>

ኦነግ ሸኔ በዘመቻ እንጂ በእርግማን አይጠፋም...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ኦነግ ሸኔ በዘመቻ እንጂ በእርግማን አይጠፋም…!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

 *…. ለሸኔ የቄስም የሼክም የፓስተርም ምክር፣ የአባ ገዳም እርግማን አይጠቅመውም። ይልቅ ያሰለጠንከውን ወታደር ዝሙቱን አስትተህ ተነሥተህ ዝመት በለው። አዘምተው እንጂ አታዘሙተው። ዝሙት የወታደር ወኔ ይሰልባል። ጠላት ከፊትለፊትና ከጀርባ አስቀምጦ የምን መርመጥመጥ ኖ?!?
~ ይሄም የወንድም ምክር ነው።
•••
በየትኛው ዓለም አማፂ፣ አመጠኛ፣ ሽፍታ፣ ወንበዴ፣ ነፍሰ ገዳይ፣ ዘራፊ፣ አሸበርቲ፣ በእርግማን አይጠፋም። በኢትዮጵያችን እያየነው ያለው ግን ኢንዴዢያ ነው። ኦነግን ለማጥፋት በአባ ገዳዎች ማስረገም ነው የተያዘው። ኦነግ በእርግማን አይጠፋም። አከተመ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ግማሽ ሚሊዮን ወታደር አሰልጥኖና አስመርቆ ታይቷል። ታዲያ ይሄ ነፍ መኪና ጭምር የተበረከተለት፣ በዘመናዊ መሣሪያ የተሟላ ሰልጣኝ ምሩቅ ወታደር ኦነግ ሸኔን ይገጥሙ ዘንድ፣ ወይ ደግሞ ከህወሓት ጦር ጋር ይገጥም ዘንድ መላክ ሲገባው ኦቦ ሽመልስ  ተመራቂ ሠራዊቱን የት እንደከተው ዋቃ ብቻ ነው የሚያውቀው። ከምር የት ገቡ ግን?
… ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሜዲያኑ የሽመልስ አብዲሳ የቲያትርና የቁማር ቡድን ኦነግ ሸኔ በጦርነት አይጠፋም፣ አይደመሰስም የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ይመስላል ሸኔን ለማጥፋት “ እርግማንን” እንደ አንድ የትግል አማራጭ መጠቀሙን ይፋ አድርጓል። በአዲሱ የእነ ሽሜ ግኝት መሠረት ኦነግ ሸኔ የሚጠፋው በጦርነት ሳይሆን በኦሮሞ አባ ገዳዎች እርግማን ነው ብለው ሳያምኑ አልቀሩም።
•••
ህወሓትን በጦርነት፣ ፋኖን በጥይት፣ የዐማራ ልዩ ኃይልን በፍጅት ሲያሳድድ የከረመው የእነ ሽሜ የቁማርተኞች ቡድን የኦሮሚያዎቹን ሽፍታ ወንድሞቻቸውን ለማጥፋት ከጦርነት ይልቅ “ የአባ ገዳ ምክር፣ ቁጣና እርግማን” የተሻለና ተመራጮች ሆነው ተገኝተዋል እያሉን ነው። ኦቦሌሶ ኦነግ ሸኔ በእርግማን ሳይሆን በ “ጠብ-መንጃ” ነው የሚጠፋው። አለቀ።
•••
አንዱ ጨርቄን ማቄን ሳይል ለሃገሩ፣ ለዳር ድንበሩ ይዘምታል። ሌላው ደግሞ በየጫካው ሥራ ፈትቶ ይዘሙታል”። አንዱ በየበረሃው ለሃገሩ ደሙንና ላቡን ያፈሳል ሌላው ደግሞ በየጫካው በየመንደሩ ዘሩን ያፈሳል። ጎበዝ ዝሙት እና ዝመት እየለየን እንጂ፣ ዝ መሞቻና ዘ መቻ እኮ አንድ አይደሉም። ዝመት እንጂ ዘሙት አይደለም የተባለው እኮ። ለማንኛውም እርግማን የሽፍታና ወንበዴን ቅስም አይሰብርም፣ አያስወግድምም። ለወንበዴና ለሽፍታ ለአሸባሪ ምሱ ጠብ መንጃ ብቻ ነው። እሱ ነው ወገብ ዛላውን ሰብሮ ቀንጥሶ ድራሽ አባቱን የሚያጠፋው። እናም ከአባ ገዳ እርግማን ይልቅ የአባ ዳኘውን ጠብ መንጃ ብትሞክሩት ይሻላል ባይ ነኝ።
•••
ሌላው ደግሞ የጠቅላያችን ድሮን ከምን እንደደረሰች ባውቅ ብረዳ መልካም ነበር። ድሮኗ ከትግራይ ሜዳና ተራራ በቀር የወለጋና የጉጄ ጫካ አይታያትም፣ ዳፍንቷ ይነሣባታል የሚባለው ነገርስ ምን ያህል እውነት ነው። ስዩም ተሾመ በዚህ ዙሪያ ከሞሳድ የበለጠ ምርምር ያደረገ ይመስላልና ስለ ድሮኗ ማብራሪያ ቢሰጥበት መልካም ነው የሚሉም አሉ። ደፂን እየተከታተልንባት ነው የተባለችው ድሮን የት እንደደረሰች ሳይታወቅ እነ ደፂ ሰብረነዋል ባሉት የዐማራ ፋኖ፣ የዐማራ ልዩ ኃይልና የዐማራ ሚኒሻ እጅ ገብተው ሁለቱንም ጉድ ሳይሠሯቸው አይቀሩም። ዐማራ ተራራው ድሮኗን ጉድ ሠራት እያሉ መከላከያዎች ራሱ እየተደመሙ ነው ተብሏል።
•••
ለማንኛውም እርግማኑን ትተህ ዐዋጅ ዐውጅ። ሸኔን ለመደምሰስ መፍትሄው አባ ዳኘው እንጂ፣ አባ ውቃው እንጂ አባ ገዳ አይደለም። ለሸኔ የቄስም የሼክም የፓስተርም ምክር፣ የአባ ገዳም እርግማን አይጠቅመውም። ይልቅ ያሰለጠንከውን ወታደር ዝሙቱን አስትተህ ተነሥተህ ዝመት በለው። አዘምተው እንጂ አታዘሙተው። ዝሙት የወታደር ወኔ ይሰልባል። ጠላት ከፊትለፊትና ከጀርባ አስቀምጦ የምን መርመጥመጥ ኖ።
… ለአሁን አበቃሁ ካነሰ እያየሁ እጨምራለሁ !!
•••
ሻሎም !   ሰላም !   
ህዳር 28/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic