ሱዳን በወረራ ስትይዘው ስትለቀው የኖረችውን የኢትዮጵያ ርስት ” መሬት ማስመለስ !” የሚል የፌዝ ስም ሰጥታ ወራለች…!!!
አዳነ አጣነው
ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ የምታካሄደው ወረራ ከ25 አመት በፊት የተወደብኝን መሬት ለማስመለስ ነው በሚል የአለምን እና የሱዳንን ህዝብ ለማደንገር እየሞከረች ነው ፡ እውነታው ምንድን ነው?
ሱዳን ሰሞኑን የኢትዮጵያን ግዛት በመጣስ ሰፊ ይዞታዎችን በመውረር የልማት አውታሮችን በማውደም ብዙ አርሶአደሮችን አፋናቅላለች፡፡ ሱዳን ያካሄደችው እና በማካሄድ ላይ ያለቸውን ወረራ ህጋዊ ሽፋን/Ownership of legitimacy ለመስጠት አሁን በሱዳን ጦር የተወረረው የኢትዮጵያ መሬት ከ25 አመት በፊት የሱዳን አካል እንደነበረ አድርጋ ለማቅረብ እየሞከረች ነው፡፡
እውነታው ግን በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ይህ አሁን ሱዳን በጦር ወራ የያዘችው የኢትዮጵያ መሬት የሱዳን አካል ሆኖ አያውቅም፡፡
ለማንኛውም ሱዳኖች ከ25 አመት በፊት ይዞታችን ነበር ለሚሉት አዲስ የርስት ባለቤትነት ትረካ እውነታው ምንድን ነው ብለን ጥያቄውን መመርመር እና መልስ መስጠት ያስፈልጋል ፡፡ ስለሆነም ነገሩ እንዲህ ነው፦
ወያኔ በሱዳን መንግስት ሙሉ ድጋፍ፤ በምእራቡ አለም እና ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ለደርግ ድጋፍ በመንፈጉ ምክኒያት በ1991 በፈረንጅ አቆጣጠር ደርግ ተዳክሞ ወያኔ የበላይነቱን ይዞ ወደ መሀል አገር ሲገፋ የደርግ ሰራዊት ይቆጣጠረው ከነበረው ከኢትዮ ሱዳን ድንበሮች እየለቀቀ ወደ መሀል አገር መሳብ ጀመረ፡፡ ሱዳን በኢትዮጵያ የመንግስት መዋቅር መዳከምን በመገንዘብ ብሎም የምትደግፈው ወያኔ ወደፊት ወደ መሀል እየገፋ ሲሄድ ጦሯ ከኻላ እየተከተለ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ጥሶ መግባት ጀመረ፡፡
በዚህም መሰረት በ1991 በግንቦት ወር የሱዳን ጦር ከባህርስንዱስ ተነስቶ የጓንግን ወንዝ በመሻገር የጦር ካንፖችን በደለሎ አካባቢ መሰረተ፡፡ የሱዳን ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው ደኑን በመመንጠር አዳዲስ እርሻዎችን መስርተው እንዲያርሱ አድረገች፡፡የኢትዮጵያ ገበሬዎች የሱዳንን ወረራ በመቃወም ለወያኔ አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ ጠፋ፡፡
እንደአጋጣሚ በ1996 በፈረንጅ አቆጣጠር በፈጣሪ ፈቃድ በወያኔ እና በሱዳን መንግስት መሀከል ያልታሰበ ከፍተኛ ችግር ተፈጠረ፡፡
የችግሩም መንስኤ የግብጹ መሪ ሆስኒ ሙባራከ አዲስ አበባን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ በሱዳን የሚደገፉ የግብጽ Islamic Brotherhood Party አባላት በግብጹ መሪ ላይ የግድያ ሙከራ በማድረጋቸው ነበር፡፡ የግድያ ሙከራ ያደርጉት አባላትም ገሚሶቹ አምልጠው ወደ ሱዳን መግባታቸው በመረጋገጡ ወያኔዎች ሱዳን ወንጀለኞችን አሳልፋ እንድትሰጥ በመጠየቃቸው እና ሱዳን ፈቃደኛ ሆና ባለመገኘትዋ ነበር፡፡
በዚሁ በ1996 በፈረንጅ አቆጣጠር በሱዳን እና በወያኔ መሀከል በግብጹ መሪ ግድያ ሙከራ ምክኒያት የሻከረው ግንኙነት ወደ ጦርነት አድጎ በሁለቱ አገሮች መሀከል ጦርነት ተካሄደ፡፡
