ፖሊስ የእነ እስክንድር ነጋን ችሎት ለመከታተል የሔዱ ወጣቶችን አፍሶ አሰረ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
“ጠባችሁ ከሰንደቅ አላማው ነው ወይ? ለምን ትከለክላላችሁ?”
አቶ ስንታየሁ ቸኮል
አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ አልባሳትን ለብሰው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የፍርድ ሂደት ለመከታተል ችሎት የተገኙ ወጣቶችን ፖሊስ አስሯል። ወጣቶቹ የታሰሩት ልደታ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ነው። ይህንን በተመለከተ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት የባልደራስ አደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል “ጠባችሁ ከሰንደቅ አላማው ነው ወይ? ለምን ትከለክላላችሁ?” ሲሉ ጠይቀዋል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆነችው ቀለብ ስዩም የጤንነቷሁ ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱንና ከፍተኛ ህክምና እንደሚያስፈልጋት በለቅሶ ጭምር በጠየቀች ጊዜ የፍርድ ቤትም ታዳሚ በሀዘን ተውጧል።
ጥያቄዋን የመዘገበው ችሎቱ:- “ወይዘሮ አስቴር ስዩም በግል እንዲታከሙ” ሲል ቃሊቲ ወህኒ ቤትን አዝዟል።
ዛሬ ከታሰሩት መካከል የፓርቲው አባላት ካሱ ደስታ፣ ናትናኤል የዓለም ዘውድ፣ ኤርሚያስ ሃይሉ እና አብርሃም ጫኔ ይገኙበታል።
በተያያዘ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ አሻሽሎ ያቀረበውን ክስ ለማንበብ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ ለፊታችን አርብ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ባልደራስ