>

አንዳንድ ወዳጆቻችን 'ድርድድር ድርድር!" እያሉ ነው! (አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ)

አንዳንድ ወዳጆቻችን ‘ድርድድር ድርድር!” እያሉ ነው!

አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ

 

 
* በመሰረቱ ድርድር የሚጠላ ሃሳብ አይደለም!
አንዳንድ ቴክኒካሊ አስቸጋሪ ነገሮች ስላሉ ነው እንጂ!
የመጀመሪያው …ህወሃት የፌዴራል መንግስት የለም ብላ አቋም ይዛለች!ከዚህ አንጻር ህጋዊ ተደራዳሪ በኛ በኩል ማቅረብ አንችልም! የፌዴራል መንግስትም ህወሃትን አያውቃትም! በሁለት “ህገወጦች” ( እንደነሱ አጠራር አንደኛው የሌላኛውን ህጋዊነት በማይቀበልበት ሁኔታ) የሚደረገውም ስምምነት ትርጉም አይኖረውም! ድርድሩን ለመጀመር እንኳን መጀመሪያ የፌዴራል መንግስቱን መኖሩን አምና ይቅርታ ትጠይቅ..ቀጥላም የባለፈው የትግራይ ክልል ምርጫ ሙሉ በሙሉ እንደተሰረዘ እና እንዳልተካሄደ እንደሚቆጠር ይፋዊ መግለጫ ትስጥ….ከዛ …ወደ ሁለተኛው ሃሳብ እንሂድ
2ኛው..የሰሜን እዝን አባላትን እምሽክ አድርጋ የቀረጠፈችው ህወሃት እና 524 ለፍቶ አዳሪ ኢትዮጵያውያን በስለት እንዲታረዱ ትእዛዝ የሰጡ ባለስልጣናቶቿ በሀገሪቷ ህግ መሰረት የሚጠብቃቸው ትንሹ ፍርድ (ያውም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው: እድሜያቸው እና በትምህርታቸው አብዛኛው ያልገፉ እና ድግሪዎቻቸውም የግዢ መሆናቸው ወዘተ በቅጣት ማቅለያነት ከግምት ገብቶላቸው) የሚጠብቃቸው አነስተኛው ቅጣት ….ስቅላት ነው!
ምናልባትም ድርድሩ የስቅላቱን አፈጻጸም የሚመለከት ካልሆነ በቀር ትርጉምም ስለማይኖረው
3ኛው…መንግስት በሺ የሚቆጠሩ ወታደሮች እና ንጹሃን ከታረዱ በኋላ በየትኛውም አግባብ ህወሃቶችን አንጠልጥሎ ለፍርድ ሳያቀርብ ወደኋላ ልመለስ ቢል ህዝቡ የአራት ኪሎውን ቤተመንግስት ‘ማይካድራ ‘ እንደሚያደርግለትም ስለሚያውቅ…ድርድር የሚባለው ነገር አይታሰብም!
(በነገራችን ላይ የሰሜን እዙን ግፍ እና የማይካድራውን ሰቆቃ ከመስማቴ እና ከማረጋገጤ በፊት እኔም እንደ አብዛኛዎቹ እዚህ ፌስቡክ ላይ እንደምታይዋቸው የኦነግ እና የህወሃት ደጋፊዎች የድርድር አቀንቃኝ ነበርኩ!)
ድርድር የሚታሰብ ስላልሆነ ካአሁን ወዲያ ባታነሱት!
ዳይ ወደ ብሬኪንግ ኒውስ!
የሹክሹክታ ዜናችሁ ናፎቆኛል!በነገራችን ላይ ይሄ የ ብሬኪንግ ኒውስ ሙዳችሁን አልጠላሁትም! የአርሴናል ጎል በቫር ሲጸድቅ የሚሰማኝን አይነት ስሜት አለው! መጀመሪያ ጎል ሲገባ ትጨፍራለህ..አይ አልገባም ሲባል ትደነግጣለህ ..ከተወሰኑ ሰከንዶች በኋላ አይ ትክክል ነው ተብሎ ጎሉ ሲጸድቅም በድጋሚ ትጨፍራለህ!
የሳይበር ጀነራሎች ያሻችሁን ከተማ ቀድማችሁ ተቆጣጠሩ ..በማግስቱ መከላከያ መቆጣጠሩ አይቀርም!
ድል ለጀግኖቹ
Filed in: Amharic