>

16ቱ የትህነግ የማጎሪያና ጭፍጨፋ ካምፖች...!!! (ከደምስ ይግዛው-እጩ ዶ/ር) 

16ቱ የትህነግ የማጎሪያና ጭፍጨፋ ካምፖች…!!!

ከደምስ ይግዛው (እጩ ዶ/ር) 

 

*…. ትህነግ ከምስረታው ጀምሮ እስከ ሞቱ ድረስ ህዝባችንን ያሰቃየባቸው የምድር ውስጥ ሲኦሎችን እነሆ! 
 
አቶ ገብረ መድኅን አርአያ የቀድሞው የትህነግ የኢኮኖሚ ክፍል ኃላፊ የነበሩ ሲሆን የትህነግን አካሄድ በመቃወም በ1980ዎቹ መጀመሪያ በወቅቱ ለነበረው ወታደራዊ መንግሥት እጃቸውን በመስጠት ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ደግሞ ኑሯቸውን በአውስትራሊያ በስደት ያደረጉ የአድዋ ተወላጅ ናቸው፡፡
 ግለሰቡ በ2012 እ.ኤ.አ የሰጡትን ቃለ ምልልስ መሰረት በማድረግ የትህነግ ማጎሪያና የጭፍጨፋ ካምፖች ውስጥ የሚሠራው ዘግናኝ ታሪክ እንዲህ ይቀርባል፡፡
ሀለዋ ወያነ (የወያነ እስር ቤት) ዓላማው ሁለት ነበር፡፡ የወልቃይት ጠገዴና ሌሎች አካባቢዎች  አማራ የተቀማውን ማንነቱንና መሬቱን በተመለከተ ጥያቄ ሲያነሳ ለማሰቃየት እና  ትህነግን የማይቀበሉትን የትግራይ ተወላጆች ለመግደል ነው ይላሉ፡፡
 
