>

ለጁንታው ቅሪቶች ማምለጫ የታሰቡ ሁለት በሮች! (ሙሉነህ ዮሐንስ)

ለጁንታው ቅሪቶች ማምለጫ የታሰቡ ሁለት በሮች!

ሙሉነህ ዮሐንስ

1)የሱዳን ወታደራዊ ዘመቻ በሉግዲን
2)የማይጠምሪውን የኤርትራ ስደተኞች 
ሰሞኑን ከሱዳን ጋር በድንበራችን አካባቢ የተፈጠረው ወታደራዊ ግብግብ ምክንያት ምንድነው ብለን ስንፈትሽ አንድ ግልፅ ሆኖ እየመጣ መረጃ አለ። ከቦታው ያገኘነው መረጃ የሚከተለው ነው።
1)#የጁንታው ቅሪቶችን ለማስመለጥ ከሱዳኖች ወታደራዊ ዘመቻ በስተጀርባ ያላቸው “ዓላማ የተከዜ ተፋሰስን ይዞ (መጉዕ፣ ዋልድባ፣ ማይጠብሪ፣ ፍየል ውሃ እና ደጀና) መስመር ሳይቋረጥ ወጥ  እንዲሆንና ለጁንታው የማምለጫ መንገድ ለማመቻመች ነው። የአብደራፊው ግምባር ማስቀየሻ  distraction ነው።”
ሱዳኖች ይገባኛል የሚጠይቁበት መሬት እስከ ቋራ ያልፋል። ካርታው ላይ እንደምታዩት መተማ አካባቢ ደለሎ የሚባለውን የኢትዮጵያ ይዞታ በሙሉ የእኛ ነው ባይ ናቸው። ለዚህ መነሻ የሚያደርጉት ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ በእንግሊዝ ቅኝ ገዣቸው የተዘጋጀውን የ1902 (እኤዓ)ጉየን መስመር ነው። መስመሩ እንደምታዩት በካርታው ላይ የሚታየውን #የደለሎ ሰፊ ቦታ እና #ጓንግ ወንዝ ምላሽ ያለውን የኢትዮጵያ ሰፊ የእርሻ ልማት ቦታ ነው። ይህ ብቻ ስፋቱ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሚበልጥ እና ሱዳኖች #አልፋሽጋ ብለው ይጠሩታል። ይሁንና አሁን ሱዳኖች ሃይላቸውን እያሰባሰቡ ያሉት ግን #ሉግዲ ነው። ሉግዲ ማለት በሑመራ እና ምድረ ገነት (አብደራፊ) ከተማ መካከል የሚገኝ ሲሆን በወያኔ ዘመን ከሱዳን ጋር የደረቅ ወደብነት ከሱዳን መገናኛ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። ማይካድራ ከተማም ከዚሁ አቅራቢያ ናት።
ወደ 5,000 የሚጠጉ ሱዳን ፈርጥጠው የገቡ የትህነግ ታጣቂ የነበሩት አሁን ሱዳንን አስታጥቁንና አብረን እንውጋ ማለታቸውን አስተማማኝ መረጃ አለ። ሉግዲን ላይ ትኩረት የተደረገውም ወያኔ ማምለጫ ለማድረግ ያዘጋጃት እንደነበረች በጦርነቱ ሰሞን ሲነገር ነበር። አሁንም ከሉግዲን እስከ ጠለምት ግንባር ፍየል ውሃ ከተማ ላይ የተከበበውን የወንበዴ ቅሪት አስከፍቶ ለማስወጣት የሚደረግ የተልእኮ ጦርነት ነው። በጦርነቱ ዙሪያ የሶዳን መንግስት ሃይሎች ወጥ አቋም አልያዙም የሚባለውም ለዚህ መላምት ግብአት ይሆናል።
2)#ከሁለት ሳምንት በፊት ጎንደር ያሉ ምንጮች እንግዳ የሆነ እንቅስቃሴ አለ ማይፀምሪ የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች በብዙ አውቶብሶች ሙሉ ተጭነው ወደ አዲስ አበባ እየተወሰዱ ነው ብለውኝ ነበር። ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ስደተኞቹ ወደ ነበሩበት ተመልሰው ይስፈሩ ማለቱን ሰምተናል። ከላይ ከጠቀስኩት ሁለት መረጃ በፊት አፍላ ጦርነቱ ሰሞን አንድ የደረሰኝ መረጃ ግን የሚከነክን ነው። ምንጩ እንደሚለው የሞሳድ እና የምእራባውያን ሰላዮች በደባርቅ አካባቢ እያዣበቡ ነው። እነዚህ አይመስሌ ሰዎች እነ ደብረፅዮን አይያዙም ያመልጣሉ የሚል ጉዳይ በጦርነት መሃል “ለሁነኛ” ሰው ሹክ ብለው ነበር።
ለዚህ እቅድ ዋናው አንዱ ግብአት ከዚሁ ተከዜ አቅራቢያ ዋሻ የመሸገውን የወንበዴ አመራር ለማስወጣት #የኤርትራ #ስደተኞችን መጠቀም አንዱ የተዘጋጁበት መረብ ነበር ማለት ነው። ከተያያዘው ምስል እንደምታዩት ማይፀምሪ ላይ የኤርትራ ስደተኞች ትልቅ ካምፕ አለ። እነዚህ ምእራባዊያን ሰላዮች ሌላው ያዘጋጁት በአለም አቀፍ ድርጅቶች የሰብአዊ እርዳታ ልኡካን ስም የጁንታውን አመራሮች ሸፋፍኖ ማውጣት ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ዘግይቶም ቢሆን ጉዳዩ የገባው ይመስላል። ምመኪኖቹን በጥይት መትቶ እስከ ማስቆም እርምጃ ተወስዷል። በእኛ ዘገባዎች ግን ወደ ጦርነት ቀጠናው ከላይ የጠቀስናቸው ሃይሎች እንዳይገቡ ቀድመን መልእክት አስተላልፈን ነበር።
መደምደሚያ:- እስከ አሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የወንበዴው ቅሪቶችን ለማስመለጥ ከተከዜ ሸለቆ ካለችው ፍየል ውሃ ከተማ እስከ ሑመራ ግንባር ሉግዲን ድረስ ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ያስፈልጋል። በእርዳታ ስም ትግራይ ውስጥ ለመንቀሳቀስ እድል ካገኙ “የእርዳታ” ድርጅቶችም ከሚሽናቸው አይመለሱም። በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ተሰግስገው የሚሰሩት “local staff” የሃገር ቤት ሰራተኞች የወያኔ ቅጥረኞች ናቸው። ከሞሳድ እና ከምእራባውያን ጋር ያላቸውንም ትስስር ከላይ ስለገለፅነው ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
Filed in: Amharic