>

በጣሊያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ሁለት የደርግ ባለስልጣናት ምህረት ተደረገላቸው...!!!

በጣሊያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ሁለት የደርግ ባለስልጣናት ምህረት ተደረገላቸው…!!!
*… ኘረዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምህረቱን በፊርማቸው ማፅደቃቸውም ታውቋል…!
 
ላለፉት 30 ዓመታት አዲስአበባ በሚገኘው ጣልያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የቆዩት ሁለቱ ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት ምህረት ተደርጎላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ተወሰነ።
በኤምባሲው ተጠልለው የሚገኙትና የምህረቱ ተጠቃሚ የሆኑት  የ85 ዓመቱ ሌተናል ኮሎኔልብርሃኑ ባይህ እና የ77 ዓመቱ ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ ናቸው።
ኘረዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምህረቱን በፊርማቸው ማፅደቃቸውም ታውቋል።
የቀድሞ ባለስልጣናቱ ከአራት ዓመት በፊት ጀምሮ በምህረት እንዲለቀቁ የተለያዩ አካላት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የታወቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት ግን  ብሔራዊ እርቀ ሠላም ኮምሽን ከመንግስት ጋር በመነጋገር ሰዎቹ በምህረት እንዲለቀቁ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል ተብሏል።
የቀድሞባለስልጣናቱ ሰሞኑን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።(አዲስ አድማስ፤ ታህሳስ 10/2013)
#ፎቶ:- ከግራ ወደቀኝ ሌ/ኮ ብርሃኑ ባይህ እና ሌ/ጀ አዲስ ተድላ
Filed in: Amharic