>

መከላከያ በመተከል ድባጤ ከ300 በላይ አስክሬኖችን የጅምላ መቃብር ሊፈጸምባቸው ነው ...!!! ( አሻራ ሚዲያ)

መከላከያ በመተከል ድባጤ ከ300 በላይ አስክሬኖችን የጅምላ መቃብር ሊፈጸምባቸው ነው …!!!

             አሻራ ሚዲያ 

* … በኦነግ ታጣቂዎችና በጉሙዝ ታጣቂዎች ጥምረት በግፍ የተገደሉትን አማራዎች አስክሬን ለማንሳት አካባቢው ማህበረሰብ ፍላጎት ቢያሳይም አማራ ሲገደል የማይደርሰው ኮማንድ ፖስት (መከላከያ) “አስክሬን ማንሳት አትችሉም” በሚል ለጅምላ መቃብር ሲዘጋጅ ከተመለከተው ህዝቡ ጋር ከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ ገብተዋል…
—–
በመተከል ድባጤ ወረዳ ጋሌሳ ቀበሌ የመከላከያ ሰራዊት የሟቾችን አስክሬን ማንሳት አትችሉም በሚል ፊት ለፊት መፋጠጣቸው ተሰምቷል፡፡
በትናንትናው ዕለት በኦነግ ታጣቂዎችና በጉሙዝ ታጣቂዎች ጥምረት በግፍ የተገደሉትን አማራዎች አስክሬን ለማንሳት አካባቢው ማህበረሰብ ፍላጎት ቢያሳይም አማራ ሲገደል የማይደርሰው ኮማንድ ፖስት አስክሬን ማንሳት አትችሉም በሚል ለጅምላ መቃብር ሲዘጋጅ የተመለከተው ህዝቡ ከህፍተኝ አለመግባባት ውስጥ ገብተዋል ሲሉ ምንጫችን ከቦታው ነግረውናል፡፡
ከአሁን በፊት ያለ ምንም ሀፍረት በግፍ የተገደሉትን ንጹሀን በጅምላ ቀብሮ ያለ ምንም ማጽናናት ስራ ላይ ነኝ የሚለው ኮማንድ ፖስት ዛሬ ደግሞ ሌላ ጅምላ መቃብር እያዘጋጀ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡
ህዝቡ ሟቾችን በክብር ለማሳረፍ ጥረት እያደረገ ሲሆን  ነገርግን መከላከያ ሐይሉ አይቻልም አንሰጥም፣ ወደዚህ ሰው እንዳይ ጠጋ በማለቱ ከህዝቡ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል።
300 የሚሆን አሰከሬን አንድ ቦታ ላይ አከማችተው እንደ በኩጅ በጅምላ ሊቀብሮቸው ነው በሚል በጋሌሳ ህዝቡ በከፍተኛ ቅሬታና ሀዘን ሚዲያዎች በአፋጣኝ ለህዝብ ያሳውቅልን ብለዋል። የመከላከያ  ስራም ንፁሃን መጠበቅ ሳይሆን ንፁሃንን መቅበር ሆኗል፡፡
ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው
Filed in: Amharic