ወቅታዊ የአቋም መግለጫ…
አሳዬ ደርቤ
እንደተደረገብን ግፍ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያንም ሆነ የፌደራል መንግሥቱን መካድ የነበረብን እኛ ነበርን፡፡
ግን ያንን ለማድረግ አስተዳደጋችንም ሆነ ኅሊናችን ስለማይፈቅድልን የአገር ደጀን ሆነን ተገኘን፡፡
.
ሲቀጥል ደግሞ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት ጋር እኩልነትን ይዞ ወደ አራት ኪሎ ለገባ መሪ ሁሉ ምቾት እንጂ ሥጋት የምንፈጥር ሕዝቦች አይደለንም፡፡
እኩልነታችን እስካልነፈግከን ድረስ ሲዳማ ሁን፣ ኦሮሞ ሁን፣ ትግሬ ሁን፣ አፋር ሁን ግድ አይሰጠንም፡፡ ‹‹የአገራችን ብርቅዬ መሪ›› ብለን እንዘምርልኻለን፡፡
ምክንያቱም የሥልጣን ጥያቄ በእኛ ዘንድ እጅግ ትንሹ ጥያቄ በመሆኑ ‹‹አማራ ያልመራት አገር ጥንቅር ብላ ትቅር›› የሚል አስተሳሰብ የለንም፡፡
.
ከዚህ ባለፈ ግን በእነ ሽመልስ አብደሳ ፉከራ የምንሰበርበት፣ በአዲሱ አረጋ የፌስቡክ ፖስት የምንበረግግበት፣ በቁማርተኞች ሤራ የምንገደልበት ዘመን አብቅቷል፡፡
የአማራ ብልጽግናም የወመኔ ባለሥልጣናትን ትፋት ማስተባበል ሰልችቶት በግልጽ አማርኛ “ተጠንቀቁ” ማለት ጀምሯል፡፡ እኛም በዚህ አቋሙ እስከቀጠለ ድረስ ተገቢውን ድጋፍ ልንቸረው ተዘጋጅተናል፡፡
ይሄው ነው❗️
‹‹ሐቀኛ ፌደራሊዝምን እውን እናደርጋለን›› እያሉ “ተወካይ” ለሚያስፈልጋቸው ሕዝቦች “ገዳይ” መማቻቸት ከህውሓት ጋር አብሮ ተቀብሯል፡፡ በእከሌ መከፋት እከሌን ማስደሰት፣ በአማራ ሞት የኢትዮጵያን ቀጣይነት ማረጋገጥ አብቅቶበታል፡፡
በተረፈ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እንጂ “ምክትል” የሚባል ሕዝብ የለም፡፡ ‹‹እኩል›› እንጂ!