>

አሐዳዊ ሥርዓት አራማጆቹ  እነማን ነበሩ? (አቻምየለህ ታምሩ)

አሐዳዊ ሥርዓት አራማጆቹ  እነማን ነበሩ?

አቻምየለህ ታምሩ

አነ ታዬ ደንደአ አራዶ እና አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ሰልቃጩን ኦሮሙማን የፌዴራላዊ ሥርዓት ተምሳሌት፤ የዚህ እሳቤ ፈረሰኞችን ደግሞ የፌደራል ሥርዓት መምህሮች አድርገው ለማቅረብ እየቃጣቸው ይገኛል። በተቃራኒው ደግሞ አማራውን የአሐዳዊ ሥርዓት መገለጫ አድርገው ያጠይሙታል።
መሬት ላይ ያለውና የነበረው እውነት ግን በተቃራኒው ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ  በመላው ኢትዮጵያ እጅግ ፍጹም የሆነ አሐዳዊ ሥርዓት ያስተዋወቁት የኦሮሞ ተወላጅ የኢትዮጵያ መሪዎች ነበሩ። ይህም የሆነው በደርግ ዘመን ነበር። ለዚህ ማስረጃ የሚሻ ቢኖር መስከረም 2 ቀን 1980 ዓ.ም. የታወጀውን የኢሕድሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 4 ይመለከት። በደርግ ዘመን 17 ዓመታት ሙሉ በኢትዮጵያ ላይ የተጫነውን ደፍጣጭ አሐዳዊ ሥርዓት ተጀምሮ እስኪጨረስ ይመሩት የነበሩት የኢትዮጵያ ገዢዎች በሙሉ የኦሮሞ መኮንኖች ነበሩ።
ከታች በቪዲዮ የምትመለከቷቸው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንቶች በሙሉ  በደርግ ዘመን 17ቱን ዓመታት ሙሉ  እስከ ቀበሌ  ድረስ የሚገዙበት አሐዳዊ ሥርዓት ዘርግተው ሲገዘግዙ የነበሩ የኦሮሞ ተወላጅ የኢትዮጵያ ገዢዎች ነበሩ።
በቪዲዮ ቅንብሩ በመጀመሪያ ላይ ሲናገሩ የሚሰሙት ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ሲሆኑ ከ1967 ዓ.ም. – ጥር 26 ቀን 1969 ዓ.ም. ድረስ  ኢትዮጵያን  በፕሬዝደንትነት የገዙ አሐዳዊ መሪ ነበሩ። አሐዳዊው የኢትዮጵያ መሪ ጀኔራል ተፈሪ በንቲ ኦሮሞ ናቸው።
ሁለተኛው  ሲናገር የሚታየውና የሚደመጠው ሊቀመንበር መንግሥት ኃይለ ማርያም ወልዴ አያና ነው። ሊቀመንበር መንግሥቱ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት የነበረው ከጥር 26 ቀን 1969 ዓ.ም. – ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም.  ሲሆን እንደ ጄኔራል ተፈሪ ሁሉ  መንግሥቱም ኦሮሞ ነው።  ከኦሮሞ ቤተሰብ ስለመወለዱ ራሱም በድምጹ ያረጋግጣል።
የመጨረሻው  ላይ ሲናገር የሚታየው የደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ጄኔራል ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ገመዳ ሲሆን አሐዳዊው ጄኔራል ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ገመዳ የኢትዮጵያ ፕሬዝደትን የነበረው ሊቀመንበር መንግሥቱ ከአገር ከኮበለለበት ከግንቦት 13 ቀን – ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ነበር። ወያኔን ሻዕብያን ተከትሎ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሲገባ ጀኔራል ተስፋዬ ጣሊያን ኢምባሲ ጥገኝነት ጠይቆ እስከ ሕይወቱ ዘመን ፍጻሜ ድረስ የኖረው አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ነው።
አንግዲህ! የደርግ ዘመን ተጀምሮ እስኪጨረስ ድረስ እጅግ የተማከለ ወይም ፍጹም የሆነ አምባገነናዊ አሐዳዊ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ያስተዋወቁትና  17 ዓመታት ሙሉ በዘረጉት አሐዳዊ ሥርዓት እስከ ቀበሌ ድረስ ይገዙ የነበሩ አሐዳውያን መሪዎች ኦሮሞዎች ሆነው ሳለ ነው እነ ታዬና አዲሱ አማራን የአሐዳዊ ሥርዓት መገለጫ ፤  ኦሮሞን ደግሞ የፌደራላዊ ሥርዓት አምሳያ  አድረገው ሊያቀርቡ የሚቃጣቸው።
______________
በቀጣይ ክፍል ከደርግ ዘመን በኋላ በመንግሥትነት የተሰየመው ሰልቃጩ ኦሮሙማ ስለዘረጋው   እጅግ የተማከለውአሐዳዊው የአፓርታይድ አገዛዝ እና አሐዳዊ  አድርገው የሚያቀርቡት አማራ ስለዘረጋዊ ፍትሐዊ ፌደራላዊ ሥርዓት እጽፋለሁ።
Filed in: Amharic