>
5:29 pm - Monday October 11, 5745

የእነ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ውሎ!!! (ጥላሁን ታምሩ)

የእነ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ውሎ!!!

ጥላሁን ታምሩ

* ችሎት ለመታደም የሄዱ ግለሰቦች በፖሊስ ታገቱ!!!
ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ተቀጥሮ የነበረው የእነ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለዛሬ ጥር 5/2013ዓ.ም መሻሻሉ የሚታወቅ ነው።
በዚህም የነ እስክንድርን ችሎት ለመታደም የገቡ ግለሰቦች በጅምላ ተይዘው በፖሊስ ጣቢያ ታግተው እንደሚገገኙ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ተቀጥሮ የነበረው የእነ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለዛሬ ጥር 5/2013ዓ.ም መሻሻሉ የሚታወቅ ነው።
በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት እነ እስክንድር ፍ/ቤት ቀርበዋል ። የቀጠሮ መሻሻሉን አስመልክቶ ፍ/ቤቱ መጠነኛ ገለፃ በማድረግ ፤ በቀጣይ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የሚሰሙበት ቀን ፍ/ቤቱ የገለጸ ሲሆን ከጥር 26 ጀምሮ ዐቃቤ ህግ በቀን 4 ምስክሮችን እንዲያሰማ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡
 ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፤ የምስክር አቀራረብ አስመልክቶ የእነ እስክንድር ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የሆኑት በወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ መሰረት አስቀድሞ ስም ዝርዝራቸው ሊደርሰን ይገባል የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፤ ዐቃቤ ህግ በሰጠው ምላሽ የምስክር አቀራረብ አስመልክቶ በሌላ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያልንበት ጉዳይ ነው የእሱን ውሳኔ እየጠበቅን ነው ብለው ተከራክረዋል።
 በዚህም መሰረት ለምናቀርባቸው ምስክሮች ጥበቃ ስለሚያስፈልግ ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ ያድርግልን በማለት ምላሽ ሰጥቷል ።
የግራ ቀኝ ክርክር የሰሙት ዳኞች ፤ በችሎት ፊት ሲመካከሩ ለደቂቃዎች ከቆዩ በኋላ ፣ ወደ ውስጥ ገብተን እንነጋገር በማለት ለአፍታ ቆይታ አድርገው በመመለስ ፤ የምስክር አቀራረብ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በዚሁ ችሎት የተሰጠው ውሳኔ ተፈጻሚ እንደሚሆን፤ ነገር ግን የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር እና ማንነታቸ አስቀድሞ ይገለጽልን በማለት የቀረበውን ጥያቄ ፍ/ቤቱ አለመቀበሉን የመሐል ዳኛው ገልጸዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፦ በችሎት ታዳሚ የነበሩ ፤ የባልደራስ ፓርቲ አባላትና ደጋፌዎች ፤ ችሎት ከበቃ በኋላ ከፍርድ ቤት ውጪ በመንገድ ላይ በጅምላ ተይዘው ፤ በፍርድ ቤት አቅራቢያ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ይህ መረጃ ይፋ እስከሆነበት ሰዓት ድረስ ታግተው እንደሚገኙም ተመላክቷል ።
Filed in: Amharic