ከትላንት የዛሬው ከከፋ፤ ነገ የሚሆነው እጅግ ያስፈራል…!!!
ያሬድ ሀይለማርያም
* የግፉአን አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው ይላል ቅዱስ መጽሐፉ። ሕውሀት የገባችበት ጥልጉ ጉድጓድ ማለት ነው። ያ ጉድጓድ ቶሎ ካልተደፈነ ብልጽግናዎችም የህውሃት እጣ ፈንታ ነው የሚጠብቃችሁ…!!!
የትላንት ግፈኞች እየተሳደዱ ከየዋሻው በሚታሰሩበት እና ገሚሱም በሚገደልበት በዚህ ሰዓት በመተከል፣ በኮንሶ እና በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እና የመብት ጥሰት እያንዳንዱን ቀን በሀዘን እንድናሳልፍ ብቻ ሳይሆን ነገንም እንድንፈራ የሚያደርግ ነው። ዜጎች መንግስትን ሲፈሩ ኖረዋል ነገር ግን በመንግስት ላይ እምነት ያጡበት እንዲህ ያለ አስከፊ ግዜ ያለ አይመስለኝም።
ዜጎች በመንግስት ላይ እምነት የሚያጡት የሕግ የበላይነት ሲጠፋ፣ በዛም የተነሳ የሰዎች ሕይወት በየቀኑ አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ የመንግስት አካላት ከጥፋት ጏይሎች ጋር ተናበው ሲሰሩና ለዜጎች ደህንነት ስጋት ሲሆኑ፣ ተመሳሳይ ጥቃት በየቀኑ ሲፈጸም እና ለነገም ደህንነት ዋስትና ሲጠፋ ነው።
የግፉ ጽዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። የግፉአን አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው ይላል ቅዱስ መጽሐፉ። ሕውሀት የገባችበት ጥልጉ ጉድጓድ ማለት ነው። ያ ጉድጓድ ቶሎ ካልተደፈነ ብልጽግናዎችም የህውሃት እጣ ፈንታ ነው የሚጠብቃችሁ።