የፋሽት አያት፣ አባት እና ልጅ ታሪክ ….!!!
ክርስቲያን ታደለ
1) «አማራ አይቀጠርም፤ አማርኛ መናገር ክልክል ነው፤ አማሮችን አፈናቅሉ፤ ከአማራ ቅኝ ግዛት ነፃ አውጪዎች ነን!»
~ አያት ፋሽት (አልበርቶ ሳባኪ፣1985)
ውጤት፦ ፋሽት በአርበኞች ብርቱ ክንድ ተደቁሶ ውርደትን ተከናነበ፤ የኃፍረት ማቅ ለበሰ!
2) «ጨቋኟ የአማራ ብሔር ዘላለማዊ ማኅበራዊ ረፍትን አታገኝም።»
~ አባት ፋሽት (የትሕነግ ማንፌስቶ፣1968)
ውጤት፦ ትሕነግ በአርበኞቹ ልጆች ወደ ተረትነት ተቀይራለች፤ ከተማ ስትገባ ወደ ህገ መንግስትነት የቀየረችው ማኒፌስቶዋም ገደል አፋፍ ላይ ደርሷል
3) “….አማራው አማራ ነኝ ያለ ቀን ከአማራ ጋር ጦርነት ገጥማችሁ የትግራይን ታሪክ እንዳታበላሹ ጦርነት ለአማራ ገበሬ ሰርጉ ነው ።
ወልቃይትን መልሱ የሚልበት ቀን ከመጣ በሰላም መልሶ ህዝባችንን በወልቃይት ላይ የሚኖረውን ጥቅም በፖለቲካ ታክቲክ አስጠብቆ አብሮ መኖር ነው ይሄን ካላደረጋችሁ ግን እመኑኝ እኛ ደደቢት ላይ እንደተመሰረትን ሁሉ ወልቃይት ላይ እንፈርሳለን…”
አባት ፋሽስት :- መለስ ዜናዊ ስለ አማራ ጀግንነት ለባንዳ ጓደኞቹ በሚስጥር የተናገረው …
ውጤት:- ፋሽስቶችም ትንቢት ይናገራሉ እንዴ ? ያሰኘ ክስተት ታየ
4) «ነፍጠኞችን[አማሮችን] በሰበሩን ቦታ አከርካሪያቸውን ሰብረናቸዋል…!»
~ ልጅ ፋሽት (ሽመልስ አብዲሳ፣ 2012)
ውጤት፦ የዚህኛው ምእራፍ ትግል ሲቋጭ የማን አከርካሪ እንደሚሰበር ታሪክ የሚፋረደን ይሆናል። አማራ ኃቅና እውነትን እስከያዘ ድረስ እንደማይሸነፍ ግን የትርክት ጌቶቻችሁን አወዳደቅ ማስታወስ በቂ ነው።
ማጠቃለያ፦ በየትኛውም የታሪክ አንጓ ከኃቅና እውነት በተቃርኖ አልቆምንም፤ ዛሬም ሆነ ወደፊትም አንቆምም። ኃቅና እውነት እስካለን ድረስ አንገታችንን ቀና አድርገን እንራመዳለን። ትናንት ያሸነፍነው ኃቅና እውነት ስላለን ነው። ነገም የምናሸንፈው ኃቅና እውነት ስላለን ነው።
መውጫ፦ ፋሽዝም ከወንድማማችነት ይልቅ ልዩነትን የሚዘራ ፀረ–ኢትዮጵያና ፀረ–ሰው የጥላቻ ደዌ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ ታግለን ድል ልናደርገው ይገባል። የፋሽዝም መክሰም የኢትዮጵያ ትንሳዔ መጀመሪያ ይሆናል!
በፋሽዝም አማራ ጠል ትርክት አንጋቢዎች ምክንያት ሰማእት ለሆናችሁ ወገኖቼ ዘላለማዊ ረፍትን እመኛለሁ!