>
5:26 pm - Tuesday September 15, 2753

"የነገስታቱን ምስል እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ  ለበሳችኋል" በሚል የታሰሩ የባልደራስ አባላት ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ!!! (በወግደረስ ጤናው)

“የነገስታቱን ምስል እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ  ለበሳችኋል” በሚል የታሰሩ የባልደራስ አባላት ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ!!!

በወግደረስ ጤናው

ለታህሳስ 15 ተቀጠሩ
 
ጠበቃ ሄኖክ ከስፍራው እንደገለፀልን አባላቱ ዛሬ ጠኋት አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት  ነው የቀረቡት።
ፖሊስ ያቀረበው የክስ ጭብጥም እጅግ አሳዛኝም አስቂኝም ነበር በማለት ጠበቃው እንደሚከተለው ገልፀውታል።
 ~ አድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራት ነው!
~ ታሪክ የማያስተምራቸው ታሪክን ይደግማሉ!
እንዲሁም የዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና የንግስት ጣይቱን ምስል  ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጋር ያለበት ቲሸርት  በመልበስ በአዲስ አበባ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲሞክሩ ያዝኳቸው የሚል ነበረ ብለዋል።
በመሆኑም ፖሊስ የምርመራ ስራየን ስላላጠናቀኩ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን ሲል መጠየቁም ተገልጿል።
የተከሳሽ ጠበቃ በበኩሉ ቲሸርቱን መልበስ በወንጀል የማያስጠይቅና ሆን ተብሎ አባላቱን ለማሸማቀቅ እንዲሁም በታሪክ እንዲያፍሩ የሚደረግ ጥረት በመሆኑ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የማያሰጥ ነው ብሎ ተክራክሯል።
ክርክሩን ያደመጠው ፍ/ቤት ፖሊስ ምርመራውን እስከ ነገ ጠኋት ጨርሶ እንዲቀርብ አዝዟል። ተከሳሽ የባልደራስ አባላትም እስር ቤት እንዲቆዮ ወስኗል።
ድል ለታሪካችን!
ድል ለዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አባት አጤ ምንሊክ እና ንግስት ጣይቱ ብጡል
ድል ለጥቁሮች የነፃነት ዓርማ ሰንደቅ ዓላማችን!!
Filed in: Amharic