>
5:26 pm - Sunday September 17, 3245

አስቴር ስዩም  በጀርባ ህመም እየተሰቃየች ነው...!!!  (ይድነቃቸው ከበደ)

አስቴር ስዩም  በጀርባ ህመም እየተሰቃየች ነው…!!! 

ይድነቃቸው ከበደ

አስቴር;/ ቀለብ ስዩም በወያኔ ዘመን ከፍተኛ ስቃይ ያየች  የፍትህ አርበኛ ናት ። የመጀመሪያ ልጇን አጥብታው ሳይጠግብ ታስራ ከ4 አመት እስር በኋላ በህዝብ ትግል ነፃ ወጥታ ነበር  አሁንም ሁለተኛ ልጇን ጥላ በግፍ መታሰሯ የዚህ መንግሥት ኢፍትሐዊ ፍርድ መገለጫ ነው።
    አስቴር ስዩም በህወሐት/ኢህአዲግ ዘመን በማዕከላዊ እና በቅሊንጦ በደረሰባት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት (ቶርች፣ ግርፋት፣ስቃይና በደል) ምክንያት የጀርባ ህመም የዲስክ ችግር ገጥሟት እንደነበር ይታወሳል፡፡
ዛሬም በቃሊቲ እስር ቤት የጀርባ ህመሟ አገርሽቶ ችግር ላይ ናት ። ህክምና እንድታገኝ የእስር ቤት አስተዳደሩን የጠየቀች ምላሽ አላገኘችም።
ባለቤቷ በለጠ ጌትነት በተደጋጋሚ እንደሚገልጸው አስቴር አሁን ላይ ህመሟ እየጸናባት እንደሆነ ገልጿል ።
የችግሩ አሳሳቢነት አስመልክቶ ፤ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ  አስቴር ስዬም አስቸኳይ  የህክምና  እንድታገኝ እንዲደረግ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ለሰብዓዊ መብት ጉባኤ ደብዳቤ መጻፉ ተገልጿል ።
    ♦ አስቴር በጀርባ ህመም እየተሰቃየች ነው ! ህክምና ትሻለች ፤ ይህ የህግ ጥያቄ ብቻ አይደለም ሰብዓዊነት ጭምር ነው !!!
አስቴር አሸባሪ አይደለችም። 
መጣ የተባለው እውነተኛ ለውጥ ከሆነ ንፁህ ታሳሪዎች የሰብአዊ  መብታቸው የሆነውን ህክምና የማግኘት መብታቸውን ተገፈው መንገላታት የለባቸውም!
Justice for አስቴር ስዩም አበራ
Filed in: Amharic