>

ጅራፍ ራሱ ዠልጦ  መልሶ ይጮሃል  (ታጠቅ መ ዙርጋ)

ጅራፍ ራሱ ዠልጦ  መልሶ ይጮሃል 

 

ታጠቅ መ ዙርጋ

 

 

 ትህነግ/ህወሃት በጠምንጃ አፈሙዝ  የአገራችንን ምድርና ሰማይ  በመቆጣጠር  ለ27 ዓመታት በቀጥታና በተዘዋዋሪ  በሕዝባችን ላይ ሲፈጽመው  የነበረውን ፦ 

– ፍጹም (አፈና፣ሰቆቃ ፣ኢፍትሃዊና ኢሰብአዊ ግፍና ደባ እንዲሁ አገር በቀል የዘር መድሎ ( homogeneous apartheid)

– በአማራው ፤በወልቃይቴው ፣በጋምቤላው ወዘተ.. ሕዝብ ላይ ያደረስውን ጭፍጨፋ 

–  መፈጠሬያቸውና መቀበርያቸውን ከሆነው -ከአያት ከቅድመ አያቶቻቸውን  ከወረሱትን  መሬታችው  አፈናቅሎ –  ለባለሃብት ትግሬዎችና ባዕዳን  (investors) መስጠትን

– ብዝበዛን፣ የሃብትና ንብረት ዘርፋን፣ የመሬት መቀራመርትን -ባጠቃላይ በኢትዮጵያውያን ላብ የተከማቸውንና የተፈጥሮ የሃብት ምንጫችንን በቁጥጥሩ ሥር አውሎ እንድፈለገው ማድረግን ወዘተ.. በተመለከተ ፤

( ለመቃወማ ፣ ለማውገዝ፣ ለሰብአዊ መብት ተማጋች ድርጅቶችና በዲምክራሲያዊ  ሥርዓት ለሚተዳደሩ  መንግሥታት ለማሰማት) ስንሰለፍና እንደቁራ ስንጮህ ተጋሮች   አብረውን አልተሰለፉም፣ አብረውን አልጮሁም ። 

እኔ በኖርኩበት አካባቢ ክሁለትና ሶስት የማይበልጡ ተጋሮች  በተወሰኑ የተቃሞ ሰልፎች መገኘታቸውን አስታውሳለህ ። ከዚህ ውጪ- እንኳንስ ተቃውመው  ሊወጡ ፤ ለምን ተቃወማችሁ በማለት የተቃውሞ ተቃውሞ  ሰልፍ ይወጡ ነበር ።

ዛሬ  መርዮቻችን የሚልዋቸው ቅጥረኛ ጋንግስተሮች – ዳርድንበራችንን በመጠበቅ የሃገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር አገልግሎት ላይ የነበሩትን – በተለይም የትግራይ ሕዝብ ሲንከባከቡ በነበሩትን በመከላኬያ አባላት ላይ-የፈጸሙትን ግፍና ክህደት ፤ በዓለም  የሰው ልጅ ታሪክ ተደርጎና ተሰምቶ  የማይታወቅ እንግዳ ነገር ነው ። ድርጊቱ -ወፈፌዊ፣ንውጻዊ፣ ጽሉላዊ ወዘተ..ማለት (psychopathic act)  ነው ።

ተጋሮች በየባዕዳን አገራት ዋና ከተማ  የሚያደርጓቸው ሰልፎች  – ለመግለጽ ቃላት ያጣንለትን  ዘግናኝ አይስሳዊ እርድ -ለማውገዝና ሃዘናቸውን ለመግለጽ መሆን  ነበረበት። በሰልፎቹ  የሚያሰሟቸው   መፈክሮች  ሲታዩና  ሲደመጡ  ድርጊቱን ከማውገዝ በተጻራሪ ነው። ጎሽ እንኳን አደረጋችሁት የሚል  አጽናዎት  ይመስላል   

 ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ መልሶ  መግዛት ወይም ማጥፋት ወይም እኛ መጥፋት በማለት  ቅጥረኛውና  ጸረ-ኢትዮጵያው  ትህነግ  የከፈተውን  ጦርነት ለመከላከል ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማድረግ ላይ ያለውን፤  አማራጭ የሌለውና ፍትሃዊ ጦርነት (just war) ለመቃወምና ለማውገዝ ነው አደባባይ የሚወጡት ።  አሳፋሪና  ጅራፍ ራሱ ዠልጦ -መልሶ ይጮሃል አይሆንምን?  

