>

" አዲስ አበቤን ጠቀማችሁት እንጂ አልጎዳችሁትም፤ ይልቁንስ እነ ወለጋን፣  አርሲ  ባሌን ነው የጎዳችኋቸው  ...!!! "(ግርማ ካሳ)

” አዲስ አበቤን ጠቀማችሁት እንጂ አልጎዳችሁትም፤ ይልቁንስ እነ ወለጋን፣  አርሲ  ባሌን ነው የጎዳችኋቸው  …!!! “

 ግርማ ካሳ

ለኦሮሞ ክልል ፍርድ ቤት ብለው 1.8 ቢሊዮን ብር፣ ለኦሮሞያ ፖሊስ ጽ/ቤት
ብለው 700 ሚሊዮን ብር፣ ለኦሮሞ ጀግኞች መታሰቢያ ብለው 1 ቢሊዮን ብር. መድበዋል፡፡ እነዚህ ሶስቱ ፕሮጀክቶች ብቻ 3.5 ቢሊዮን ብር ደርሰዋል፡፡ ሶስቱም የሚገነቡት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ አላማቸው አዲስ አበባን የኦሮሞ
ብቻ (oromize) ለማድረግ ነው፡፡
የዴሞግራፊ ለውጥ ለማድረግና ከሌሎች ቦታዎች ኦሮሞዎችን በስፋት ለማስፈር ነው፡፡ ይሄ የዴሞግራፊ ለውጥ ፕሮጀክታቸውንም፣ ደግሞ አቶ ለማ መገርሳ፣ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ ሺመልስ በግልጽ የተናገሩት ነው፡፡ የኦሮሞን የበላይነት በአዲስ አበባ ለማስፈን በአዲስ አበባ መስተዳደር በኩል ብዙ ኢፍትሃዊ፣ ዘረኛ አሰራሮችን ዘርግተዋል፡፡
ይሄ አካሄድ ምን ያህል የኦሮሞ ማህበረሰብን ይጠቅማል ብላችሁ ብትጠይቁኝ መልሴ በጭራሽ አይጠቅምም የሚል ነው፡፡ አለመጥቀም ብቻ አይደለም፣ የሚጎዳም ነው፡፡
አንደኛ በኦሮሞ ማህበረሰብና በተቀረው ኢትዮጵያዊ መካከል መቃቃርን እየፈጠረ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበበ ያለው ብዙ ሕንጻዎች ያሉበት ሰፊ ቦታ የያዘውን የኦሮሞ ባህል ማእከል ብትመለከቱ አንድ የምንማረው ነገር አለ፡፡ ጭር ያለ ነው፡፡ ማንም ሰው ሲጎበኘው አይታይም፡፡ አልፎ አልፎ ከኦሮሞ ክልል የመጡ ካድሪዎችን ከማሰለጥን ውጭ ፡፡ ለምን ቢባል መልሱ ቀላል ነው፡፡
ሁለተኛ በኢኮኖሚ አንጻር ሌሎች የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች እንዲረሱ አድርጓል፡፡ የኦሮሞ ክልል መሪዎች ለኦሮሞ ክልል ፎቆችና ሰገነቶች መገንባታቸው የአዲስ አበባን ሕዝብ የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ክልል ዋና ከተማ
አዲስ አበበ ነው ብለው ለኦሮሞ ክልል የተመደበ ባጀትን አዲስ አበባ ላይ ማፍሰሳቸው የአዲስ አበባን ነዋሪ ነው የሚጠቅመው፡፡ እነዚህ በኦሮሞ ክልል
መስሪያ ቤቶች የሚሰሩት የሚኖሩ የት ነው ? የሚዝናናቱ የት ነው ? የሚበሉት የት ነው ? የሚሸምቱት የት ነው ? ገንዘባቸውም የት ነው የሚያፈሱት ? ታዲያ በዚህ ሁሉ ማን ነው የሚጠቀመው ? የጊምቢ ወይስ የሸገር፣ መቱ ያለ ጉሊት ወይስ ቂርቂስ ያለ ጉሊት ? የለገሃር ታኪስ ነጂ ወይንስ የነቀምቴ ባለ ባጃጅ ?? ዴሞግራፊዉን በመለወጥ አንጻር ደግሞ መቼም አይሳካላቸውም፡፡ እንኳን የአዲስ አበባን ዴሞግራፊን ሊቀይሩ የአዳማን፣ የቢሾፍቱን፣ የሰበታን፣ የዱከምን፣ የአሰላን፣ የሻሸመኔን ፣ የዝዋይን ….ዴሞግራፊን መቀየር አልቻሉም፡፡
