>
5:13 pm - Monday April 19, 2849

በመተከል ዞን የሰው ደም በየእርሻ ማሳው እየፈሰሰ ነው"  (ዘጋቢ:-አዳሙ ሽባባው)

በመተከል ዞን የሰው ደም በየእርሻ ማሳው እየፈሰሰ ነው” 

ዘጋቢ:-አዳሙ ሽባባው

* ነዋሪዎችም የድርሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው

 
ባሕር ዳር፡  ታኅሣሥ  06/2013 ዓ.ም (አብመድ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አሁንም ሰው እየሞተ ነው፣ መፈናቀሉም ቀጥሏል፣ ነዋሪዎቹም የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። ቀደም ሲል ቀጣናውን ለማርጋጋት ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ወደ ቦታው አቅንተው ነበር፣ አካባቢው በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደርም ተደርጓል። ይሁን እንጂ አሁንም ሞት እና መፈናቀል እየተባባሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአብመድ ተናግረዋል።
 
በቡለን ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች “የሰው ደም በየእርሻ ማሳው እፈሰሰ ነው፤ የሚመለከተው አካል ሊድርስልን ይገባል” ብለዋል። በዚህ ሁለት ቀን እንኳን ከጥቃት ለመዳን ሲሉ ከ300 በላይ ነዋሪዎች ቀያቸውን እንደለቀቁ ተናግረዋል። 
 
ነዋሪዎቹ ለአካባቢው የወረዳ አስተዳደር የድርሱልን ጥሪ ቢያሰሙም የሚመለከተው የጸጥታ አካል በፍጥነት ደርሶ ሕይወታቸውን መታደግ አለመቻሉንም ገልጸውልናል።
ጉዳዩን በሚመለከት ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም እና ህዝብ ደኅንነት ቢሮ ብንደውልም ስልክ አይነሳም፡፡ ምላሽ እንዳገኘን ይዘን እንቀርባለን፡፡
Filed in: Amharic