>
9:38 am - Friday June 2, 2023

ለሱዳንና ለግብፅ ወረራ 15 የመፍትሄ ሀሳቦች (መስፍን ሙሉጌታ)

ለሱዳንና ለግብፅ ወረራ 15 የመፍትሄ ሀሳቦች

መስፍን ሙሉጌታ


ኢትዮጵያ ትክክለኛ መስመር ላይ ነች የምንለው ሰላምንና ትእግስትን መምረጧና የሀገር ውስጥ ባንዳዎችን በትክክለኛ ጊዜ ድል መንሳትዋ ቢሆንም ሀገራችን ስለፈለገች ብቻ ሰላም ትሆናለች ማለት አይደለም።  የሰላም አማራጩን ግን አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል። ግብፅ፣ ሱዳንና እስራኤል ዳርዳር እያሉ የጉሙዝ አማፂ ያሰማሩ እንጂ የመጨረሻው ግባቸው የህዳሴው ግድብና ቤኒሻንጉል ክልልን መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን  ሀገራችንን መንግስት አልባ ማድረግ መሆኑን ግልፅ አድርገዋል። የዘርፉ ባለሙያ ባልሆንም የሀሳብ ትንሽ የለውምና ኢትዮጵያ በሚከተሉት ጉደዮች ላይ በቂ ስራ መስራት አለባት የሚል አከኝ። ጊዜ የለም በሚል መንፈስ።
1) ፕሮፌሰር ብርሀኑ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ አቶ ኦባንግ ሜቶ ሌሎችም ከምእራባዊያን ጋር የሚተዋወቁ ታዋቂ ባለሙያዎች መንግስትን በዲፕሎማሲ እንዲደግፉ ማድረግ ያስፈልጋል።
2)  ከቻይና፣ ከሩሲያ፣ ከባይደን አስተዳደር፣  ከአውሮጳ ህብረት እንዲሁም ከግብፅ ጋር የማይስማሙ እንደ ቱርክ ካሉ አካላት ጋር ለመስራት በየጊዜው መረጃ የሚሰጥ ካውንስል በአስቸኳይ ማቋቋም ቢቻል።
3) ግብፅና ሱዳን ውስጥ በቂ የደህንነት
ስራተጂ ነድፎ ኦፊሰሮችን አዘጋጅቶ  ማሰማራት።
4) የክልል ልዩ ሀይሎች ወደ መከላከያ ውስጥ ገብተው የሚጠረነፉበት የህግ ማእቀፍ አዘጋጅቶ ከወዲሁ ልምምድ ማድረግ ቢጀምሩ። መከላከያችንም ከትግራይ ተልእኮ በኋላ መልሶ የማደራጀት ስራ መስራት ቢቻል።
5) የኢትዮጵያና የኤርትራ የመንግስት አመራሮች በተለይ ጠ/ሚ አብይና ፕ/ት ኢሳያስ ለረቂቅ ድሮኖች ጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ማድረግ
6) አሁን የማንፈልገው ጦርነት ውስጥ እንደሆንን አስቦ መንግስትና ህዝብ ከአይምሯዊ ዝግጅት ያለፈ ስራ መስራት ቢቻል
7) ሊቢያ ውስጥና ቀይባህር አካባቢ ስራ መስራት ይገባል። ከተጠቃን በሱዳን እግረኛና የጦር ጄት ሳይሆን በግብፅ የባህር ሀይል ነው። ስለዚህ ቀይባህር አካባቢ የባህር ሀይል በውሰትም ቢሆን ማሰማራት።
8) የሚሊተሪ ጄቶች ሳንጠቀም በኢትዮጵያ የህዝብ ማመላለሻ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ሰፊ ስምሪት መስጠት።
9) እንደ ዳርፉር የግጭት ስበት ማእከሎችን መጠቀም።
10) ከአልሲሲ ተቃዋሚዎች ጋር በመስራት ለግብፅ መንግስት ውስጣዊ አጀንዳ መስጠት
11) ከአረብ ሀገራት መካከል ደጋፊ ለመፍጠር መጣር።
12) ቤኒሻንጉል ሙሉ ለሙሉ ለጠቅላይ ሚኒስተር ተጠሪ በሆነ ኮሚቴ እንዲተዳደር ተደርጓል። ትልቅ ስራ ነው። አሁን የህዳሴ ግድብ የጥቃት ኢላማ እንዳይሆንና ስራ እንዳይስተጓጎል በደንብ የተዘጋጀ አንድ ብርጌድ/ሻለቃ መከላከያ ሰራዊት ስምሪት መስጠት።
13) እንደሰማሁት ከሆነ 16 የግብፅ የጦር ጄቶችና 600 የጦር መኮንኖች ከባለፈው ህዳር ጀምረው ለግሱዳን ሰራዊት ስልጠና እየሰጡ ናቸው። በኛ በኩልም ዝግጅት ማድረግ።
14) ጦርነት የማይቀር ከሆነ የኛና የወራሪዎች የጥቃት ኢላማዎችን መለየትና ጦርነቱ በኛ ግዛት እንዳይሆን ማድረግ።
15) ቻይና ሩሲያና የባይደን አስተዳደር በቴክኖሎጂና በዲፕሎማሲ እንዲያግዙን ማድረግ። ደግሞም ጉዳዩ ከአፍሪካ ህብረት እጅ ወጥቶ ለአለም አቀፍ ሴክዩሪቲ ካውንስል መቀረቡ ስለማይቀር ከወዲሁ ሰነድ ዘዘጋጅቶ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቂ መረጃ መስጠት።
ኢትዮጵያዊነት አሸናፊነት ነው! ድል ለሀገራችን! ሁሌም!   
መስፍን ሙሉጌታ: EMAIL: mesfinmulugetaw@gmail.com
Filed in: Amharic