>

ፈጣን፣ ተጨባጭ እና ዘላቂ መፍትሔ የሚሻው የመተከል ጉዳይ! (ኢሰመጉ)

ፈጣን፣ ተጨባጭ እና ዘላቂ መፍትሔ የሚሻው የመተከል ጉዳይ!

ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በማጣራት መንግሥት እና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ጊዜ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና፤ ይህን ጥሪና ማሳሰቢያ ተከትሎ ተግባራዊ እርምጃዎች በበቂ ሁኔታ ባለመወሰዳቸው፤ አሁንም የበርካታ ንጹኃን ሰዎች ሕይወት ከእለት ወደ እለት በአሳዛኝ ሁኔታ እየጠፋ ነው፡፡
ኢሰመጉ፤ ከትላንት በስትያ ማክሰኞ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከሌሊቱ 10፡00 ጀምሮ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ከ100 በላይ ንጹኃን ሰዎች ሕይወት ማለፉን ከተጎጂዎች ባሰባሰበው መረጃ ለማወቅ ችሏል፡፡ ኢሰመጉ፤ የአሁኑን ጥቃት ጨምሮ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለይም በመተከል ዞን ስር ባሉ በርካታ ወረዳዎች ላይ የሚፈጸመው ተደጋጋሚ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና ስቃይ እጅጉን አሳስቦታል፡፡
ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ቀስትን የመሳሰሉ ድምጽ አልባ መሳሪያዎችን በመያዝ በአካበቢው በጸጥታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሚሊሻዎችን ገድለው፣ ወደ መንደሩ በመግባት ቤቶችን በእሳት በማቃጠል እና ሰዎች ለመውጣት ሲሞክሩ ከውጪ ሆነው ጥይት በመተኮስ በጅምላ መግደል እንደጀመሩ ተጎጂዎች
ለኢሰመጉ ተናግረዋል፡…
Filed in: Amharic