አማራን ከምድረ-ገፅ የማጥፋት ፕሮዤው መቼም አይሳካም!
ታየ ቦጋለ አረጋ
* በዘረኛ ጭንቅላትህ ነቅዘህ፦ ለኦሮሞ ገበሬዎች ሲሆን ካሳ ኮንዶሚኒየም መሬቱ ተነጠቀ… ኡኡኡኡኡ! ብሎ የጮኸ አንደበትህን እያደነቅሁ
Vs.
ተገለባብጠህ ለራያ ወልቃይት እና ጠለምት ሲሆን… እየተያዘ ያለ የሚያቅለሸልሽ ፀረ-አማራ የማስታወክ አቋምህ አልተገናኝቶም። ያቅለሸልሸኛል።
(Double standard at its best) ያሳቅቃል!
–
* አይሁዶችን ለናዚዎች፣ ቱትሲዎችን ለሁቱዎች፣ አማራዎችን ለወያኔ ገዳዮች በድጋሚ አሳልፎ ለመስጠት በማሴር ስለፍትሀዊነት ማውራት አይቻልም!
እኔ ታየ ቦጋለ፦ ለኦሮሞ ገበሬ በአደባባይ ያውም ሰው በሚገደልበት በዚያ ክፉ ወቅት፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስከ ሸራተን ተሟግቻለሁ።)
–
የአማራ ሲሆን፦ መርህ፣ ምክንያት፣ ህግ ገለመሌ ትላለህ። መጀመሪያ አማራ መሬቱን የተነጠቀው በመርህ ነው ወይ?!
ጣሊያን ለአምስት ዓመታት የተወሰኑ የኢትዮጵያ መሬቶችን ያዘ፤ በኋላ በአርበኞች ተጋድሎ ለቀቀ።
ትህነግ በጉልበት የአማራን መሬቶች ለሠላሳ አመት ያህል ይዞ፤ ከጣሊያን ይቅርና ከናዚ የማይነፃፀር አረመኔያዊነት ፈፀመ። አማራ በተጋድሎ ርስቱን አስመለሰ። ይኸው ነው!
“የአማራ መሬት ትግራይ እንጂ ኡጋንዳ አልሄደም” ለምትሉ፦
የአማራ መሬት ለአማራ ተመለሰ እንጂ ኢራቅ አልሄደም ብንላችሁ መልሳችሁ ምንድነው?
“መሬቱን እንጂ ሰዉን አልፈለጋችሁም” ለምትሉ፦ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል አሉ። መሬቱን እንጂ ሰዉን ስላልፈለጋችሁማ፦
500,000 አማራ ከመሬቱ ነቀላችሁ።
በአስር ሺዎች በጅምላ ጨፍጭፋችሁ ገደላችሁ።
አሁን እንኳ፦ ማይካድራ ሁመራ…
በቋንቋህ አትማር አትዳኝ አትተዳደር አላችሁ።
የእርሻ መሬቱን ለትህነግ (TPLF) አባላት ሸንሽናችሁ አደላችሁ ወዘተርፈ ስንት ትግሬ ነው አማራ ክልል ተከብሮ የሚኖረው? በአስርሺዎች።
ታዲያ መሬቱን እንጂ ሰዉን የማይፈልገው ማነው? ንገሩን ባዮች።
መከላከያን ጭምር አረዳችሁ። እና እንደገና ለማረድ መጥታችሁ ታስተዳድሩት?!
ራያ ወልቃይት እና ጠለምት 30 ዓመታት የተፈናቀለው ተመልሶ ራሱ በመረጠው ይተዳደራል። ባሻው ቋንቋ ይማራል ይዳኛል… ፌደራሊዝሙም ቢሆን የሚለው ይህንን ነው።
ለመሆኑ በጉልበትና በገደላ እንጂ በህገመንግሥት የተወሰደ መሬት ታሳዩኛላችሁን?!
ሁለት ፖስቶች ጨምሬያለሁ፤ እስከወዲያኛው ደህና ሁኑ ።
አይሁዶችን ለናዚዎች፣ ቱትሲዎችን ለሁቱዎች፣ አማራዎችን ለወያኔ ገዳዮች በድጋሚ አሳልፎ ለመስጠት በማሴር ስለፍትሀዊነት ማውራት አይቻልም!
አማራን ከምድረ-ገፅ የማጥፋት ፕሮዤው መቼም አይሳካም! አማራ ነህ ካልኸኝ ባምር ምን ይከፋኛል። አማራነት ከእነማን በስተግርጌ ነው?
ሁሉም የሰው ዘር እኩልና ኢትዮጵያውያን አንድና ያው ነን። ታየን አሸማቅቃለሁ ከማለት ሸምቀቆ ሠርተህ፤ በሺልንግ ገመድ ብትሸመቀቅ ይቀልሀል።