>
5:13 pm - Friday April 19, 6622

"በመግለጫ  ድንፋታ አንገት የሚደፋ ልዩ ሀይል የለንም!!!" (የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ተፈራ ወንድም አገኝ)

“በመግለጫ  ድንፋታ አንገት የሚደፋ ልዩ ሀይል የለንም!!!”

የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ተፈራ ወንድም አገኝ

     በቀስትና ገጀራ ሰዉ እየፈጀሁ እየዋልኩ አትናገሩኝ አይነት የጋጥወጥ መግለጫ ከወደ ቤንሻንጉል እየሰማን ነዉ።
    ክልሉ ያዘጋጀዉ ልዩ ሀይል ቅድሚያ ተግባሩ የክልሉን ነዋሪ ሰላም ማስጠበቅ እንጂ ዜጋን መታደግ አቅቶት ሊራዳዉ ከመጣ ሀይል ጋር መዋጋት አይደለም።
   ትላንት ሰበርናችሁ እያሉ ሲደነፉ የነበሩ የታሪክ አተላዎች በግፍ በየሜዳዉ ስለታረዱ ሰዎች ተጨንቀዉ ከማዉገዝ ይልቅ በፌስቡክ ሲነታረኩ መዋልን መርጠዋል።
   መታወቅ ያለበት ነገር ግን እርሻ ማሳ ዉስጥ ደም እየጎረፈ ኬክ ሲጎራረስ የሚዉል ነዉረኛ ወንበዴ ለፍርድ ለማቅረብ ሲታገሉ መሞት ለአማራ ልዩ ሀይል ክብሩ እንጂ ዉርደቱ ሆኖ አያዉቅም።ይህን ወደር አልባ ጀግንነት ደግሞ ያሳየዉ በመግለጫና ወሬ ሳይሆን አለም በአይኑ ባየዉ ተግባር ነዉ።
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ የተሰጠው መግለጫ ይህን ይመስላል:-
በህገ-መንግስት የተደራጀ ክልል ውስጥ ከፌደራል መንግስት ዕውቅና ውጭ ገብቼ እዋጋለሁ ብሎ በተደጋጋሚ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አዘል ቃላቶች ጭምር በመጠቀም መግላጫ መስጠት በህዝቦች መካከል ግልፅ ጦርነት ማወጅ ነው!!!
በፌደራል ሥራዓት ውስጥ የክልሎች ጤናማ ግንኙነት መኖር  ወሳኝ ተግባር ነው፡፡
 ክልሎች የተዋቀሩበት ዋና ዓላማ  በፌደራል ሥርዓት ውስጥ ሆነው በራስ አስተዳደር  ሥርዓት  አካባቢያቸውን ሙሉ በሙሉ የመምራት ኃላፊነት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡
ሆኖም ግን አንዳንድ  የአሮጌ ሥራዓት ናፈቂዎች አሁንም  ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም በጉልበት በማፍረስና ህገ-መንግስታዊ ሥርዓትን በመናድ በህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየውን አብሮነትና ወድማማችነት እንዲሻክር  ይባስ ብሎም  የብሔረሰብ  ስም በመጥቀስ  ጥላቻና  ግጭት እንዲበረታ  አልሞ በመስራት ላይ እንደሚገኙ  ለማስተዋል  ችለናል፡፡
 ባለፉት ዓመታት በሀገራችን  ፖለቲካ  ውስጥ በብሔርተኝነት፣ በዘረኝነትና  በጎጠኝነት አስተሳሰብ ሲያከፋፈሉንና ሲያባሉን የነበሩ አሁንም የብልፅግና ካባ ደርበው ሁልጊዜ ከብሔር ቆጠራ ያልወጡ በርካታ የለውጡ አደናቃፊ ኃይሎች በመንግስትና በፓርቲ መዋቅር ውስጥ ራሱን በመደበቅ  ክልል ከክልል ጋር በማጋጨት እኩይ ተግባራቸወን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
በአንድ ክልል ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ቶሎ የብሔር  እና በክልሎች የሚገኙ ብሔረሰቦች አጀንዳ  በማድረግ  ችግሮች የበለጠ እንዲባባሱ ከዛም አልፎ ሉዓላዊነት ያለው፤ በህገ-መንግስት የተደራጀ ክልል ውስጥ ከፌደራል መንግስት ዕውቅና ውጭ ገብቼ እዋጋለሁ ብሎ በተደጋጋሚ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አዛል ቃላቶች ጭምር በመጠቀም መግላጫ መስጠት በህዝቦች መካከል ግልፅ ጦርነት ማወጅ ነው፡፡
ስለሆነም በክልላችን ውስጥ የሚትኖሩ ብሔር-ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጦርነት ለማንም የማይበጅ አጥፊ ተግባር መሆኑን ተረድታችሁ  በተለይ በመተከል ዞን ሥር የሚትገኙ  ወረዳዎች በሚድያና በመግለጫ ጋጋታ ሳትደነጋገሩና ሳትረባበሹ  እንዲሁም በብሔርና በጎጥ ሳትከፋፈሉ ለረጅም ዓመታት ያካበታችሁትን የባህል እሰቶቻችሁን በመጠቀም  ከመንግስትና ከፀጥታ አካላት ጋር  ሆናችሁ አካባቢያችሁን  በንቃት  መጠበቅ ቀዳሚ ሥራ መሆኑን በመረዳት  እና አጥፊዎች  ለህግ  ቀርቦ ተገቢ ፍትህ እንዲያገኙ የራሳችሁን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ እንጠይቃለን።
Filed in: Amharic