በዚሁ ጦርነት በኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ለወረራዋ ከባድ አጸፋ በመመለስ በ1991 ከያዘችው የኢትዮጵያ ግዛት ተጠራርጋ ወጣች፡፡ ሱዳን ተሸንፋ በ1991 በወረራ ከያዘችው ቦታ ለቃ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ድንበር ወደ 1991 በፊት ወደነበረው መልከአምድር ተመለሰ፡፡
አሁን ሱዳን ከ 25 አመት በፊት በኢትዮጵያ ሚሊሻዎች የተወሰድብኝን መሬት ነው ያስመለስኩት የምትለው ትረካ ሲፈተሽ ከላይ እንደተጠቀሰው በ1991 ደርግ ሲወድቅ የተፈጥረውን ክፍተት በመጠቀም የሱዳን ገብሬዎች ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው ያረሱትን የኢትዮጵያ መሬት ሲሆን ይህ መሬት በ1996ቱ ጦርነት መልሶ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ የተደረገ የኢትዮጵያ አካል ነው፡፡ ሌላ ታሪካዊ ሂደት የለውም፡፡
=================
በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ በ2006 አካባቢ ያቀርብኩትን ጽሁፍ ጉዳዩን በበለጠ ለመረዳት ይረዳ ዘንድ አባሪ ተድርጓል፡፡ የ1996 ቱን የወያኔ እና የሱዳን ልዩነት እና የጦርነት ውጤት ያትታል፡፡
የኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ (2006 በፈረንጅ)
============
በ1991 በፈረንጅ አቆጣጠር የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅት ከሱዳን፣በተደረገለት ሰፊ ሁለንተናዊ ትብብር የደርግ መንግስት ሲወድቅ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር የተፈጥሮ ወሰን የሆነውን የጓንግን ወንዝ በመሻገር በኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ጦር በማስፈር የሱዳን የታወቁ ባለሀብት ገበሬዎችን አስፍሮ ከለላ በመስጠት ሱዳኖች የኢትዮጵያን መሬት ማረስ ጀመሩ፡፡
ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ ገዥ ለወያኔ አቤቱታ አቀረቡ፡፡
ወያኔም በወቅቱ በሰላም እንፈታውአለን ጊዜ ስጡን በሚል ህዝቡ ከሱዳን ጋር ጦርነት እንዳያነሳ ተማጸነ፡፡ህዝቡም በተወሰነ ደረጃ የወያኔን ጊዜ ስጡኝ ጥያቄ ከሞላ ጎደል ተቀብሎ እስከ 1992 በፈረንጅ በትእግስት ጠበቀ፡፡
በ1993 በፈረንጅ ሱዳን እንዳውም ይባስ ብሎ ከልጉዲ በሁመራ አቅጣጫ እስከ ነብስ ገባያ ድረስ ወደ 200 ኪሎ ሜ የሚያዋስነውን ለም መሬት እስከ 40 ኪሜ ዘልቆ በመግባት ይዞታውን አስፋፋ፡፡ህዝብ ለወያኔ አቤቱታ ቢያቀርብም ሰሚ ጠፋ፡፡
1993 የወያኔ መንግስት፣ ከወያኔ ሰራዊት የተቀነሱ አባላቱን ሽመለጋራ ላይ አስፍሮ የሱዳን ገበሬዎች በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ጥቃት እንዳይደርሳባቸው እንዲከላከሉ እና እራስቸውም በመሀበር ተደራጅተው እንዲያርሱ አሰፈረ፡፡ሱዳን ለሰፈሩ የወያኔ የተቀነሱ ጦር አባላት ትራክተር እና ቁሳቁስ አቀረበች፡፡
እንዳአጋጣሚ ከወያኔ የተቀነሱ የጦር አባላት ቦታው ለጤናችን አልተስማማንም በሚል ካፓቸውን ለቀው 1994 ተበተኑ፡፡የኢትዮጵያ ገበሬዎች በተቻልቸው መጠን ከሱዳን ጦር ጋር በመጋጨት ብዙም ሰላም ሳይሰፍን ሆኔታዎች እንዳሉ ቀጠሉ፡፡
1995/1996 በፈረንጅ በትግሬ-ወያኔ እና በሱዳን መሀከል አለመግባባት ተፈጠረ!
