የሁለቱ ጄኔራሎች ወግ…!!!
ኤርሚያስ ለገሰ
፩: ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ (በጦቢያ)
#1. “ነፍጠኛ ማለት የጦር መሣሪያ ፣ ነፍጥ ይዞ የመንግስት ሕግ የሚያስፈጽም ማለት ነው። ደመወዝ የለውም። መተዳደሪያውን የሚያገኘው ከገባር መሬት ነው። ደግሞ የአማራም፣ የኦሮሞም፣ የትግሬም ነፍጠኞች ነበሩ።”
#2. ” ቅኝ ገዥው ጣሊያን ኢትዮጵያ ከገባ ሁለት አመት በኃላ አማራውን አስወጡ ብሎ ሲቀሰቅስ ነበር። አንዳንዱ የቅኝ ገዢዎችን ስብከት ሰምቶ ችግር መፍጠር ጀመረ። ሁኔታው አጐቴን አባዲዩ ዋሚን በጣም እያሳሰባቸው ሄደ። አንድ ቀን የአካባቢውን ባላባቶች ሰብስቦና ሰርገኛ ጤፍ አቅርቦ <<ነጩንና ጥቁሩን ለዩልኝ>> አሏቸው። ሁሉም <<እንዴት ይችላል>> ሲሉ መለሱ። <<እንግዲያው ከአማራና ኦሮሞ ያልተጋባና ያልተዋለደ ምን አለ? ጠላት የሚላችሁን አትስሙ ሲሉ መከሯቸው። አማራውን ማሳደድ ከዚያ ግዜ ጀምሮ ቆመ። እኔም እንደ አጐቴ ነው የማስበው።”
#3. “የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ የመሰረትኩት ከልጅነቴ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ነፃነትና አንድነት ብዙ የደከምኩ ሰው ነኝ። ኤርትራ እንድትገነጠል ተደርጐ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጐሳ እንዲከፉፈል ሲገፋፋ በጣም አሳሰበኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነቱ በነፃነቱ ኮርቶና ተከብሮ እንዲኖር ስለምፈልግ ፓርቲውን ለመመስረት በቃሁ።”
* ” አጴ ምኒልክ እና ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቅኝ ገዥዎች ናቸው!’
ነጻና ሰላም የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር እየፈጠርን ነው¡¡¡ ማለቱ ይሆን???
* “ጁንታው በመደምሰሱ የኢትዮጰያ ህዝብ እፎይታ አግኝቷል፤ በመላ አገሪቱ አሁን ሰላም ነው”
ይህን አይን ያወጣ ውሸት ለአለም በሚናገሩበት ወቅት በየ እለቱ በመተከል በወለጋ በኮንሶ በመቶዎች እየተገደሉ፤ በሺዎች እየተፈናቀሉ ፤ ቤት ንብረት እየወደመ፤ የዜጎች ንብረት የማፍራት ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት ቀርቶ በህይወት የመኖር ዋስትና የታጣበት አገር ኤታሞዦር ሹም ሆኖ ሳለ
“….የኢትዮጰያ ህዝብ እፎይታ አግኝቷል፤ በመላ አገሪቱ አሁን ሰላም ነው” ይለናል።