>

ተራራው ዐማራ ሆዬ - ስማኝማ ልንገርህ ...!!!   (ዘመድኩን በቀለ)

ተራራው ዐማራ ሆዬ – ስማኝማ ልንገርህ …!!!

  ዘመድኩን በቀለ

 

•  “ እንደ ንስርም እንደ አንበሳም ሁን ”
#ETHIOPIA |~ የወዳጅ ምክር ነው።
•••
አሁን ስለ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ራያና ሁመራ ያለቀ፣ የተከተተ፣ ፋይሉ የተዘጋ ጉዳይ ማውራቱን፣ ማውጋቱን ትተህ ስለ ቀጣዩ አጀንዳና የቤት ሥራ ብታወራ፣ ብታወጋ፣ ብትመክር፣ ብትዘክር ይሻልሃል ባይ ነኝ። “የሞተ ዘመድ የለህም እንዴ? ” ትል የለ እንዴ ስትተርት። አበቃ፣ ሞተ፣ ተከተተ። የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን።
•••
ይልቅ አሁን ትክ ብዬ ሳየው በድኑ ብአዴን ራሱ ድልህን ዓይቶ፣ ነቃ ቀስቀስም ያለ፣ የወንድ ሱሪ፣ የጀግና የፋኖ ቁምጣም የታጠቀ፣ ቀበቶውንም ያጠበቀም ነፍጠኛ አባቶቹን የመሰለ፣ ግርድና አሽከርነቱን የተወም ይመስላል። የሆነ ነገሩ ወንድ ወንድ የመሽተት ምልክትም አሳይቷል። እናም ብአዴንን ከማስደንበር ማጀገን፣ ከጎኑ መቆም፣ ስንቅና ትጥቅ፣ ወኔም ሞራልም ጭምር መስጠት ያስፈልጋል ባይ ነኝ። የሰሞኑን ብአዴን ያየ ብአዴን አዴፓን አሁን ላይ አይሰድብም። አያዋርድም። እናም አትሞኙ ብአዴንን ዐማራ አድርጉት። በስሱ አጨብጭቡለት፣ አፏጩለት፣ አይዞኝ አለንልህ ከጎንህ ነን በሉት። ሰድባችሁ ለሰዳቢ አትስጡት። ከኦነግ ከኢዜማና ከገገማ እኩል አብራችሁ አትስደቡት። ይሄን አበክራችሁ ሥሩበት።
•••
ሕገ መንግሥት ተብዬው የህወሓት ሰነድ ዐማራውን አያውቀውም። ዐማራውም ሕገ መንግሥቱን አያውቀውም። ሕገ መንግሥቱ ላይ የተወያዩት፣ ያጸደቁት፣ ትግሬዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ሲዳማዎች ወዘተ ናቸው። ዐማራ በውይይቱ አልተጠራም፣ አልተወከለም። አልተጋበዘም። ጉራጌው ታምራት ላይኔ፣ ኤርትራዊው በረከት ስምኦን፣ ሲዳማው ተፈራ ዋልዋ፣ ትግሬው አዲሱ ለገሰ፣ ዐማራን አይወክሉም። እናም ዐማራው በማያውቀው ሕገ መንግሥት ስር እስከዛሬ ድረስ ኢትዮጵያን ብሎ በጨዋነት ተገዝቷል፣ ተረግጧል፣ ተወግሯል፣ ዘሩ ጠፍቷል፣ ተፈናቅሏል፣ ተሰዷል፣ ተዘርፏል፣ ተገድሏል፣ ማንነቱቱን፣ ርስቱን፣ መሬቱን፣ ንብረቱን፣ እርሻውን ተቀምቷል። እናም ዐማራው ስለ ሕገ መንግሥቱ አያገባውም። አይመለከተውም። ጧ በል።
•••
በመጨረሻም ከ27 ዓመት በኋላ ሕገ መንግሥት ብላ የራሷን ሰነድ ለኢትዮጵያውያን ያስረከበችው ሕወሓትን በምሥራቅም፣ በምዕራብም፣ በሰሜን ዐማራም  ጭምር የዐማራ ልጆች ገርፈው፣ ገርፈው፣ ለብልበው አይቀጡ ቅጣትም ቀጥተው ዓለሙ ሁሉ እያየ፣ ሻቢያም እየተመለከተ፣ ኦህዴድና ኦነግም እያዩ፣ ምሷን ሰጥተው ከተከዜ ማዶ ወደ ቀደመ ርስቷ መልሰዋታል። ሰነዱንም ቀዳደው ከወያኔ ጋር ቀብረውታል። እናም ዐማራ ተራራው ህወሓት የተባለችን የኢትዮጵያ መርዝ፣ ነቀርሳም የሆነች ሥጋ የለበሰች አጋንንት ከላዩም ላይ፣ ከኢትዮጵያውያኑም ላይ አሽቀንጥሮ ጥሏል። ተረኛ ህወሓት ሕወሓት ልጫወት የሚል ግልገል ጁንታ ካለ ሶቶ ግቡለት። አበቃ። አከተመ።