1. አጼ ሀለዋ ወያነ
~~~~
ይህ የማጎሪያና የመግደያ ካምፕ አድዋ ማይ ሀውያ አካባቢ የማገኝ የማሰቃያ ማእከል ነው፡፡  ቂንጣል በሚባል ቦታ የተመሰረተ ሲሆን ከምድር በታች የተሰሩ 150 ክፍሎች (Cells) አሉት፡፡ በየአንዳንዱ ክፍል ከ100 -150 ሰዎች ተጨናንቀው ይታጎሩበታል፡፡
በዚህ የማጎሪያ ካምፕ በአብዛኛው ሰዎች የሚታጎሩት ለቶርቸርና በጭስ በማፈን ወይም በ Chamber of Gas ለመግደል ነው፡፡  ይህ እስር ቤት በዋናነት የወልቃይት አማራዎችን ዘር ለማጥፋት ታቅዶ እንደተገነባም ይናገራሉ፡፡
በዚህ ማሰቃያ ቤት በተፈጸመው የግድያ  ዘዴ እስከ ከ1973 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ከ 15 ሺ በላይ አማራዎች  እንደተገደሉበት ተናግሯል፡፡
2. አዲ ማህበዳይ ሀለዋ ወያነ 
~~~
ይህ የማጎሪያና የመግደያ ካምፕ ሽሬ ውስጥ ሽራሮ በተባለ ቦታ የሚገኝ ሲሆን ከመሬት በታች የተገነቡ ብዙ ቤቶች ያሉበት ነው፡፡ ታሳሪዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ የወልቃይትና ጠለምት አማራዎች ሲሆኑ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ህጻናት ይገኙበታል፡፡
በዚህ ማሰቃያ ቤት ውስጥ በወንዶች ብልት እና በሴቶች ጡት ላይ አስከ 5 ኪ.ግ የሚመዝኑ ቁሶችን በማንጠልጠል ግፍ የሚፈጸምበት ነው፡፡
በጊዜውም እስር ቤቱ  45 ገዳዮችን በጠባቂ ስም ያካተተ ነበር፡፡ በዚህ የስቃይ ማማ  የሆነ የግፍ ማጎሪያ ውስጥ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በግፍ የተጨፈጨፉ መሆኑን ቃለ ምልልስ አድራጊው ይናገራሉ፡፡
3. ወርኢ ሀለዋ ወያነ
~~~~
በትግራይ አዲግራት አዴት በተባለ ቦታ የተመሰረተ ሲሆን የቀድሞው መንግሥት ሠራዊት ምርኮኞችን ለመግደያነት  ታልሞ የተሠራ ማጎሪያ ነው፡፡
በዚህ እስር ቤት ግድያ ይፈፀም የነበረው በክኒን መልክ በሚሰጥ ገዳይ መድኀኒትና በጋለ ብረት ሆድን በመተኮስና ያበዱ ውሾች በሚገደሉበት ሳይናይድ በተባለ መርዝ እንደነበር አቶ ገብረ መድኅን ይናገራሉ፡፡
በዚህ እስር ቤት ከ770 በላይ የቀድሞው መንግሥት ወታደሮች የተገደሉበት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
4. ጉንበንድ ሀለዋ ወያነ 
~~~~
ይህ እስር ቤት ህንፍሽፍሽ ፈጥራችኋል የተባሉ የትህነግ አባላት በ1969 ዓ.ም. የተፈጁበት ነው፡፡
ይህ እስር ቤት 30 ገዳይና ጠባቂዎች ነበሩበት፡፡
5. ሱር ሀለዋ ወያነ 
~~~~
ይህ ማጎሪያ ከጉንበንድ ወደ ሱር ስሙ የተቀየረ ሲሀነ የሚገኘው በቀድሞው ቦታ ሽራሮ አጽረቃ በሚባል አካባቢ የሚገኝ አደገኛ ማሰቃያ ነው፡፡
በዚህ የስቃይ ቤት ውስጥ ከመሬት በታች ሁለት ካሬ በሁለት ካሬ የሆኑ በርካታ ክፍሎች ያሉት ነው፡፡ በአንድ ክፍል ውስጥ እስከ 200 ሰዎች ታጭቀው ይታሰሩበት ነበር፡፡
በእዚህ እስር ቤት ከ19 እስከ 15 ሺ አማራዎች እንደተፈጁበች ቃለ ምልልስ አድራጊው ይናገራሉ፡፡
6. አዲ በእግሪድ ሀለዋ ወያነ
~~~~
በዚህ እስር ቤት ግድያ የማፈጸመው በመርዝና በሚስጥር በሚሰጥ መርፌ ነው፡፡
7. አይጋ ሀለዋ ወያነ 
~~~~~
የራሱ የሆነ ታሪክ ያለውና ከወልቃይት ጠገዴ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ሲሆን ብዙ የወልቃይት አማራዎች የተፈጁበት የእስርና የመግደያ ቤት ነው፡፡
8. ባህላ ሀለዋ ወያነ
~~~~~
ይህ ማጎሪያ የትግራይ አርበኞችና የወልቃይት ጠገዴ አማሮች የተፈጁበት ነው ሲሉ ይገልጻሉ፡፡
9. ፍልውሃ ሀለዋ ወያነ
~~~~
