.
ምዕራፍ አንድ
:
በመጀመሪያ ደደቢት የሚባል በረሃ ነበረ:: በረሃውም ህወሓት የተባሉ ጭራቆችን አበቀለ:: ጭራቆቹም ቀንጠብቀው አዲስ አበባ ገቡ:: እነሆም ቤተመንግሥቱ ባዶ ነበረና ያለከልካይ በዙፋኑ ላይ ሠፈሩበት::
በሥልጣናቸው መጀመሪያ ወራት “በኢትዮጵያ ምድር በጎሳ እና በነገድ የተሸነሸኑ #ክልሎች ይሁኑ” አሉ:: እነሆ እንዳሉትም ሆነ:: ህዝቡም በየነገዱ ተቧደነ:: “እሸሸግበት ጎሳ እቧደንበት መንደር የለኝም” ያሉትን ዜጎች እስከምድር ዳርቻ አሳደዱ:: “ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚል የህገር ሰው እትብቱ በተቀበረባት ምድር ባይተዋር እና መጻተኛ ሆነ::
_______________________
የህወሓቶ ጭፍሮች ሰዉን ሳያፍሩ ፈጣሪንም ሳይፈሩ የሀገሪቱን ሀብት ተናጠቁት:: ህዝቡንም እነርሱ ሲበሉ ከደጅ ቆሞ እንዲቁለጨለጭ ፈረዱበት:: ሆዳቸው ሞልቶ ደረታቸው ቀልቶ ጥጋባቸውን አላስችል ባላቸው ጊዜ በሜዳ እና በየሸንተረሩ ያገሱ ዘንድ ወጡ:: ህዝቡንም “የግሳታችንን ድምጽ ትሰሙ ዘንድ ሰልፍ ውጡ” ሲሉ አዘዙ::
የተገዳደሯቸውን ጎበዛዝቱን እጅ እና እግራቸውን አስረው ሽንታቸውን ሸኑባችው:: ወይዛዝርቱን በማህጸናቸው የጋለ ብረት ሰደዱባቸው:: እርጉዞች አስወረዱ:: አዛውንቶች ተዋረዱ:: ይብስ ብለውም ከቅዱሱ መቅደስ ካባና አክሊል አስወጥተው ተጎናጽፈው በአደባባይ ተሰላቁ!
_______________________
የደጋጎች ምድር በሆነችው ኢትዮጵያ የግፉ ጽዋው ሞልቶ በፈሰሰ ጊዜ ከመከራው ጽናት የተነሳ የህዝቡ አምርሮ ወደፈጣሪው አለቀሰ:: እንባውንም ከደመና በላይ ወደመንበረ ጸባኦት ረጨ::
_______________________
የህወሓቶች የዘመናቸው ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ፈጣሪ የቁጣውን በትር አነሳ:: ኃያላኑን አዋረዳቸው:: ከዙፋናቸውም ገለባበጣቸው:: እነርሱ ግን ከፈጣሪ ጋር ይገዳደሩ እና ዙፋናቸውን ያጸኑላቸው ዘንድ #ሸኔ #አባቶርቤ #ሄጎ እና #ሳምሪ የተባሉ የሰይጣን ግልገሎችን ሲኦል ውስጥ እስፈልፍለው የመርዝ ጡት እያጠቡ አሳደጉ:: ህዝቡን ይፈጁላቸው ዘንድ በሠፈሮች እና በመንደሮች አሠማሩአቸው:: እንዳሉትም ሆነ::
_______________________
ፈጣሪ የህዝቡን እንባ ያብስ ዘንድ የቅዱሳንን ጸሎት ሰምቷልና የግፈኞች ጀንበር አዘቀዘቀችባቸው:: የግፋቸው ጽዋ ሞልቶ ፈስሶ ነበርና ፈጣሪ ሀብታቸውን ቅጠል ጉልበታቸው ቄጤማ ዐይናቸውም ጨለማ አደረገ:: እነሆም ከዙፋን ወደ አመድ አወረዳቸው:: ሎሌዎቻቸውን አሰለጠነባቸው:: ከጌትነት ወርደው በሚጠሏት ምድር በኢትዮጵያ ተቅበዝባዦች ሆኑ::
እነሆም ከሰማይ ከተወረወረችው የፈጣሪ የቁጣ ሰይፍ ይሸሸጉ ዘንድ ወደጥንተ በአታቸው ተመልሰው በቀበሮ ጉድጉዋድ ውስጥ ተሸሸጉ:: ፍጻሜያቸውንም በጭንቀት እና በሰቀቀን ይጠባበቁ ጀመር….
:
ምዕራፍ ሁሉት …….