በሁለቱ ማለትም በወያኔ እና በሱዳን በ1995/1996 የተፈጠረው አለመግባባት ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም እድልን ፈጠረ፡፡ የወያኔ መንግስት ለሱዳን ውለታ ለመክፈል የኢትዮጵያ መሬት በሱዳን በ1991 ሲወረር ዝምታን ቢመርጥም በ1995/96 በፈረንጅ በሱዳን እና የትግሬ ወያኔ ቡድን መሀከል ልዩነት ተፈጠረ፡፡
የልዩነት ምክኒያት የሆነው በዋናነት የሱዳን የስለላ ድርጅት ከግብጹ የእስላም ወንድመማቾች/Islamic Brotherhood ንቅናቄ ጋር በመመሳጠር ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሚስጥራዊ ህዋስ ፈጠሩ፡፡ወያኔ መረጃው ደረሰውና ለሱዳን መንግስት እርማት እንዲደረግ ይጠይቃል፡፡ከዃላ ሆኖ የሱዳን መንግስትን ይመራ የነበረው ዶር አል ቱራቢ የወያኔን ጥያቄ ከምንም ሳይቆጥር መልስ ሳይሰጥ ቀረ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ በ1995 በፈረንጅ የግብጹ መሪ ሆስኒ ሙባረክ አዲስ አባባን ሲጎበኙ ከቦሌ ወደ ማረፊያ ቦታቸው በኢትዮጵያ ጸጥታ ሀይሎች ታጅበው በመጓዝ ላይ እንዳሉ የግብጽ Islamic Brotherhood ደፈጣ ተዋጊዎች ተኩስ በመክፈት በግጹ መሪ ላይ የግድያ ሙከራ አደረጉ፡፡ ሆኖም የግብጹ መሪም ከአደጋው ተረፉ፡፡
ወያኔም በሁኔታው ቁጭት ውስጥ ገባ፡፡፡፡በግብጹ መሪ ግድያ ሙከራ የተሳተፉ ሰዎች በከፊል አምልጠው ወደ ሱዳን መሸሸታቸው ታወቀ፡፡ ወያኔም በግብጹ መሪ የተሳተፉ ሽብርተኞችን ሱዳን ለኢትዮጵያ እሳልፋ እንድጸጥ ወያኔ ይጠይቃል፡፡ ሱዳን በወያኔ ጥያቄ ላይ አፌዘ፡፡
በወያኔ አና ሱዳን በግብጹ መሪ የግድያ ሙከራ ምክኒያት ግንኙነታቸው በብርቱ ተበላሸ፡፡
በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢም እንዲሁ ውጥረት ሰፈነ፡፡ በመተማ ደቡብ ታያ አካባቢ የወያኔ ወታደሮች ስለ ድንበሩ ጸጥታ ጉዳይ ለመወያየት 5 የጦር አባላት ወደ ሱዳን ታያ ላኩ፡፡
ሱዳንም ከወያኔ የተላኩትን የጦር አባላት መልእክተኞች በጥይት ረሸኗቸው፡፡ነገር ተበልሸ፡፡
የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ ሱዳን ያሳየነውን መልካም ወዳጅነት ወደ ንቀት ቆጠሩት/Abuse our Relationship ሲል ሱዳንን ወነጀለ፡፡