በሰልፎቹ ከሚያሰሟቸው  መፈክሮች አንዱ ፦  የትህነግ መሪዮች ‘የፈለጉትን ደባ ፈጽመው ኢትዮጵያን ካልገዙ ፣ከሕግ ተጠያቂነት ነጻ እስካልሆኑ ፣ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ  ላይ እንደፈለጉ ካልጋለቡ  ወዘተ..’ ኢትዮጵያ የተጋሮች አገር  እንዳልሆነ’ ነው የመፈክራቸው  ዝንባሌ/ቃና ።

የጉራጌ ብሄረሰብ “በርቸ የስራብኽ” ይላል ። ይህ ማለት የሥራህን ይስጥህ ፣ጡር ይድረሰብህ ወዘተርፈ ማለት ነው ። አገርና ሕዝብ ወዳድ ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን  የህወሃትን/ትህነግን አፈና፣ ጭቆና፣ግፍ፣ኢፍትህ፣ ብዝበዛ ወዘተ.. በመቃወም   ለ27 ዓመታት የጮኽንባቸው አደባባዮች ፤ ዛሬ በተጋሮች ተተክቷል ። ይህ ማለት በርቸ ደርሶባቸው  ውይም  የሥራቸውን አግኝተው  እየተንጫጩ  ነው ። በሌላ አነጋገር ለሁሉም ነገር ግዜ ስላለው ፤ ግዜ እየመሰከረ ነው ።

  

የአእምሮ ንውጻዊነት/ጽሉላዊነት የጋራ ምልክቶች (Common signs of psychopathy) የሚከተሉት ናችው፦

0 . socially irresponsible behavior

 1. disregarding or violating the rights of others
 2. inability to distinguish between right and wrong

0 difficulty with showing remorse or empathy

 1. tendency to lie often
 2. manipulating and hurting others
 3. recurring problems with the law
 4. general disregard towards safety and responsibility

የአማርኛ ትርጉማቸው ፦

 • ለማኅበረሰብ ሃላፊነት የጎደለው ባህሪ ወይም ፀረ-ማኅበረሰብ ባህሪ
 • የሌሎችን መብት የማያከብር ፣የሚጋፋ፣ የሚጥስ ወዘተ..
 • የትክክለኛና የኢ-ትክክለኛ ልዩነት መለየት የማይችል
 • ጸጸት ፣ ሃዘኔት፣ የኅሊና ወቀሳ  ወዘተ.. የማይሰማውና ጨካኝ ማንነት ያለው
 • አዘወትሮ የመዋሽት ዝንባሌ ያለው
 • የሰዎችን አእምሮ ተቆጣጥሮ ወይም አሳስቶ በሰዎች ላይ የሚጠቀምና ስዎችን የሚጎዳ
 • በተደጋጋሚ ሕግ የመጣስ ችግር ያለበት
 • ስለራሳቸውም ሆነ ስለሎች ደኅንነትና ሃላፊነት ከቶ አይሰማቸውም /ግድየላቸውም

ከነዚህ ውስጥ የወያኔዎች ግላዊና ቡድናዊ ስብዕና ማንነት (individual and collective personality) የማንጸባርቅ/የማይወክል ነጥብ  አለን? እኔ አመለካከት ከላይ ተጠቀሱትን ሁሉ_የትህነግ/የህወሃት/የወያኔ  ባህሪያት  ያንጸባርቃሉ ። ንውጻዊ (psychopathic) አእምሮኖ ያላቸው ። በዚህ ዓይነት ንውጻዊ  አእምሮ (insane state of mind) ነው – የአገር መከላኬያ ሃይል  አባላትን እንደ ቄራ ከብት ያረዷቸው ፡፡

 

Filed in: Amharic