•••
አሁን ፊኒፊኔ ኬኛ፣ ራያ ኬኛ፣ ወልቃይት፣ ሁመራና ዳንሻ ጠገዴ ግን “የኢትዮጵያ ኖ” የሚለውን ለፍላፊ ካድሬ ታዬ ደንደአ የሚባል ዳግማዊ ጌታቾ ረዳ የሆነ ሰው ቢጮህ፣ ቢያጓራ አትስሙት። በመከላከያ ሠራዊት ስም ሊያስፈራራ የሚፈልገውን ኦቦ ታዬን መከላከያውን ራሱን ያዳነው ዐማራው ተራራው መሆኑን ጆሮውን ቆንጥጣችሁ በግድ ጋቱት። ክቡር ዐቢይ አሕመድ አስር ጊዜ ቢያጉረመርም፣ ቢያጉረጠርጥም አትስሙት። የጩጬውን ድንፋታ ከቁብም አትክተቱት። ሽመልስ አብዲሳ ከጉምዙ ነፍሰ ገዳይ ነፍሰ በላው የዐማራ ጠላት ከአሻድሊ ጋር ቢወዛወዝ፣ ቢንከላወስ አትስሙት። ኦህዴድ በተከፋይ ካድሬዎቹ በኩል እሪሪ ቋቀምበጭ ቢል አትስሙት። አሁን ቁማሩን ዐማራ የጠቅላይ በልቶታል። አለቀ።
•••
ዐረና የሚባል የሕወሓት ዲቃላ አረም፣ ፈንቅል የሚባል የዐቢይ አሕመድ ፒንሳ፣ የትግራይ ብልጽግና የሚባል የኦህዴድ ኮንዶም፣ በቀቀኖቹ እነ ዮናታን ተስፋዬ፣ ስዩም ተሾመ ቢያጓሩ ቆማችሁ አትስሟቸው። ጆሮም አትስጧቸው። ይልቅ ዐብንና ብአዴንን አጀግኑ፣ ፋኖንና ሚኒሻውን ተንከባከቡ፣ የአሳምነው ጽጌ፣ የአምባቸው መኮንንን ፍሬ የዐማራ ልዩ ኃይልን አዘምኑ፣ አጠንክሩ፣ አጠባብቁት። በደረሰባችሁ የዘር ማጥፋት የበቀል እጃችሁን እንዳታነሡ፣ ታላቅነታችሁን በይቅር ባይነት ግለጡት። የሰው አትፈልጉ፣ የራሳችሁን ግን እያናፈጣችሁ አስመልሱ። ለሌባ ድርድር አያስፈልገውም። ሌባን በፍልጥ እንጂ በፈሊጥ ለማስረዳት አትድከሙ። ዓለሙ ሁሉ የዐማራን ከፍ ያለ ሞራልና ስብዕና ይመሰክር ዘንድ በአንዳቸውም ላይ የበቀል እጃችሁን እንዳትሰነዝሩ። ዐማራው ተራራው፣ ከፍታው። ኣ
•••
በቀጣይ ሕገ መንግሥት ተብዬው ያሳጣችሁን፣ የቀማችሁን ርስት በሙሉ ለማስመለስ ተዘጋጁ፣ ሲሆን ሲሆን በምክክር፣ በክርክር፣ ካልሆነ ደግሞ በነፍጥ እያናፈጥክ ለማስመለስ ተዘጋጅ። ከእንግዲህ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ዐማራ ከኢትዮጵያ ውጭ በኬንያ በደቡብ አፍሪካ፣ በሱዳንና በግብጽ፣ በየመንና በሳዑዲ አረቢያ ያለውን፣ የሚኖረውን ዐማራ ባለበት ስፍራ ተከብሮ፣ ጫፉም ሳይነካ እንዲኖር ለማድረግ ምከር፣ ዝከር። ወጥር ዐማራዬ። በመንግሥታችሁ በመጣችሁ ጊዜ ግን አስቡኝ። ማሩኝ፣ ይቅር በሉኝ። ራሩልኝም። ሂኢ።
•••
ሰሞኑን ለአንድ ቀን ተጠርቶ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ሁለት ቀን በፈጀ የሞቀ ንትርክ የዐማራው ብልጽግና የእነ ደመቀ መኮንኑ ቡድን፣ የእነ ገዱ፣ የእነ ተሻገሩ ቡድን የእነ ታዬ ደንደአን፣ የእነ ሽመልስ አብዲሳን ቡድን ወጥ በወጥ አድርጎ አምበጫብጮ በድል አድራጊነት መውጣቱን በስብሰባው ተሳታፊ ከነበሩ ከሁለቱም ወገን ተሳታፊዎች አረጋግጫለሁ። ኦህዴድ ልኩን አውቋል። አፍህን ዝጋም ተብሏል። ኡስስስ  በራያ በወልቃይት በጠገዴ ጉዳይ ኡስስ። አለቀ።
