>
8:23 pm - Tuesday June 6, 2023

በመተከል ንጹሀንን ሲያስገድልና ሲያፈናቅል  የኖረው ደበሊ በልጋፎን ጠቅላይ ምኒስትሩን አጅቦ ውሏል ... ❗(መተከል ሚድያ ኔትዎርክ)

በመተከል ንጹሀንን ሲያስገድልና ሲያፈናቅል  የኖረው ደበሊ በልጋፎን ጠቅላይ ምኒስትሩን አጅቦ ውሏል … ❗❗❗

መተከል ሚድያ ኔትዎርክ

ዛሬ አብይ አህመድን በመተከል አቀባበል ካደረጉትና ወደ አዲስ አበባም ከሸኙት  አመራሮች መካክል  ደበሊ በልጋፎ ን በኩራት ቆሞ መመልከት በአገሪቱ የፍትህ ስርአት ተስፋ ያስቆርጣል።
የአቶ ደበሊ በልጋፎ ቤት ዛሬም ተፈትሾ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ካራ(ቢላዋ)በኩርቱ ሙሉ፣ብዙ ቁጥር ያላቸው ክላንሽኮቭ መሳርያዎች፣የቡድን መሳሪያዎች፣የመገናኛ ሬድዮ መገኘቱ ታውቋል ❗
አቶ ደበሊ በልጋፎ ማለት የድባጤ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበረና ንፁሃንን ሲያስገድል የነበረ አሁን የተሻለ ስልጣን ተስጥቶት ወደ ዞን የተዘዋወረ ሲሆን ከተለያዩ አካላት ጋር ሲገናኝ እንደነበርና የመተከልን ህዝብ ለማስጨፍጨፍ ሲሰባሰቡ የተነጋገሩበትን አጀንዳ ማስታወሻ ደብተሩ ሲበረበር የተገኘ ሲሆን ሌሎችም የተለያዩ ምስጥሮች እንደያዙ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ሰምተናል❗
የሚገርመው ዛሬ ደበሊ መታሰር ሲኖርበት ከኮለኔል አያሌው በየነ ጋር በመማካከር እንዲድበሰበስ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል❗
የመተከል ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ሃላፊ (ከአንድ ወር በፊት) የድባጤ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበረ ደበሊ በልጋፎ መኖሪያ ቤቱ  በመከላከያ ሰራዊት ሲፈተሽ 6 የታጠቁ የጉሙዝ ወጣቶችን ጨምሮ ቦምቦች፤  4 ክላሽ እና አንድ ሱኪ  በጣም በርካታ ቀስት ጩቤና የተለያዩ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ተገኝቶበታል።
ይሄ ነብሰ በላ አውሬ ሊታሰር ቀርቶ አይዞህ በርታ ተብሎ ማበረታቻ፤ ተጨማሪ ጥቅምና ስልጣን እንደተሰጠው ነው  የተረዳነው።
#ኮለኔል አያሌው በየነ ማለት ከዚህ በፊት ጎንደር ላይ ብዙ ጉዶችን የሰራ መሆኑ ቢታወቅም አሁን የመተከል ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ተድረገው ለአስገዳይ የጉምዝ ባለስልጣናት ሽፋን እየሰጠ የሚገኝ ቁልፍ ሰው መሆኑ እየተሰማ ይገኛል❗
ኮለኔሉ ከዚህ ስራቸው በፍጥነት የማይቆጠቡ ከሆነ ሌሎች ብዙ ጉዳዮቻቸውን ይዘን እንደምንታገላቸው በግልጽ የምንናገር ሲሆን የአቶ ደበሊ በልጋፎ ለፍርድ የመቅረብና ያለመቅረብ ጉዳይ የመጨረሻው ቀዩ መስመራችን ይሆናል❗
Filed in: Amharic