>

ለመተከሉ ጭፍጨፋ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  ቀጥተኛ ተጠያቂ ናቸው! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ለመተከሉ ጭፍጨፋ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  ቀጥተኛ ተጠያቂ ናቸው!

ያሬድ ሀይለማርያም

*….ለመተከሉ እልቂት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የክልል እና የፌደራሉ ባለሥልጣናት ተጠያቂዎች ናቸው። ሽመልስ አብዲሳን ካባ ያለበሰች አገር ገና ብዙ የመተከል፣ ብዙ የሻሸመኔ፣ ብዙ የማይካድራ፣ ብዙ የወለጋ አይነት እልቂቶችን ልታስተናግድ ትችላለች!
ዛሬ በመተከል የሆነው ትላንት በቡራዩ፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በማይካድራ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከተከሰቱት ዘር ተኮር ጭፍጨፋዎች የተለየ አይደለም። ደጋግሜ እንዳልኩት በሁሉም ጥቃቶች ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፤ በተለይም ጥቃቶቹ  የተፈጸሙባቸው አካባቢዎች ላይ ያሉ የመንግስት ባለሥልጣናት አንድም ጥቃቶቹን ባለማስቆም እንዲሁም ለዜጎች በቂ ጥበቃ ባለማድረግ ቀጥተኛ ተጠያቂዎች ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሕግ ተጠያቄ ሊሆኑ በሚገባቸውን ሹማምንት ተከበው መቀጠላቸው በአገሪቱ ውስጥ ከሕግ ተጠያቂነት የማምለጥ ባህል እየደነደነ መምጣቱን ብቻ ሳይሆ የሚያሳየው ጠቅላዩ ከሕዝብ ደህንነት ይልቅ ለራሳቸው ሥልጣን ቅድሚያ የሚሰጡ ሰው መሆናቸውንም ጭምር ነው። ለግፉአን እንቆማለን የምትሉ እና ለሰዎችም መብት እንቆረቆራለን የምትሉ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን እና የመብት አቀንቃኖች ኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው እየተፈጸመ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፍራ እና የመንግስትን ከልክ ያለፈ ዳተኝነት በግልጽ ቋንቋ በማውገዝ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የመጠየቅ ሞራላዊ ግዴታ አለባችሁ።
Filed in: Amharic