>

"የኢትዮጵያ ልሂቃን፣ ጥልቅ ፍርሃት እና የአድር ባይነት ባህል" ያሬድ ሀይለማርያም

“የኢትዮጵያ ልሂቃን፣ ጥልቅ ፍርሃት እና የአድር ባይነት ባህል”

ያሬድ ሀይለማርያም

 አጠር ያለ ትዝብቴን ልጽፍ አሰብኩና ነገርየው በአጭር ጽሑፍ እንደማይቋጭ ሳስብ ስንፍና ተሰማኝ። ሰለዚህ ነገሩን ወደ ጥያቄ መንዝሬ ሕዝብ እንዲወያይበት ወደድኩ፤
1.  ልሂቃን በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ተውጠው ያሰቡትን መተንፈስ ይቅርና በነጻነት ማሰብንም ጭምር የሚፈሩ ከሆነ፣
2. ልሂቅ የሚባለው የማህበረሰብ ክፍል የመስሎ አዳሪነት ወይም የአድር ባይነት ባህሪን ከተላበሰ፣
3. ልሂቃን ለእውነት፣ ለፍትህ እና ለርትህ ጀርባቸውን ሰጥተው ቁርጥ ቀን ሲመጣ የሹም ጭራ ከሆኑ፣
አገር ምን ተሰፉ ይኖራታል? ነጻ ያልወጣ ልሂቅ ነጻ አገር ይፈጥራል ወይ?
ትርጉም፤ ልሂቅ የሚለው መገለጫ የጏይማኖት አባቶችን፣ ፖለቲከኞችን፣ ምሁራንን፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ሹማምንት፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዬች፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች፣ ማህበረሰብ አንቂዎች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ ወዘተ… ያካትታል።
እስኪ እንወያይበት።
Filed in: Amharic