ስላልቻሉ አይደለም እንዴ ከሻሸመኔ ውጭ ሆ ብለው መጥተው ሻሸመኔን ያወደሙት ??? ሌላው ማህበረሰብ ደንግጦና ፈርቶ ጥሎ እንዲሄድ ፡፡
ዴሞግራፊን ለማስፈር ብለው ሰዎች ሸገር ጭነው ቢያመጡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ፣ እንዲሰፍሩ የተደረጉትን ልጆቻቸውንም አዲስ አበቤ ነው
የሚያደርጋቸው፡፡ የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ መቀየር፣ አዲሳበባን የኦሮሞ ብቻ ማድረግ የማይሆን ነገር ነው፡፡ የሞኞች እቅድ! ሌላ ምርጫ ይኖራል፡፡ ኦህዴዶችና ወይንም የኦሮሞ ብልጽግናዎች አሁን በሽገር ፈላጭ ቆራጭ የሆኑት ተመርጠው ሳይሆን በግርግርና በሹመት ነው፡፡
በምርጫም መወገዳቸው አይቀርም፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳደር ከኦሮሞ ብልጽግና ውጭ ይሆናል፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳደርም አዲስ አበባ ራሷን
የቻለች ክልል እንድትሆን ያስደርጋል፡፡ ያኔ የኦሮሞ ክልል ከአዲስ አበባ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ታዲያ ይሄ ሁሉ ግንባታ ያኔ ምን ሊያደርጉት
ነው ???????? የገነቡት ፎቅ ተሸክመው ሊሄድ ነው ????
ከፍተኛ ፍርድ ቤቱን አምቦ፣ የኦሮሞ ልዩ ፖሊስ ጽ/ቤትን አሰላ ቢያደርጉትና በነዚህ ከተሞ ች ግንባታዎች ቢያደርጉ ግን በከተሞቹ የተወሰኑ የስራ እድል መፍጠር ይችሉ ነበር፡፡  ለኦሮሞ ጀግኞች መታሰቢያ ያሉት ደግሞ አሁን እርሱ ምን ያደርጋል ? ለዚህ ፕሮጅከት የሚያወጡት አንድ ቢሊዮን ብር 40 ፋብሪካዎች ፣ አስር መቱ፣ አሰር፣ አሰላ፣ አስር ነቀምቴ፣ አስር ጎባ ሊገነቡበት አይችሉም ወይ ? ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል አይፈጥሩም ወይ ? አዲስ አበባ እነዚህ ግንባታዎች መደረጋቸው እስቲ ምንድን ነው ለአብዛኛው የኦሮሞ ማህበረሰብ የሚፈይደው ?
አሁንም ደግሜ እላለሁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የፌንፊኔ ስካር ከማንም በላይ እየጎዳ ያለው የኦሮሞ ማህበረሰብን ነው፡፡ እነ ወለጋን፣ እነ አርሲ እነ ባሌን ነው እየጎዳ ያለው፡፡ በ30 አመታት ውስጥ እጅግ በጣም ዘመናዊ በሆነ መንገድ እነ አሰላ፣ ነቀሜቴን፣ መቱን የትናየት ማድረስ በቻሉ ነበር፡፡
Filed in: Amharic