>

ብትንትን ያርጋችሁ (አልይ እንድሬ)

ብትንትን ያርጋችሁ

 

አልይ እንድሬ


     እድሜ ለለውጡና ለለውጡ ፈር ቀዳጆች እንጅ ዛሬማ ምናለ ሁሉም ይፅፋል፣ያሻውን ያወራል፡፡ እሚያስፈራው ነገር የለም፡፡ ምክንያት ቢሉ መርዛማው የህወሃት/ኢህአዴግ ክፉ ጥርስ እረግፎለታላ!! ((የሚገርመው ነገር ከቀበሌ እስከ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ተሰግስገው ከህወሃት/ኢህአዴግ ጋር ወግነው ህዝቡን ሲያሰለቹ፣ ደም ሲያስለቅሱ፣ሲበሉና ሲያስበሉ የነበሩ ሁሉ የማይቀረው ለውጥ ከመጣ በኃላ ጀርባቸውን አዙረው እንደ ለውጥ አርበኛው ሁሉ ህውሃት/ኢህአዴግን ሲያንቋሽሹ ነው፤ እንዲህ ዓይነቶቹን አባቶቻችን ‘‘እበላ ባይ’’ ሲሉ ይጠሯቸዋል፡፡ ሆድ ነው እንጅ፣እምነትና ጭንቅላት የላቸውም በሚል ይሆን? ))

     ወደ ዛሬው ቁምነገሬ ስመለስ ከላይ መጀመሪያው መስመር ላይ ልገልፅ እንደሞከርኩት እንደዛሬው መናገርና መፃፍ በማይቻልበት በዛ በክፉ ወቅት፣ በዛ ሰው በፅሁፍም ሆነ በቃል ሃሳቡን ባልገለፀበት ሁኔታ እንዲሁ በግምት ‘‘ለእኛ ያለህ አስተሳሰብ ጥሩ አይደለም፣ ጓደኛህ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነው’’፣ ወዘተ በሚል ሰው በሚታሰርበት፣በሚገረፍበት፣ በሚሰቃየይበትና በሚገደልበት ወቅት፣ ለህይወታቸው ሳይፈሩ የህወሃትን ክፋትና ሸፍጥ በድፍረት ሲያጋልጡ የነበሩ ጀግኖች ጨርሶ አልጠፉም ነበር፡፡ የህውሃትን ውድቀት በማፋጠንና ዛሬ ለመጣው ለውጥ ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ረገድ የነዚህ ፀሀፍት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡እንዲህ ካሉት ብዕረኞች ውስጥ ሰይፉ የተባሉ ፀሃፊ ገና ከጅምሩ የህወሃት/ኢህአዴግ ክፉ ስራ አስከፍቷቸው ነበርና የዛሬ 20 ዓመት ገደማ በደምሳሳው ድርጊቱን የረገሙበትና እኔም በደብተሬ ጀርባ ከትቤ የያዝኩት ፅሁፍ የሚከተለው ነበር፡፡ አቶ ሰይፉ በነሃሴ ወር 1993 ዓ.ም ‘‘ብትንትን ያርጋችሁ’’ በሚለል ርዕስ በጦቢያ መፅሄት ቁጥር 1 እትም ያሰፈሯት ግጥም እንዲህ ትነበባለች፡- 

ብትንትን ያርጋችሁ

ቅድስት ኢትዮጲያን ክብሯን የነካችሁ፣

ያንድነት ታሪኳን ተረት ነው ያላችሁ፣

ክፋት ተግባራረችሁ ሴረኛ ስማችሁ፣

ብርሃናችሁ ይጥፋ ቀን ይጉደልባችሁ፡፡

        ሀገርን በጎሳ የምትሸነሽኑ፣

         አንድነት ጠልታችሁ ህዝብ የምትበትኑ፣

         ውርደት ለናንት ይሁን ውጡ ከሰው ተራ፣

         ስማችሁ ምንጊዜም ባገር አይጠራ፡፡

ህዝቦቿን በብሄር የከፋፈላችሁ፣

ብሄን ከብሄር ያጨፋጨፋችሁ፣

መጠለያ ቤቱን ያፈራረሳችሁ፣

ያገር – የህዝብ ሀብት የመዘበራችሁ፣

ለእግራችሁም ጉድጓድ ሰይፍ ላንገታችሁ፣

መዓቱን ግለቱን ድኝ ያዝንብባችሁ፣

በምድርም በሰማይ ፍፁም አይቅናችሁ፡፡

          የታሪክ ቅርሶቿን ለውጭ የሸጣችሁ፣

        ሌላው ነባር ቅርሷን በግፍ ያጠፋችሁ፣

        ስማችሁ ይዋረድ ይርከስ እንደ ውሻ፣

        እሬሳችሁ ይሁን የመንገድ ቆሻሻ፣

        አፈር ሳር ቅጠሉ አራዊት እንስሳ፣

        ሰላም ይሰፍን ዘንድ በናንተ ይነሳ፡፡

        ፍርድ ያጣመማችሁ ለገንዘብ ስትሉ፣

        በቁም እያላችሁ በስቃይ ተበሉ፡፡

  ለሰው ልጆች መቅሰፍት ለግፍ የቆማቸሁ፣

 እንደ ባህር አሸዋ ብትንትን ያርጋችሁ፣

 በክፉ ስራችሁ እጅ እግራችሁ ይስለል፡

ለሰው ከተሰጠው ፀጋችሁ ይጓደል፣

ሞታችሁ ስጋችሁ ላፈር አይታደል፣

መዓት ወርዶባችሁ ግቡ ከሳት ገደል፡፡

Filed in: Amharic