ይህ እስር ቤት በወልቃይት ጠገዴ የሚገኝ ሲሆን ከ15 ሺ እስከ 20 ሺ የሚደርሱ የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች የተፈጁበት ነው፡፡
10. ግህነብ ሀለዋ ወያነ
~~~~~
ይህ ማሰቃያ በሽሬ ማይገባ በተባለ አካባቢ አሁን ወልቃይት ስኳር ፋብሪካ የሚገነባበት በቃሌማ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝ ነው፡፡
በዚህ የስቃይ ማጎሪያ ሲሆን 200 የጉድጓድ እስር ቤቶች የነበሩትና አብዛኛው ጨለማ ቤቶችን የሚያካትት ነው፡፡  በዚህ የምድራችን የስቃይ ቦታ  ሟች ራሱ መቃብሩን የሚቆፍርበት ጭምር ነው፡፡
በዚህ እስር ቤት ታሳሪዎች በጨለማው ምክንያት ዓይናቸው የሚታወርበት፤ የሴቶችና ወንዶች ብልትም በእሳት በጋለ ብረት እየተተኮሰ የሚገደሉበት ነው፡፡
በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወየወልቃይት ጠገዴ አማራዎች እንደተገደሉበት ይገመታል፡፡
በዚህ እስር ቤት ከ1969 እስከ 1983 ዓ.ም. እስከ 40 ሺ የሚገመቱ የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች የተገየሉበት ነው፡፡
11. አዲ ጨጓር ሀለዋ ወያነ
~~~~~
ይህ እስር ቤት ብዙ አማራዎችና ፀረ ትህነግ አቋም የነበራቸው የትግራይ ተወላጆች  የተገደሉበት ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመሪያ  ህንፍሽፍሽ ወይም ትርምስና ማደናገር ፈጥራችኋል በሚል የተገደሉበት ነው፡፡
12. በለሳ ማይ ሀማቶ ሀለዋ ወያነ 
~~~~~~
ይህ እስር ቤት አድዋ ገረሁ ሰናይ አካባቢ ልዩ ስሙ እገራ በተባለ አካባቢ የተመሰረተ ሲሆን ብዙ የወልቃይት አማራዎች እና ፀረ ትህነግ አቋም የነበራቸው የትግራይ ተወላጆች የተገደሉበት ነው፡፡
በዚህ እስር ቤት 25 አባላት የነበሩት የገዳይ ቡድን የነበረ ሲሆን እስረኞች የሚመረመሩትም በግርፋት፣ በእሳት በጋለ ብረት ራቁትን ካደረጉ በኋላ አስተኝቶ ከግንድ ጋር በማሰር እንዲሁም በወንድ ብልትና በሴቶች ጡት ላይ አሸዋ በማንጠልጠል የሚከናወን ነበር፡፡
እስከ ሚያዚያ 1972 ዓ.ም. ድረሰ  በአረጋዊ በርኸና ስብሐት ነጋ ትእዛዝ ሰጭነት153  የትግራይ አርበኞችና  232 ታጋዮች ህንፍሽፍሽ ፈጥራችኋል ተብለው እንደነ ወርቀ ልዑል፣  ግራዝማች ታደሉ ያሉ ታስረው የተገደሉበት ነው፡፡ የጅምላ መቃብርም ያለበት ነው፡፡
13. አዲ ዋእሎ ሀለዋ ወያነ 
~~~~~
በዚህ እስር ቤት ብዙ ሺ አማራዎች ተገድለዋል፡፡
14. አስገራ ሀለዋ ወያነ
~~~~~
ይህ ማጎሪያ በአፋር ክልል አቅራቢያ የተመሰረተ ሲሆን ብዙ ዜጎች ተገድለውበታል፡፡
15. ማሩዋ ሀለዋ ወያነ
~~~~~
ይህ እስር ቤት አድዋ ገርኡ ሰናይ ሀውያ አካባቢ የሚገኝ የማሰቃያ ማእከል ነው፡፡
16. የዱጋ ዱግን ማጎሪያ፣ ማሰቃያና መግደያ ካምፕ
~~~~
ይህ የማጎሪያና ማሰቃያ ካምፕ ወይም የኮንሰንትሬሽን ካምፕ በሽረ አስገደ ወረዳ ዱጋ ዱግኒ ቀበሌ በሚገኝ ተራራ ሥር ከመሬት በታች በ 2 ኪ.ሜ. ጥልቀት ተቆፍሮ የተሠራ ነው፡፡
 የስቃዮች ሁሉ ማማ በሆነው በዚህ የማሰቃያ ማእከል በምሽግ መልክ የተሰሩ በርካታ ክፍሎች ሲኖሩት በአንድ ክፍል ከ 70 እስከ 80 ሰዎች ተፋፍገውና ተጨናንቀው ያለመኝታ ወይም በፈረቃ በመተኛት ለግድያ የሚዘጋጁበት ነው፡፡
በዚህም ብዙ የወልቃይት፣ ጠለምትና ጠገዴ  አማራዎች አበሳና ስቃይ ከይተው የሞት ጾዋን ጨልጠውበታል፡፡
በዚህ ማጎሪያ ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ግፍ ሲፈጸምበት የቆየ ሲሆን በ1976 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ብቻ ከ 3500 የሚልቁ የወልቃይት ሴት ፣ ወንድና ህጻናት ተፈጅተውበታል፡፡
Filed in: Amharic