ወያኔ በ1996 በፈረንጅ ከልጉዲ አቅጣጫ እስከ ነብስ ገብያ ድረስ በሱዳን ወታድሮች ይዞታዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት ከፈተ፡፡
ከሳምንት ውጊያ በኻላ ሱዳን ተሸንፎ በ991 ይዞት ከነበረው የኢትዮጵያ ይዞታ ከ 5 አመት በኻላ ጥቅልሎ ወጣ፡፡ብዙ የጦር ኣባላቱ አንድ ሙሉ ጀነራልን ጨምሮ ተማረከ፡፡ የሱዳን ጦር አምርሮ ሸሸ፡፡
የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ወደ 1991 ወደነበረበት ተመለሰ፡፡ የሱዳኑ ጀኔራል ከተማረኩ ወታደሮች ጋር በኻላ ተለቀቀ፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬዎችም ተደሰቱ፡፡ይዞታቸውንም መልሰው ማልማት ጀመሩ፡፡የኢትዮጵያ መሬት መመለሱ ተረጋገጠ፡፡
ወያኔ እንደገና ሀሳቡን ቀይሮ በ2006 በፈረንጅ አንዳንድ የሱዳን ገበሬዎች የጓንግን ወንዝ ተሻግረው እንድያርሱ ፈቀደ፡፡
ወያኔ ቀብራ ከሄደቻቸው የጊዜ ቦምብ አንዱ በኢትዮ-ሱዳን ወሰን ይገባኛል ቁርሾ ነው!
ይህ ትኩሳት ላለፉት ግማሽ ክፍለዘመናት ተደባብሶ ቢተውም ሱዳኖቹ የመተማንና ቋራን ገበሬዎች በተደጋጋሚ ሲተነኩሱ ኖረዋል ።
የአገር ድንበር እያለፈ ጥቃት ለሚሰነዝር ሽርጥ ለባሽ የአርማጭሆና ቋራ ታጣቂ እያቀመሰ አደብ አስገዝቶ ቢኖርም የሰሞኑ የሱዳን አሰላለፍ ከተለመደው አግባብ መስመር ያለፈ ይመስላል ።
ሱዳን በየትኛዉም ጂኦፖለቲካል ስትራተጂያዊ አጋርነት ከኢትዮጵያ የተሻለ ወዳጅም ደራሽም የላትም!
በገልፍ አገራትም ሆነ በሌሎች አይዞህ ባይነት ስህተት ትሰራለች ብዬም አላምንም ።
ምክንያቱም አንድም በቅጡ የቆመ መንግሥት የላትምም በውስጥ የኢኮኖሚ ቀውስም የምትታመስ በመሆኗ ።
ከዛም ባሻገር በብሉ ናይል ፣ ዳርፉር ፣ ኑብና ኮርዶፋን ግዛቶቿ እንኳ ያሉ ተገንጣይ ታጣቂዎችን አደብ ማስገዛት ያልቻለ ሰራዊት ነው ያላት ።
የጦር መሪዎቻቸውም እንደኛዎቹ በዲስፕሊን ያልተገሩ በጥቅም የሚደለሉ ፣ በውጊያ ክህሎት ደካሞችና ከአገር ለቡድን ኢንተረስት የተቧደኑ ናቸው ።
ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ማንኛውንም ቁርሾ ከዲፕማቲክ አግባብ በቀር ሀይል ለመጠቀም መሞከር ቤንዚን ይዞ ከእሳት እንደመጠጋት ከመሆን የዘለለ እርባና የለውም!
በኛ በኩል የአርማጭሆ ፣ ቋራና መተማን ገበሬ ታጣቂዎች በቅጡ ጥይት ማቅረብ በቂያቸው ነው!
መንግስት አካባቢውን በሚገባ መጠበቅ በቸልታ ሊያየው የሚገባ አይደለምና ትኩረት ለጎንደር!