ነበር። ኦነግን ከነመሳሪያው ወደሃገሪቱ እንዲገባ ሲያደርጉ በአጋጣሚ አልነበረም። ጠ/ሚኒስትሩ ኦነግን በምን ሁኔታ እንደሚጠቀሙበት ከጠዋቱ ያውቁ ነበር።  ኦነግ ወደ 20 የሚቆጠር ባንክ ሲሰብር ራሱን ማደራጃና ማስታጠቂያ የሚሆነውን ራሽን እንዲያገኝ ተፈቅዶለት ነው። በባንክ ዘረፋው ሰሞን ከጠ/ሚኒስትሩ የተሰነዘረ ግሳፄ ወይም በኦነግ ላይ የተሰማራ ህግ አስከባሪ ነበር? እንድም ኮሽታ አልነበረም። ከዛም በሁዋላ ኦነግሸኔንና ቄሮን አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደዘረገፉት በኦህዴድ/ኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ፋይናንስ አድራጊነት ሽብራቸውን እንዲቀጥሉ ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩና አባሮቻቸው ናቸው። እሳቸው ቤተመንግስት ቀለም ያስቀባሉ፣ ኦነግ፣ኦነግሸኔና ቄሮ ከትህነግ ጋር ሆነው ወንጀላቸውን ይፈፅሙላቸውል። ደሞም ሴራው በደንብ ሰርቶአል ምክንያቱም ምንም እንኩዋ አሁን ጥያቄ ውስጥ ቢገባም የኖቤል ሰላም ተሸለሚ ሆነዋል።
ታዲያ አሁንም ህዋሃትንና ትህነግን ማጥፋት ቀርቶ በማይካድራው ጄኖሳይድ  እንኩዋን ተጠያቂ እንዲሆኑ በመንግስት ሚዲያዎች ስማቸውን ጠቅሰው እልወነጀሉዋቸውም። ምክንያቱም ለወደፊት ህዝብን እያሸበሩ ትኩረትን እንዲስቡላቸው ይፈልጉዋቸዋል። ጠ/ሚኒስትሩ በስራ አያምኑም፣ ሃላፊነትን በመውሰድ አያምኑም፣ የቃል እምነት እንደሚያስተምራቸው በመመኘትና በማውጠንጠን ነው አገርን ማስተዳደር የሚፈልጉት። ወንጀሎችን በህግ ማስወገድ እጅግ ያስፈራቸዋል። ስንት የኢሃደግ ወንጀለኞች እምባሳደሮች ሆነዋል። እነጌታቸው አሰፋን የመሳሰሉ ወንጀለኞች አሁን ድረስ ሳይነኩ ተቀምጠዋል።
ይህ ከወንጀለኞች ጋር፣ ከኢፍትሃዊነት ጋር ተለጥፎ የመስራት አባዜ በመንፈሳዊውም አለም እየተገበሩት ነው። ሃሰተኞች ነቢያትንና ሃዋሪያቶችን ከብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች ጋር ወጣቱን ሲበክሉ፣ ህዝቡን ሲዘርፉ፣ ጠ/ሚኒስትሩ ሽርካቸው ናቸው።  ጤናማዋን ቤተክርስትያንና እውነቱን እያፈረጡ ሃሰተኞቹን የመቅደስ ዘራፊዎች በመድረክ ቆመው በሃይለ ቃል ሲያወግዙ የቆዩ ሰባኪዋችን ከወሮበሎቹ ሃሰተኞች ጋር ያስታረቁ መሪ ናቸው። ካውንስል የተባለው ጉድ ለፖሊቲካ አጀንዳቸው ማስፈፀሚያ ምእመናንን አስሮ እግራቸው ስር እንዲጥልላቸው የተመሰረተ ኢወንጌላዊ አካል ነው። ለሳቸው አጀንዳ አስፈፃሚ ነው።
እንደ ሁልጊዜው እኚህ መሪ ያለ ትህነግ፣ ህዋሃት፣ ኦነግ፣ ኦነግሸኔዎችና ቄሮዎች መንቀሳቀስ አይችሉም። ስለዚህም ህዝብንና አገርን ለማስፈራሪያነትና ለትኩረት መሳቢያነት ይጠቀሙባቸዋል እንጅ አያጠፉዋቸውም።
ይብላኝ ለአምራው የማንም ቁማር ቺፕስ (Gambling Chips) ለሆነው። የማንም መወራረጃና መቆራቆዣ ለሆነው። 
አማራዎችና ፍትህ ፈላጊ ዜጎች የእነኝህን ሁለት ቀበጦች (ህዋሃትና ብልፅግና ፓርቲ) ማወናበድ ብዙ ትኩረት አትስጡት። የሚሰሩት አብረው ነው። የሚያስተሳስራቸው የጋራ ጠላታቸው አማራው ነው። ነገ በለቅሶና በይቅርታ እቅፍ ይተቃቀፋሉ።
አማራውን ከጨረሱት በሁዋላ እርስ በእርስ ይፋጫሉ። እስከዛው ግን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።
Filed in: Amharic