•••
አሁን ክቡር ዐቢይ አሕመድ ስኳሬ የሆነች ሥልጣኑን ስለሚፈልጋት የኃይል ሚዛኑ ወደ አጋደለበት ፊቱን ያዞራል። ዐቢይ ዐማራውን ከመደገፍ ውጪ ሌላ አማራጭም የለውም። ለዐማራ ክብር፣ ለፋኖ፣ ለሚኒሻው ክብር፣ ለዐማራ ልዩ ኃይል የግዱን ክብር ሊሰጥ ይገባል። ዐማራ ተራራ ነው። በዲፕሎማሲም፣ በነፍጥም ዐማራው ያሸንፋል። የዐማራው የማሸነፍ ምስጢሩ ግን መጨቆኑ ነው። መገፋቱ፣ መሰደዱ ነው። መታረዱ መፈናቀል መገደሉ ነው። ዐማራውን አሸናፊ የሚያደርገው ፍትሕ ዳኛ ማጣቱ ነው። የማንም መንደሬ ዘረኛና ጎጠኛ የቀስት መለማመጃ መሆኑ ነው። ዐማራን አሸናፊ የሚያደርገው የማያባራው የሴረኞች ጭካኔ ከአዕምሮው በላይ በመሆኑ ነው። የግፍ ጽዋው ሞልቷል፣ ፈስሷል። አሁን መብቱን ለማስከበር ዐማራ ተራራው የማንም ይሁንታ አያስፈልገውም።
•••
ሁሌ እንደምለው ዐማራው ጨክኖ ከተነሣ፣ በውስጡ ያለውን መናናቅ፣ መከፋፈል ካስወገደ፣ ዐማራው ዐማራ ነኝ ብሎ ከተነሣ  በድኑ ብአዴንም ዐማራ ዐማራ ከሸተተ፣ ዐማራ ተራራው መጀመሪያ ራሱን ዐማራውን ነፃ ይወጣል። ቀጥሎ የእኛ ኢትዮጵያችን ነፃ ያወጣል። ዐማራ እኮ ፍርድ ዐዋቂ ነው። ፍትሕ ዐዋቂ ነው። ቢያንስ እንደ ሽመልስ አብዲሳ አሳርዶህ ገዳይህን አይደብቀውም። አይሸልመውም። ዐማራ ዐማራ ሆኖ ቢነሣ እኔም የናፈቀችኝ ሃገሬ  ከነ ልጆቼ እመለሳለሁ። ግሸን፣ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጣና ክርስቶስ ሠምራ፣ ዙርአምባ፣ ደብረ ሊባኖስ ደብረ ደሞ፣ ቁልቢ፣ ጻድቃኔ፣ ኢቲሳም እሄድ እሳለም ነበር። ነፃ አውጪዬ ዐማራው ነው። ዐማራው ቢፋቅ ውስጡም ላዩም ኢትዮጵያዊ ነው። ደሙ ራሱ አረንጓዴ ቢጫ፣ ቀይ ቀለም ነው። ቅልቅል፣ ድብልቅ የሌለበት ንፁሕ ኢትዮጵያዊ ነው። የዘር ቦለጢቃን በኢትዮጵያ ምድር የሚቀብረው ዐማራው ተራራው ነው። ቅር የሚልህ ካለህ ቅራሪ ጠጣ። ከፈለክ ጧ በል። ፈንዳ። እውነቱ ይሄው ነው።
•••
ዐማራ ተራራው ወጥር። በርታ፣ ወጥር፣ አይዞኝ አንበሳዬ፣ ለጥቃቅን ቀበሮ ሃሳብ፣ ጥንቸል ለሚመስሉ ሃሳቦች ቆመህ ጊዜህን አታባክን፣ ጥንቸሏ ትዝለል፣ ድንጋይ ይዘህ እሷን ለመውገር አትድከም። ጊዜህንም አታባክን፣ ምንም አባቷ አታመጣም። አሁን ፊትህን ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ መልስ። ወደ መተከል ተመልከት። በዚያም ገዳይህን በአናቱ ትከል። ሽመልስ አብዲሳ ያድነው እንደሁ እስቲ አብረን እናያለን።
… ለዛሬ አበቃሁ። ካነሰ ግን እያረፍኩ፣ እየቆየሁም እጨምራለሁ።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ህዳር 27/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic